Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
ርዕሶች ከሰርጥ:
Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.55K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-05 03:57:03
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:-

እንኳን ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!

በዓሉ፦ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የደስታ ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እና የአንድነት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።

  (መልካም ትንሳኤ ፤ መልካም በዓል!)

@EthioHumanity
@EthioHumanity
5.8K views00:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 21:06:22 ብርጭቆህን ባዶ አድርግ!!

ቻይና ውስጥ አንድ በጣም ጠቢብ የዜን ፍልስፍና (Zen Philosophy) መምህር ነበር።  ሰዎች የእርሱን እርዳታ ለማግኘት እና ጥበብ ለመቅሰም  ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ይጓዙ ነበር።  

አንድ ቀን አንድ የተማረ (ምሁር) ምክር ለማግኘት መምህሩን ይጎበኛል።   ምሁሩም ስለ ዜን የህይወት ፍልስፍና ለመማር እንደመጣ ይናገራል።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ውይይቱ ተጀመረ። ምሁሩ አእምሮው ‘በሁሉን አውቃለሁ ባይነት’ የተሞላ እና በእራሱ አመለካከት፣ አስተሳሰብ  እና እውቀት ፍፁምነት  ያምን ነበርና በንግግራቸው ወቅት መምህሩ የሚናገረውን እና የሚያስተምረውን ከመስማት እና ትኩረት ከመስጠት ይልቅ የራሱን ታሪክ እና ስለ ምሁርነቱ በማውራት መምህሩን የመናገር እድል ይነሳዋል። 

መምህሩም በእርጋታ አንድ ላይ ሻይ እንዲጠጡ ሐሳብ ያቀርባል። ለእንግዳው (ምሁሩ) ባቀረበው ብርጭቆም ሻይ ይቀዳለታል።  ብርጭቆው ሞላ። 

ነገር ግን መምህሩ እየፈሰሰም ቢሆን ሻይውን መቅዳቱን አላቆመም። ጠረጴዛው ላይ እስኪፈስ ድረስ ሻይ እየቀዳለት ነበር።  ሻይው ወለሉ ላይ ብሎም በምሁሩ ጃኬት ላይም ይፈስ ነበር።   ምሁሩም በመገረም እየተመለከተው ‘’“ተው እንጅ!  ብርጭቆው እኮ ሞልቷል።  ማየት አትችልም እንዴ ” ይላል።

መምህሩ በፈገግታ “ብርጭቆህን ባዶ አድርግ! አንተም  ልክ እንደዚህ ብርጭቆ ሁሉ አእምሮህ ባረጁ ሃሳቦች እና እምነቶች የተሞላ ስለሆነ ከዚህ በላይ ምንም አዲስ እውቀትና ሃሳብ መቀበል አቁመሃል። ‘’ በማለት ተናግሮ ብርጭቆውን ባዶ አድርጎ እንዲመለስ መከረው።  .

እኛም በህይወታችን ውስጥ በየቀኑ ተመሳሳይ ታሪክ ይከሰታል። ሁሉንም የምናውቅ ይመስለናል እናም ‘በትህትና ማዳመጥ እንዲሁም ከሌሎች መማር አያስፈልገንም!’ ብለን አእምሮአችንን ሞልተን ባዶ ማድረግ አቅቶናል!!!

In Zen we don't Find the Answer , We loose the question" የምትል ግሩም አባባል አላቸው። ራስህን ባዶ አርገህ መማር ከፈለክ ዙሪያህ ሁሉ አስተማሪ ነው!  ሩቅ ሳትሄድ ከጎንህ ላለው ሰው ልብህን ክፈት፣ በመጠየቅ በመመለስ ሳይሆን በመረዳት እና በማስተዋል ነው አብርሆት የሚፈጠረው።

የሰው ልጅ የነብሱን መንፈሳዊ ጎዳና ትክክለኝነት ማወቅ የሚችለው መንገደኛው ራሱ ነው..ስለ ሕይወትህ ችግር ከገጠመህ ወይም ጥያቄ ከተፈጠረብህ ዙርያህን አጥና... ያለህበት ሁኔታ ከሕይወትህ ጋር ያለውን አንድምታ መርምር በተለይ ትንሽ ትልቅ ሳትል በአቅራብያህ ያሉ ሰዎችን ህይወት በመመልከት ላንተ ምን መልእክት እንዳለው በትጋት ተከታተል ምክንያቱም የተፈጥሮ መንፈሳዊ አንደበት ናቸውና..."

