Get Mystery Box with random crypto!

የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ! ፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨ የሰዎችን ህይወት ማድመቅ፣ ማድነ | Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ!
፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨
የሰዎችን ህይወት ማድመቅ፣ ማድነቅ ክፋት የለውም፤ የእራስን መርሳት ማደብዘዝ ግን ትልቅ ክፍተትን ከብዙ ችግር ጋር ይፈጥራል። የየለት አጀንዳህ የሰዎች ህይወትና አኗኗር ከሆነ ለእራስህ ጊዜ ሊኖርህ አይችልም። የእነርሱን ትንሽ አጀንዳ በማጉላት ከተጠመድክ ያንተው ትልቅና ወሳኝ አጀንዳ አስታዋሽ በማጣት ስር ሰዶ ውድቀትህን ሲያፈጥን ልትመለከት ትችላለህ።

አዎ! በቅድሚያ የእራስን ሸክም ማራገፍ ስልጣኔ ነው። ሁን ተብሎ የሚሰራን ድራማ የህይወት አጀንዳ ማድረግ ቅለትና ብክነት ነው። አለም አዳዲስ አጀንዳ አታጠም፤ አዳዲስ ወሬ አታጣም። ያንተ በእርሷ ጊዜያዊ ድራማ መታለል ዋጋ እንደሚያስከፍልህ፤ ዋጋ እንደሚያሳጣህ አስታውስ።
አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ! አለምን የማትሰማበት፣ ከጫጫታዋ ዞር የምትልበት፣ በማይረቡ አዳዲስ አጀንዳዎቿ የማትታለልበት፣ አኗኗሪ መሆንህ የሚያበቃበት፣ ነዋሪነትህ የሚጀምርበት ጊዜ አሁን ነው፤ ዛሬ ነው።

አዎ! ፈተና ከተባለ እራስን ከማስረሳት በላይ የሚፈትን ነገር አይኖርም። በየቀኑ የሚመጡ የአለም ክስተቶች ለእራሳችን ጊዜ እንዳይኖረን፣ በእነርሱ ጉዳይ መጠመድ፣ መብከንከን ዋነኛው ተግባራችን እንዲሆን እያደረጉን ነው። የሌላውን ስናደምቅ የእኛ ሲፈዝ፣ የሌላውን ስናሳምር የእኛ ሲበላሽብን መመልከት የየለት ተግባራችን ኋኗል። ህይወትህ ላይ ጠብታ ያክል ነገር የማይጨምር የአለም ጋጋታ ማብቂያው አሁን ነው። በጊዜያት ለማይቀረው ለእራስህ ጊዜ መስጠት ጀምር፤ አለምን ካንተ ቦሃላ ነችና ቀዳሚውን የህይወት አጀንዳህን እራስህ አድርግ።
ውብ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel