Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 80

2022-07-16 08:17:34 አሁን ምንም አያመልጥህም!
፨፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨፨
ይደረስበታል እያልክ ያመለጠህ፣
የት ይሔዳል እያልክ የሔደብህ፣
የት ይደርሳል እያልክ የሸሸህ፣ የራቀህና ያፈነገጠብህ የእራሴ የምትለው ሰው፣ ቁስ ወይም ሃሳብ ኖሮህ ያውቅ ይሆናል። በሰዓቱ የሚያመልጥህ አይመስልህም፤ አንተ ባለህበት እርሱም የሚኖር ይመስልሃል፤ ቢሸሽ እንኳን በቀላሉ የምትደርስበት፣ ቢለይህም መልሰህ የእራስህ ማድረግ የምትችለው፣ የምትገዛው ሊመስልህ ይችላል። ነገር ግን ካመለጠህ የማታገኘው ብዙ ነገር አለህ። ያወጣሃቸውን ቃላቶችህን አስታውስ፤ ያሳለፍካቸውን ውድ ጊዜያት ተመልከት፤ በፍቃድህ ያመለጡህን እድሎች ወደኋላ ቃኝ።

አዎ! ጀግናዬ..! አሁን ምንም አያመልጥህም፤ ነገን ግን አታውቅም፤ መጪዎቹ ጊዜያትም ዋስትና አይሆኑህም። የአሁን ውድነት ቦሃላ እስኪገባህ አትጠብቅ፤ የዛሬን ዋጋ ነገ ለመረዳት አትሞክር። ያለፈ ሁሉ የነበር ዋጋ ቢኖረውም ትርጉም አልባ ነው። ሂደት መልካም ቢሆንም የበዛው ቀጠሮ ግን ትርጉም ከመስጠቱም በላይ ትርጉም አልባ ዋጋ ቢስ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ልኬት፣ መጠን፣ ጊዜ ወሳኝ ነገር ነው። የዛሬ ሚስጥራት ዛሬ ይፈታሉ፤ የአሁን ተግባራት አሁን ይተገበራሉ፤ ደቂቃ በሄደ ቁጥር አሁንና ዛሬ ነገ ላይ ይውላሉ፤ ለሌላው የተዛባ ቀጠሮም መንገድ ይከፍታሉ።

አዎ! ሃሳብ እንኳን ቅፅበታዊ ነው። አሁን ያሰብከው ቦሃላ አይኖርም። እስከወዲያኛው ያንተ ቢመስልህም በማስታወሻ ካላሰፈርከው፤ ዳግም እንደምትመለስበት ካላስገነዘብከው ያንተ መሆኑ በጊዜያት ያበቃል። ምን ነበር እያልክ የምትብሰለሰልበት ሰዓት ሩቅ አይሆንም። ዳግም እንደማታገኛቸው እያወክ የምትቀጥራቸው፤ ቦታ የሰጠሃቸው በማስመሰል ልትሸውዳቸው የምትሞክረው፣ በግንዛቤህ እጥረት ሚዛን ያልደፉ በእውነታው ግን ሚዛን የሚደፉ አያሌ የህይወት ቅመሞች ይኖሩሃል። ብትገፋው የማይገፋልህ፣ ብትሸሸው የማይርቅህ፣ እለት እለት ሃሳቡ ሌላ ሃሳብ እየወለደ፣ ለጭንቀት፣ ለትካዜ መንገድ እየጠረገ የሚሄድ የዛሬና የአሁን ጉዳይ አለህና ቀጠሮ አታብዛ፤ የዛሬን ለዛሬ የአሁንን ለአሁን አድርገው። ከነገ ጋር ግብግብ አያስፈልግህም። አባሮሹን፣ ድብብቆሹን ተውና የማያመልጥህን አሁን፤ ያንተውን ዛሬ በፍካት ኑር፤ በነፃነት ተጠቀም።
ውብ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.9K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 20:33:54 የምትሰሪው ይሻልሻል!
፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨
የተሰራና በእራሱ ብቁ እንደሆነ የሚያስብ ሰው ያንቺን አስፈላጊነት የመመልከት እድሉ በጣም አናሳ ነው። ዋጋሽ የሚያድገው፣ አለመኖርሽ የሚያጎድለው እርዳታሽን በሚፈልግ ሰው ህይወት ውስጥ ነው። ሁሉ እያለው ብታገኚው፣ እርዳታን በማይፈልግበት ሰዓት ብታውቂው ያንቺ መምጣት የሚጨምረው ነገር አይኖርም። አንቺ ኖረሽም ሳትኖሪም የእርሱ ህይወት የሚያስፈልገው ነገር ከሌለ የአንቺ መኖር ዋጋ ማጣቱ አይቀርም።
አዎ! ጀግኒት..! የምትሰሪው ይሻልሻል! የምታግዢው፣ ዋጋሽ የሚታይበት፣ አስፈላጊነትሽ የገባው፣ ማንነትሽን የመረጠው፣ ከአጋርም ባለይ ረዳቱና ብርታቱ እንደሆንሽ የሚያስበው ያ አንቺ በትልቁ አሻራሽን የምታሳርፊበት ሰው ይሻልሻል። ሁሉን ቢኖረው ያንቺ አስፈላጊነት አናሳ ይሆናል፤ በሂደት የሚያድግ፣ የሚሳካ ሃሳብና ራዕይ ቢኖረው ግን ደጋፊው አንቺ ትሆኚያለሽ፤ ረዳቱ አንቺ ትሆኚያለሽ።

አዎ! የተሰራውን መፈለግሽ የሚጨምርልሽ አይኖርም፤ ያለውን መመኘትሽ ዋጋሽን አያሳድግም። እድገትን ካንቺ ጋር፣ ለውጥን ካንቺ ጋር የሚያስበው፣ ዋጋ የሰጠሽ፣ መኖርሽን ትርጉም የሰጠው እርሱ የልብ መሻትሽ ይሆን ዘንድ ፍቀጂ። የስኬቱ አጋዥ እንጂ የስኬቱ ተካፋይ ለመሆን አትሽቀዳደሚ። ብርቱ ሴት የእራሷን ወንድ ትሰራዋለች እንጂ የተሰራና በእራሱ የቆመን ሰው የምትመኝና የምታሳድድ አይደለችም። ልዩነት ፈጣሪነትሽን የሚያሳየው ኖሮት ስታገኚው ሳይሆን ሳይኖረው እንዲኖረው ባደረግሽው ልክ ነው። ዋጋሽ የሚገባው፣ አበርክቶትሽን፣ እርዳታሽን፣ ድጋፍሽን የሚረዳው በማደግ ላይ ያለውና ድጋፍን የሚፈልገው ነው። ዋጋሽን ማወቅ ከፈለግሽ ስኬታማ የሆነውን ሳይሆን ለስኬታማነት የሚታገለውን፣ የሚጣጣረውን፣ ድጋፍና እገዛሽን የሚፈልገውን ተጠጊ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.1K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:26:46 የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ!
፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨
የሰዎችን ህይወት ማድመቅ፣ ማድነቅ ክፋት የለውም፤ የእራስን መርሳት ማደብዘዝ ግን ትልቅ ክፍተትን ከብዙ ችግር ጋር ይፈጥራል። የየለት አጀንዳህ የሰዎች ህይወትና አኗኗር ከሆነ ለእራስህ ጊዜ ሊኖርህ አይችልም። የእነርሱን ትንሽ አጀንዳ በማጉላት ከተጠመድክ ያንተው ትልቅና ወሳኝ አጀንዳ አስታዋሽ በማጣት ስር ሰዶ ውድቀትህን ሲያፈጥን ልትመለከት ትችላለህ።

አዎ! በቅድሚያ የእራስን ሸክም ማራገፍ ስልጣኔ ነው። ሁን ተብሎ የሚሰራን ድራማ የህይወት አጀንዳ ማድረግ ቅለትና ብክነት ነው። አለም አዳዲስ አጀንዳ አታጠም፤ አዳዲስ ወሬ አታጣም። ያንተ በእርሷ ጊዜያዊ ድራማ መታለል ዋጋ እንደሚያስከፍልህ፤ ዋጋ እንደሚያሳጣህ አስታውስ።
አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ! አለምን የማትሰማበት፣ ከጫጫታዋ ዞር የምትልበት፣ በማይረቡ አዳዲስ አጀንዳዎቿ የማትታለልበት፣ አኗኗሪ መሆንህ የሚያበቃበት፣ ነዋሪነትህ የሚጀምርበት ጊዜ አሁን ነው፤ ዛሬ ነው።