የተፈጥሮን መንፈሳዊ ቋንቋ ተማር ስትወድቅ ሆነ ስትነሳ ፍቺው ምን እንደሆነ ውስጥህን ጠይቅ  እውቀትን ሩቅ ፍልስፍና ወይም አንቃቂ ዲስኩሮች ውስጥ አትፈልግ፣ ከራስህ ጀምር ምክንያቱም የኩራዝ ብርሃንን ብታይ በደንብ የሚያበራው አቅራብያው ላለው ነው። አንተም ለራስህ ብርሀን ሁን መማር አታቁም፣ እድገትህን አትግታ፣ እራስህን አሻሽል፤  በአዳዲስ እውቀቶች እራስህን አንፅ!

ሁሌም ብርጭቆህን ባዶ አድርገህ ተነስ!

        ውብ ቅዳሜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
8.2K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 21:06:01
6.0K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 22:01:03
ቀላል የህይወት መንገድ  ምርጫህ ሆኖ ጠንካራ፣ ስኬታማና ምርጥ ህይወት የሚኖር ሰው አትጠብቅ።

በመከራዎቹ ሁሉ ተፈትኖ እንደወርቅ ቀልጦ የምርጥ ማንነት ባለቤት የሚሆነውን ፣ ጠንካራውን፣ አይበገሬውንና የህይወት መንገድ ነፃነቱን በስኬቱ የሚጎናፀፈውን አንተን ለመተዋወቅ ሁሌም ረጅሙና ፈታኙ መንገድ ምርጫህ ይሁን።

   በረጅም ድካም የማይገኝ ነገር የለምና

          ውብ የስኬት ጊዜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
7.9K viewsedited  19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 20:38:08 በአንድ ወቅት ጫካ ውስጥ መውለጃዋ የቀረበ አንዲት ሚዳቆ የመውለጃ ሰዐቷ ደርሶ ትግል ላይ ሳለች ድንገት አከባቢዋን ስትቃኝ ከፊት ለፊቷ ወንዝ ፣ ከኋላዋ ቀስት ያነጣጠረባትን አዳኝ፣ ወደ ጎን ስትዞር የተራበ አንበሳ አሰፍስፎባት ትመለከታለች።

ይህም ሳይበቃት ጭማሪ ከፍተኛ ነጎድጓድና መብረቅ ያጀበው ደመና መጥቶ ሰማዩን ያጨልመዋል። መብረቁም ሀይለኛ ስለነበር ደኑን ይመታውና ከፍተኛ ቃጠሎን ያስነሳባታል። ምን ታድርግ?

ወደ ፊት ሮጣ እንዳታመልጥ ጥልቅ ወንዝ ተደቀነባት፤ከኋላዋ አዳኙ፤ከጎኗ ደግሞ አንበሳው፤ወደ ጫካ ገብታ እንኳ እንዳትደበቅ ደኑ ከፍተኛ ቃጠሎ ላይ ነው...
በዚያ ላይ የውልደት ህመም ነፍስ ውጪ ግቢ እያስባላት ነው ...

ሚዳቆዋ በዚህ ውጥረት ውስጥ ሆና ትኩረቷን መፈፀም ወደ ምትችለው ነገር ላይ ብቻ በማድረግ ቀሪውን ለፈጣሪ በመተው በመወለድ ላይ ስላለው ልጇ ብቻ ማሰብ ጀመረች.....

