2022-07-09 20:15:27
ቢሰለችህም አታቆምም!፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨
ሁላችንም ልናሳካቸው የምንፈልጋቸው ግቦችና ልንተገብራቸው የምንፈልጋቸው ህልሞች አሉን። የትኛውንም ለውጥ ለማምጣት ይሁን የምትሰራው ሥራህን የምትፈፅመው ሲመችህ ብቻ ከሆነ ወደ ውጤት የሚያደርስህ በቂ ወጥነት መቼም አይኖርህም።
አንድን ልማድ ለማዳበር አስበህ ብትጀምረውና የሙጥኝ ብለህ እያስኬድከው ያለኸው ቢሆን እንኳን “ተወው” የሚልህ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር እርግጠኛ አደርግሃለሁ። ስትፅፍ መጻፍ የሚሰለችህ ጊዜ አለ። ስፖርት ስትሰራ መጨረስ የሚሳንህ ጊዜ አለ… ወዘተ፡፡
በፕሮፌሽናሎችና በአማተሮች መካከል ያለው ልዩነት እንደዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ሆነህና መስራት አስጠሊና አናዳጅ ነገር ሆኖብህም ስራህን መቀጠል ነው።
ፕሮፌሽናሎች በጊዜ ሰሌዳቸው መሰረት ሳያዛንፉ ይሰራሉ፤ አማተሮች ግን ከደበራቸው ተወት ያደርጉታል። ፕሮፌሽናሎች የሚጠቅማቸውን ነገር ያውቁታልና በዓላማቸው ይገፉበታል። አማተሮች ግን በጥቃቅን እንቅፋቶች እየተገፉ ከመንገዳቸው ይወጣሉ።
አንድ ልማድ በጣም አስፈላጊህ ከሆነ በየትኛውም ሙድ ውስጥ ሆነህ ልትተገብው ቆራጥነቱ ሊኖርህ ይገባል። ፕሮፌሽናሎች በመጥፎ ስሜት ውስጥ ሆነውም እንኳን መስራት ያለባቸውን ይሰራሉ። ደስ ላይላቸው ይችላል፤ ድግግሞሹን ላለማቋረጥ ግን መንገዱን አያቋርጡም።
በአንድ ነገር ላይ እጅግ በጣም ጎበዝ የመሆናቸው ብቸኛ መንገድ አንድ ነገር ማለቂያ በሌለው ሁኔታ እየደጋገሙ በመስራት ደስ መሰኘት ነው። መሰልቸትን ማፍቀር አለብህ!
/ከየልማድ ኃይል ገፆች/
አዎ! ጀግናዬ..! አስፈላጊና ወሳኝ እስከሆነ ድረስ
ቢሰለችህም አታቆምም፤ ቢደክምህም ወደኋላ አትልም፣ አትመለስም፤ ባይመችህም ለማድረግ አመቺ ሁኔታን ትፈጥራለህ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.6K views17:15