አዎ! ፈተና ከተባለ እራስን ከማስረሳት በላይ የሚፈትን ነገር አይኖርም። በየቀኑ የሚመጡ የአለም ክስተቶች ለእራሳችን ጊዜ እንዳይኖረን፣ በእነርሱ ጉዳይ መጠመድ፣ መብከንከን ዋነኛው ተግባራችን እንዲሆን እያደረጉን ነው። የሌላውን ስናደምቅ የእኛ ሲፈዝ፣ የሌላውን ስናሳምር የእኛ ሲበላሽብን መመልከት የየለት ተግባራችን ኋኗል። ህይወትህ ላይ ጠብታ ያክል ነገር የማይጨምር የአለም ጋጋታ ማብቂያው አሁን ነው። በጊዜያት ለማይቀረው ለእራስህ ጊዜ መስጠት ጀምር፤ አለምን ካንተ ቦሃላ ነችና ቀዳሚውን የህይወት አጀንዳህን እራስህ አድርግ።
ውብ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.3K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:10:06 ዝምታህ የእውቀት ይሁን!
፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨
ዝምተኛን ዝቅ አድርገህ አትገምት፤ አሳንሰህ አትመልከት። ከሚናገረው በላይ እንደሚያውቅ አስታውስ። የተቆጠበው ንግግሩ የሚቀርለትን እውቀት ይቸረዋል። ንግርት ማንነትን አይገልፅም፤ ብዙ ማውራት ጥንካሬን አያሳይም፤ ከአፍ መውጠቱ የእውነትነቱ ማሳያ አይደለም፤ እውነታ በልብ ነው። ይልቁንም ምላስ አጥፊ፣ አስገማችና አስኮናኝ ነች። የተናገርከው ከሚጠፋ፣ ሳይሆን ከሚቀር ንግርቱ ቢቀርብህ ይሻላል።
አዎ! ካልተገባ ንገርት፣ ከልተረጋገጠ ወሬ ዝምታው የተሻለና ተመራጭ ነው። ዝምታን መምረጥ አንድም ከፍራቻ አንድም ከብስለት ይሆናል። የፍራቻ ዝምታ እድሎችን ሲያባክን የብስለት ዝምታ ግን እድሎችን ይፈጥራል። የንግግር ቅልጥፍናን ያጎናፅፋል፤ አንደበትን ርቱዕ፣ ቃላትንም ውብ፣ የተጠኑና የተስተካከሉ ያደርጋቸዋል።