አዳኙ ቀስቱን አነጣጥሮ ሊለቅ ባለበት ቅፅበት ድንገት የመብረቁ ብልጭታ አይኑ ላይ ብዥታ ፈጠረበትና ቀስቱ ተስፈንጥሮ ወደ ተራበው አንበሳ ይሄድና አንበሳውን ይገለዋል።

አጉበድብዶ የነበረው ደመናውም መዝነብ ይጀምርና የደኑን ቃጠሎ በቅፅበት አጠፋው። በጭንቅ ታጅባ የነበረችው ሚዳቆም በሰላም ተገላገለችና ወደ ቀደመው ህይወቷ ተመለሰች።

አንዳንዴ በህይወትህ ውስጥ በብዙ ፈተናዎችና ጭንቀቶች ልትከበብ ትችላለህ፣ ያኔ አንተ ልትፈታው በምትችለው ነገር ላይ ብቻ አትኩርና ቀሪውን ለመፍትሄዎች ሁሉ ባለቤት ለሆነው ለፈጣሪህ ተወው።

መውጫ መፍትሄ አንተጋ እንጂ ፈጣሪህ ዘንድ አይጠፋም። አስታውስ ሁሌም ትላልቅ ወይም ከባባድ ፈተናዎች አሉብኝ ብለህ ለፈተናዎች እውቅና ከመስጠትህ ይልቅ የከባባድ ፈተናዎች አለቃ የሆነው ፈጣሪ አለኝ እያልክ ጭንቀቶችህን አቅልላቸው፣ሁሌም በፈጣሪህ ፈፅሞ ተስፋ አትቁረጥ!!!

ገጣሚ በረከት በላይነህ ''ሳይፀልዩ ማደር'' በምትለው ውብ ግጥሙ እንለያይ፣

''ሳይፀልዩ ማደር''

የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋ ፀለየች....
"አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ
...
ነብሩም ተርቦ
ወደ አምላኩ ቀርቦ
ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ
ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ
...
የሁላችን ሰሪ
ፀሎታቸውንም ሰማቸው ፈጣሪ
አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋን አላት
"እሩጠሽ አምልጪ ከበረታው ጠላት"
...
ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት ምግብ አድርገህ ብላት"
ሚዳቆዋ ስትሮጥ
ከነብር ለማምለጥ
ነብሩም ሲከተላት
ሆዱን ሊሞላባት
.
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር
...
አውጣኝ ያለው ወቶ አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው ከርከሮ ተበላ

           ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
10.5K viewsedited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 20:37:58
7.1K views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 17:21:43
አንተ ከነሱ የተለየህ በመሆንህ ሲስቁብህ አንተ ደግሞ አንዳይነት በመሆናቸው ሳቅባቸው!

ንስር የጨለመውን ወጀብ ሰንጥቆ ያልፋል እንጅ ጨለማው እስኪያልፍ አይጠብቅምና ጀግናም ጥዋት በወጣበት ስታይል አይመለስም ለማለት ነው ።

አለም ለደፋሮች ታደላለች። ወደ ከፍ ያለ ማንነት ጉዞ ስትጀምር የነፍስክ ጥንካሬ ተአምራዊ ወደ ሆነ ቦታ ያደርሥሀል።

ሽብርቅርቅ ያለች ቅዳሜ ትሁንልን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
10.1K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 16:58:45

እንኳን ለ 1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
                
በመላው አለም የምትኖሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለ1445ኛው የዒድ  በአል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።

የዒድ በአል የእዝነት ÷ የመተሳሰብ ÷ አብሮ የመብላትና የመፈቃቀር በአል በመሆኑ በየ አካባቢያችን በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዋል።

          ዒድ ሙባረክ !!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
9.4K viewsedited  13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 20:35:27 ነፍሴ ስትመክረኝ …

የውስጥ ሰላም ከብር ፣ ከወርቅ ፣ ከአልማዝም ሆነ እንቁ ይልቃል ፤ ስኬታማነት ከውስጥ ሰላም ፣ ደስታና ፍቅር በጥብቅ የተቆራኘ ካልሆነ ትርጉሙ ጎዶሎ ነው። ወደ ሀቅ የምትጠራህ ነፍስህን በድለህ ሺህ ግዜ የምድር ሃብት ብትሰበስብ ሀብትም ሆነ ሌላ ነገርህ የውስጥ ሰላም እስካላስገኘልህ ድረስ ተሳካልህ ተብሎ አይታመንም ፤  በዚህ መልኩ የምታገኘው ነገር " ይዘህ ተገኘህ " እንጂ ተሳካልህ አያሰኝም።.