አዎ! ጀግናዬ..! ዝምታህ የእውቀት ይሁን፤ ለጥሞና ይሁን፤ ለማስተዋል፣ ለመታነፅ፣ ለብስለት፣ ለእድገት፣ ለቅንነት ይሁን። የፍራቻ ዝምታን አስወግድ፤ በተገቢው ቦታ፣ ባስፈላጊው ሰዓት ሻረው። ቃል አውጥተህ ተናገር። ዝምታህ የሚያሳጣህ፣ ንግርትህም የሚያስገኝልህ ጥሩና ብርቱ ነገር ካለ ከመናገር፣ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበል። ዝምታም ገደብ ይኖረዋልና ከብዛቱ የሚገባህን አትጣ።
አዎ! በዝምታ ውስጥ አጢን፤ ትንሽ ተናገር፤ በጥልቀት ተመልከት፣ ስሜትህን ቆጥብ፤ እራስህን ተቆጣጠር፤ ለምላሽ አትቸኩል፤ አጣጥመው፤ ተመሰጥበት፤ እይታህን አንፅበት፤ ምልከታህን አድስበት።
የበዛው ዝምታህ እንዳያስረሳህ፣ እንዳያሳንስህ፤
ገደብ አልባው ምላስህም እንዳያጠፋህ፣ እንዳያስገምትህ በአስተዋይ ልቦና፣ በመልካም ስብዕና ከልብህ ተጠንቀቅ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.4K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:43:32 አንድ ሰው ሲመጣ..!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨
አዎ! አንድ ሰው ሲመጣ፣ ወደ ህይወትህ ሲገባ የወደድክለትንንና የተማረክበትን ማንነት ብቻ ይዞ አይመጣም። ልታከብርለትና ልትቀበለው የሚገባ ሌላ የእራሱ አመለካከት፣ የእራሱ አቋም፣ የእራሱ ባህሪ አለው። የምትወድለት እንዳለ ሆኖ የማትወድለትንና የማይመችህን ባህሪውንና ስብዕናን የመቀበል ግዴታ አለብህ። አንድ ሰው አንድ ነው፤ ደስ የሚለ ስብዕና፣ ማራኪ ውበት እንዳለው ሁሉ አንዳንዴ ተቀባይነት የሌለውና መልካም የማይባል ባህሪም ሊኖረው ይችላል። ለዚህ ግድፈትና ህፀፅ ምክንያትም በፍፁም ልትተወውና ከህይወትህ ልታስወጣው አትደፍርም። ፍሬውን ለመብላት አንዳንዴም ቢሆን በእሾሁ መወጋትህ ግድ ነውና።

አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ሰው ሲመጣ፣ አንተም ስትሔድበት፣ ስትመርጠው እርሱም ሲመርጥህ መምጣቱን ብቻ አትመልከት። ይዞልህ የሚመጣው እንደመኖሩ ይዞብህ የሚመጣውም ጉዳይ ይኖራል። የምትቀበለው እርሱን ብቻ ሳይሆን የእርሱ የሆነውንም ጭምር ነው። አንድን ሰው ለይቶ መውደድ፣ ለይቶ መቀበል አይቻልም። ወደህ የእራስህ ማድረግህ ካልቀረ የማትወዳቸውን እያንዳንዱን ባህሪውን፣ ከቻልክ የምትወደው ሰው ላይ ስለሆኑ ብቻ ልትወዳቸው ትሞክራለህ፣ ካልቻልክ ግን ልታሻሽላቸው፣ ልትቀይራቸው ትሞክራለህ፣ ካልሆነም አክብሮ መቀበሉን ትመርጣለህ።

አዎ! የወደድካትን፣ ያፈቀርካትን፣ የመረጥካትን ሴት አንተ አልሰራሃትም። ይህም እርሷ አንተ የምትፈልገውን ነገር ብቻ አላት ማለት አይደለም። የማትፈልገውም ነገር ሊኖራት ይችላል፤ በፈጣሪዋና በሰሪዋ ፊት ግን እንከን አልባ፣ ምንም የማይቀነስባት የማይጨመርባት ፍፁም ነች። ፍፅምናዋን መቀበል ባይቻልህ ባንተ ፊት ጉድለት መስሎ የታየህን ማክበር እንዲሁም ለመሙት መጣር ግን ትችላለህ።
አዎ! ባንቺ መነፅር፣ ባንቺ እይታ ፍፁምና እንከን አልባ የነበረው ምርጫሽ በሂደት የጎደለው ነገር እንዳለ ሊታይሽ ይችላል። ጅማሬሽ ላዩን ቢያይም ቆይታሽና ሂደቱ ግን ውስጡን በጥልቀት እንድትመለከቺ ያደርግሻል። የእውቀት ልኩም ሽፋን ሳይሆን ውስጥ ነውና ባወቅሽው ልክ አክብሮትን፣ ፍቅርን፣ እንክብካቤን መለገስ ልመጂ። የታየሽ ልዩነትና ክፍተት ስላወቅሽው ነውና እውቀቱን አትጠይው፤ ተቀብለሽ በመቻቻልና በመከባበር ወደፊት መጓዙን ሁነኛ ምርጫሽ አድርጊ።
ውብ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.6K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:48:44 መነሻው ዜሮ ነው!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
የየትኛውም ልዕልና መነሻው አንድ ወይም ሁለት ሳይሆን ዜሮ ነው። ሁሉም ሰው መነሻው ዜሮ ነው፤ ምንም ነው። ብዙ ነገር ከማጣት እልፍ ነገር ወደማግኘት፤ ተስፋን ከማጣት ትልቁን ተስፋ ወደመሰነቅ፣ ህልም ካለመኖር የትልቅ ህልም ባለቤት ወደመሆን፣ ራዕይን ካላማወቅ ግዙፍ ሁሉን አቀፍ ራዕይ ወደማስቀመጥ መሸጋገር። ቀላል ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ክብደቱም ሆነ ቅለቱን ባለቤቱ ያውቀዋል። ልዩነቱ ማጣትና ማግኘት መሃከል እንዳለው ልዩነት ነው። ከባዶ መነሳት ከፈራክ አንድ ጋር አትደርስም፤ ሁለትን አታገኝም ወደ ቀጣዩ ከፍታም መድረስ አትችልም። ደግነቱ ከዜሮ የምትጀምረው ስራው ወይም ትግሉን እንጂ ወስጥህ ያለውን ሃሳብና ተሰጥኦ አይደለም።

አዎ! ጀግናዬ..! መነሻው ዜሮ ነው! ከባዶ መነሳት ካስጠላህ፣ እድገቱንም ሆነ ለውጡን አትፈልገውም ማለት ነው። ትናንት ምንም ያልነበረው ዛሬ ግን ብዙ ያፈራ አያሌ ሰው አለ። ምናልባት በአንተነትህ የተሰጠህ ስጦታ ከዜሮ ጀማሪነት ነፃ ሊያወጣህ ይችላል። ነገር ግን በጥረትህና በልፋትህ የምታገኘው ውጤት፣ የምታተርፈው አዲስ ግኚት ከምንም ወይም ከዜሮ ወደ አንድ ከአንድም ወደ ሁሉት እያለ በሂደት የሚያድግና የሚጨምር ነው።

አዎ! ዜሮን አትፍራ፣ በማጣትህ አትሳቀቅ፣ አትሸማቀቅ። ማጣትን በማግኘት፣ ዜሮንም በእልፍ ቁጥሮች የመቀየር አቅም አለህ። ማመን በሚገባህ እመን፤ ማድረግ የሚገባህን አድርግ፤ መውጣት ያለብህን አቀበት ውጣ፤ መውረድ ያለብህን ቁልቁለት ውረድ። አጋዠህን ምረጥ፤ ደጋፊህን አዘጋጅ። ከምንም ተነስተህ ምን ማድረግ እንደምትችል፣ የት መድረስ እንደምትችል፣ ምን ማግኘት፣ ማስተካከል፣ መቀየር እንደምትችል ለእራስህም ሆነ ለሚያይህ ሁሉ አሳይ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.4K viewsedited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 08:32:56 ወርዶ ለሚያወርድህ እጅ አትስጥ!
፨፨፨፨፨፨፨/////////////፨፨፨፨፨፨፨
አንተን አሳንሰው፣ ዝቅ አድርገው እራሳቸውን ለማንሳት፣ ከፍ ለማድረግ ለሚጣጣሩ እምቢ በል። ዝቅታው እንደማይመችህ ይወቁ፣ ከእነርሱ በታች መውረዱ እንደሚጎረብጥህ ይረዱ። ሰውነትህ ብቻ ከእነርሱ እኩል እንድትሆን ያደርግሃል፤ ከኋላም ከፊትም የረባ ታሪክ ባይኖርህም ዛሬ በህይወት ቆመህ ለንፅፅር መብቃትህ በእራሱ እርሱ ፊት ያቆምሃል።
አዎ! ጀግናዬ..! ወርዶ ለሚያወርድህ እጅ አትስጥ፤ አንሶ ለሚያሳንስህ አንሰህ አትገኝ፤ ወድቆ ውዳቂ ለያደርግህ ለሚሞክር ፊት አትስጠው። ደረጃህን የመመደብ አቅሙ የማንም ሳይሆን የእራስህ ነው። ሁሉም ተነስቶ ለንፅፅር የሚያቀርብህ፣ ባንተም ላይ ጉራውን የሚነፋ፣ ጉብዝናውን የሚለካ ሰው አይደለህም።