ሰላም የሚያሳጡ ፍጡራኖችን ያየህ እንደሆነ በሌሎች ሰዎች ዋጋና መስዋትነት ማትረፍ የለመዱ ፤ ከራሳቸው ጋር ሰላም መፍጠር ያልቻሉ ስግብግቦች እንደሆኑ  ለሰከንድ አትጠራጠር። ከእንደዚህ ዓይነት ስግብግብነት ተጠቆጠብ የሰላም እሴትህን ጠብቅ ፣ ይዘው የተገኙት እየቀደሙህ እየመሰለህ የመልካምነት ጉዞህ መሐል ላይ አትወዛገብ ከመልካምነት እና ከሀቅ በላይ አድካሚና አሸልቺ ግን ደግሞ ፍሬው ጣፋጭ የሆነ እፁብ ድንቅ መታደልና መባረክ የለም።

አንዳንድ ጊዜ በራስህ ዓለም ዉስጥ ብቻ ለመኖር ሞክር፡፡፡ ወደ ምድር የመጣኸው ትርጉም ላለው ዓላማ ነውና ሁሉም ቦታ ላይ ጥቀም፡፡ በደረስክበት ቦታ ሀሉ መልካም ዝራ፡፡

እቅድህን በመኖር ሂደት በሚገጥሙህ ፈተናዎች አታማር ከአሁን ቀደም የሆኑ ፣ እየሆኑ ያሉ ፣ ከአሁን በሁዋላ በፈለግከውም ሆነ ባልፈለግከው መንገድ የሚሆኑ ነገሮች ሁሉ በምክንያት ያጋጠሙህ እንደሆኑ እመን። የፈተና መብዛቱ ለበጎ ነው፡፡ አካሄድህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡ በችግሮች ዙሪያ ተጠበብ እንጂ አትጨነቅ ፤ ለመልካምነትና ከሀቅ ጋር ለመታረቅ የረፈደ የሚባል ግዜ የለም ፤ የቻልከዉን ያህል ስራና እረፍ ፤ ቀሪውን ለፈጠረህ ጌታ ተወው።

ሀቀኝነትን ድፈር ፤ ሀሜተኝነትንና ዋሾነትን ፍራ

ደፋር ይሰማል ፣ ያደምጣል ፣ ይናገራል ፣ ይመረምራል ፣ ይፅፋል ፣ ይወስናል ፤ የሰማውን ሁሉ እንደ ሰነፎችና ፈሪዎች እውነት ብሎ አያምንምም አይፈርጅምም ፤ የሰማኸውን ሁሉ እንደ እውነት አምነህ ደግመህ ደጋግመህ ሳታረጋግጥ አታውራ ፤ ማጣራትን አስቀድም ፤ ሳትጠይቅ እና ሳታመዛዝን አትፍረድ።

ስምህን ከምታውቀው በላይ እርግጠኛ ሁን

እንዲህ ስታደርግ ሁሉም የሚታየው ጭለማ ፣ የሚያወራው ስለጭለማ ቢሆን ላንተ የሚታይህ ብርሃን እንጂ ሌላ አይሆንም። አትጠራጠር ንስር አሞራ ፈተናዎቿን ከደመናው በላይ ከፍ በማለት እንደምትሻገረው አንተም ፈተናዎችን ከችግሮች በላይ ከፍ ብለህ በማለፍ የውስጥ ሰላምህን ቀጣይነት እያረጋገጥክ ማሳካት ወደ ምትፈልገው ግብ የማትደርስበት ቅንጣት ታክል ምክንያት አይኖርም።

እናም እየነዳን ወዳጆቼ

ሁሉንም ነገር በንቃት እየታዘብን እስከነዳን ድረስ  ፤ በችግር ውስጥ ሆኖ በመሳቅ ፣ በደስታ እና በውስጥ ሰላማችን እስካልተደራደርን ድረስ የማንሻገረው ፈተናና የማናሳካው  ግብ አይኖርም።

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
12.2K viewsedited  17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 20:34:07
9.0K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