አዎ! አንዳንዴ አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮ የእነርሱ ዝቅታና የበታችነት ጎልቶ ከታያቸው፣ ከእነርሱ እንደሚያንስ የሚያስቡትን ሰው ያስጠጋሉ፤ እርሱን እንደሚበልጡም በማሰብ እራሳቸውን በንፅፅር የተሻሉ እንደሆኑ ማሰብ ይጀምራሉ። ቀድሞውኑ ለመረጡት ሰው የወረደ ደረጃ እንደሰጡት በመዘንጋት እንደ አዲስ ሌላ የተሻለና ይበልጣቸው የነበረን ሰው የበለጡ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ሰውን መብለጥ አዳጋች ነው፤ ያልተገባ እልህ ውስጥም ያስገባል፤ በአንደኛው ዘርፍ መብለጥ ቢቻል በሌላኛው መበለጡ አይቀርምና።
አዎ! እራስህን ብለጥ፤ ከእራስህ ተሽለህ ተገኝ። ንፅፅሩ፣ ውደድሩ ከእራስህ ጋር ይሁን። ማንም ሊያሳንስህ ቢጥር አለማነስህን አሳይ። ወድቆና አንሶ መገኘት ከትናንት ማንነት የባሰ የወረደ ማንነት ውስጥ መገኘት ነውና የቀድሞውን አንተን አሸንፈው፤ አንሰው ለሚያሳንሱህ ትኩረት አትስጥ። ጫወታውን በገዛ ሜዳህ ከእራስህ ጋር አድርገው። ሌላውን ተሸናፊ ለማራቅ እራስህ ላይ አሸናፊነትን ተቀዳጅ፤ ከአሸናፊዎች፣ ከብርቱዎች፣ ከተሻሉት፣ ከድንቆች ተርታም እራስህን አስቀምጥ፤ እራስህን መድብ።
ውብ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.4K viewsedited  05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 20:14:10 መነሻህ የት ነበር?
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
ወዶሃልና አዳነህ፤
አስቦሃልና አሳለፈህ፤
አዝኖልሃልና አበረታህ፤
ተረድቶሃልና አሳረፈህ፤
አውቆሃልና ሰጠህ፤
እንዳንተ ፍራቻ፣ እንዳንተ ስጋት ያጣሀው፣ የደረሰብህ ነገር የለም። የሰሪው መንፈስ ውስጥህ አለና የፈራሀውን አሳልፎሃል፤ ከሰጋሀው አሻግሮሃል፤ በለመለመው መስክ አሰማርቶሃል፤ ከምቹው ስፍራ አድርሶሃል። ሃሳብህን በእራሱ መንገድ፣ በፈቀደው ጎዳና ፈፅሞልሃል፤ እየፀመልህም ይገኛል። ትናንት እንደዛሬ አልነበረም፤ ዛሬም እንደትናንት አይደለም። የፈተነህ ዛሬ የለም፤ ያደከመህ፣ ያታገለህ፣ የተገዳደረህ ዛሬ ተፋቶሃል፣ ትቶሃል። ነገር ግን ትቶኛል፤ አልፌዋለሁ ብለህ እንዳትረሳው። የዛሬን ብቻ ሳይሆን የትናንት ትዝታዎችህንም አስታውስ።

አዎ! ጀግናዬ..! መነሻህ የት ነበር? ኬት እዚ መጣህ? እንዴት እዚህ ደረስክ? ማን ለዚህ አበቃህ፣ ማን ደገፈህ፣ ማንስ አገዘህ? ምላሽ ላለህ ጥያቄ አትሸበር። ያለፈው ታሪክህ ላያምር ይችላል፤ የምትናገረውና በሰው ፊት የማያኮራህ ይሆናል በምትኩ የምታዝንበት፣ የሚያሳቅቅህ፣ የሚያሸማቅቅህ ታሪክም ይሆናል። ነገር ግን ማለፍ ስለነበረበት አለፏል፤ መተው ስለነበረበት ተትቷል፤ መቅረት ስለነበረበት ቀርቷል። የሁሉንም ነገር አላፊነት አይተህበታል።
በሁለት እግርህ መቆም ተስኖህ የነበረ ጊዜ ይኖር ይሆናል፣ ዛሬ ግን ከእራስህ አልፈህ ለሌሎች ምርጉዝና ድጋፍ ለመሆን በቅተሃል።

አዎ! ጀርባህን አትዘንጋ፤ ኋላህን አትርሳ። ከማንነትህ ጀርባ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ብዙዎች ሰርተውሃል፤ ከኋላህ ደጉ ፈጣሪህ አብሮህ ነበር፤ ሰሪህ ሲያግዝህ ነበር። ዛሬም ሰዎች ከጎንህ አሉ፤ በውስጥህ የአምላክ መንፈስ አለ። ሁሌም ብቻህን አይደለህም፤ ሁሉም ማለፉን አስታውስ፤ ሁሉም መረሳቱን፣ መዘንጋቱን ተረዳ። ዛሬ የሆነው ሁሉ አላፊ ነው፤ እንኳን ዛሬ ነገም ደርሶ ያልፋል፤ በሌላ ቀን፣ በሌላ ተግባር ይተካል። ሲያልፍ እንዲሁ እንደዋዛ እንዲያልፍ አተሰፍቀድ፤ ነገህን አስተካክሎ፣ አንተን አንፆ፣ አጎልብቶ ይለፍ። ባሰብከው መንገድ ይስራህ፣ ባለምከው አኳሃንም ያኑርህ፣ ያብቃህ፣ ያሳድግህ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.7K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:08:07 የስህተት ድግግሞሽ ውሳኔ ነው!
፨፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨፨
አንድ ሁለቴ ተመሳሳይ ስህተት ልትሳሳት ትችላለህ፣ አንድ ሁለቴ አንዳይነት ጥፋት ታጠፋ ይሆናል፣ ሁለተኛ እድል ለመስጠት በተመሳሳይ ሁኔታ አንድን ሰው ልታምን ትችላለህ፣ አንድ ሁለቴ በአንዳይነት ጉዳት ልትጎዳ ትችላለህ። ነገር ግን ከአንዴ ወይም ከሁለቴ በላይ አንዳይነት ስህተት ከፈፀምክ፣ ተመሳሳይ ጥፋት ካጠፋህ፣ ደጋግመህ አንድን ሰው ካመንክ እርሱ ስህተት ወይም ጥፋት ሳይሆን ውሳኔ ነው። ወደህ ፈቅደህ የምትሳሳተው ስህተት፣ አውቀህ የምታጠፋው ጥፋት።

አዎ! ጀግናዬ..! የስህተት ድግግሞሽ ውሳኔ ነው፤ የጥፋት ተመሳሳይነት ታምኖበት የሚፈፀም ነው። እራስህን አትሸውድ ሳታስበው አንዴ ትሳሳት ይሆናል፣ ሳታስተውል ሁለቴ ታጠፋ ይሆናል ከዛ በላይ ግን በፍፁም ሳታስበው፣ ሳታውቀው፣ ሳታስተውል የምትፈፅመው ተመሳሳይ ስህተት አይኖርም። ሃላፊነቱን ሽሺት፣ ከተጠያቂነት እራስህን ለማግለል አንዳልታሰበ ስህተትና እንዳልታቀድ ጥፋት ልትፈርጀው ብትሞክርም፣ እውነታው ግን ወደህ፣ ፈቅደህ፣ አሰበህበት የፈፀምከው ተግባር መሆኑ ነው።

አዎ! ስህተትን ላለመድገም፣ ከእርሱም ለመማር አንዴ መሳሳት በቂ ነው። ተመሳሳይ ስህተት ደጋግመህ ስለተሳሳት በእራስህ ከማዘን ውጪ የተለየ ነገር አታገኝም። የማይመጥንህ፣ የማይጠቅምህ፣ የሚይጎዳህ ስፍራ ወስነህ እንጂ ተሳስተህ ደጋግመህ አትገኝም። ስህተትና ውሳኔ ለየቅል ናቸው። ስህተት ሳይታወቅ፣ ሳይስተዋል፣ ግንዛቤው ሳይኖር፣ የሚያመጣው ጥፋት ሳይታወቅ ይፈፀማል፤ ውሳኔ ግን የተጠና ተግባር ነው፤ የሚያስከትለው ጥፋት፣ የሚያስገኘው ጥቅም፣ የሚያሳጣው ነገርም እንዲሁ በጥልቀት ይታወቃል።
አዎ! ስህተት በእውቀትና በአስተውሎት አይፈፀምምና ከስህተት ለዘለለው የተደጋጋመ የውሳኔ ተግባርህ ሃላፊነት ውሰድ፤ ጉዳቱን እያወክ ደጋግመህ ላጠፋሃቸው ጥፋቶችህ እራስህን ተጠያቂ አድርግ። ለብልህ አንድ ስህተት የህይወት ዘመን ትምህርቱ ነውና ከእያንዳንዱ ስህተትህ ተማር፤ ደግምም ላለመሳሳት በአስተውሎት ተራመድ።
ውብ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.7K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:14:45 ያ ጊዜ ይመጣል!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
በክፉ የፈረጁህ፣ የተቹህ፣ ያንቋሸሹህ ሰዎች ለምን ይህን እንዳደረጉ እራሳቸውን የሚጠይቁበት፣ የሚቆጩበት ጊዜ ይመጣል። ያ ጊዜ አንተ በእራስህ የምትኮራበት፣ የምትደነቅበት፣ የምትደመምበት ጊዜ ነው። ካላጠፋህ የምትቆጭበት፣ መልካም አድርገህ የምትፀፀትበት ምክንያት የለም። እውነተኛውን ስሜትህን የማስተጋባት ሙሉ መብት አለህ። ያመንክበትን ሃሳብ የመፈፀም፤ በተመቸህና በመረጥከው፣ በሚያስደስትህ መንገድ የመጓዝ ነፃነት አለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ያ ጊዜ ይመጣል! ስላልተረዱህ የሚፀፀቱበት፣ ስላስከፉህ የሚያዝኑበት፣ ስላላበረቱህ፣ ስላልደገፉህ የሚቆጩበት ጊዜ ይመጣል። ሰው የሚያዝንብህ የእውነት የሚያሳዝንና የሚያስከፋ ተግባር ስለፈፀምክ አይደለም፤ የሚያማህ፣ የሚተችህ ኣልባሌና አላስፈላጊ ተግባር ስለፈፀምክ ብቻ አይደለም። አይቶ ስላልተመቸህ ብቻ ሊፀየፍህ፣ ሊጠላህ ይችላል፤ ምንም ሳያይብህ ስራህን ሳያውቅ፤ ማንነተህን ሳይለይ በደፈናውና በጭፍኑ ሊርቅህና ሊያንቋሽሽህ ይችላል።

አንዳንዴ ለትቺት ፍላጎት እንጂ ምክንያት አያስፈልግም፤ የጥላቻ ስሜት እንጂ ተጨባጭ አመክንዮ አይጠበቅም። ለመወደድ ሰርተህ ጥላቻን የምታተርፍበት፣ ለመሞገስ አድርገህ ነቀፌታን የምታገኝበት ጊዜ አለ። ደጋፊ ስትፈልግ ተቺ፣ እገዛን ስትመኝ ግፊት የሚገጥምህ ጊዜ ይኖራል። በዚህ ሰዓት ነፃ የሚያወጣህ ፈራጁ ላይ መፍረድ፣ ተቺውን ዳግም መተቸት ሳይሆን ፈራጁን እንደ ፈራጅነቱ፣ ተቺውንም እንደ ተቺነቱ ትተህ መንገድህን መቀጠል ነው። ሳያስተውል የተናገረህ ሁሉ ስራህን ሲያይ ይቆጭበታል፤ ሳያገባው፣ ሳይገባው የዘባረቀ ሁሉ ሲገባው በእራሱ ያዝናልና በፍፁም ከትክክለኛው ጎዳናህ ዘንበል አትበል፤ ስሜት የሚሰጥህን ከማድረግ አትቦዝን። ሰሚ ያጣ ትቺት የምትሰማ፣ ምክንያት አልባ ዘለፋ የምትሰማ አይደለህምና።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.6K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