Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-13 07:13:46 ቁጪትህን ቀንስ!
፨፨፨////////፨፨፨
ህይወትህን ወደኋላ ተመልከት፤ ዳግም መፈጠር ቢቻል ዳግም በአሁኑ ማንነት የመፈጠር፣ እንደገና በመጣህበት መንገድ መምጣት፣ ሁለተኛ እዚው አሁን ያለህበት ስፍራ የመገኘት ድፍረቱ አለህን? ወይስ ዳግም በመፈጠር ውስጥ ሌላ ሰው ሆነህ፣ በሌላ መንገድ አልፈህ፣ ሌላ የተለየ ማንነትን ይዘህ መፈጠርን ትፈልጋለህ? ብዙ እራስህን እንድትወድ ወይም እንድትጠላ፤ በመጣህበት መንገድ እንድትኮራ ወይም እንድታፍር፤ በማንነትህ እንድትደሰት ወይም እንድታዝን የሚያደርጉህ ነገሮች ይኖራሉ። ያለህበትን ቦታና ማንነትህን አትወደውም ማለት ህይወትህ በቁጪት ተሞልቷል ማለት ነው፤ ውስጥህ በአሉታዊት እየተቦረቦረ ነው ማለት ነው፤ እያደር አቅም እያነሰህ፣ ወኔ እያጠረህ ነው ማለት ነው። በዚህ መንገድ ሳታውቀው እራስህን ትጎዳለህ፤ ከማትወደው ደረጃ ወዳነሰ ስፍራ በፍጥነት ትንደረደራለህ፤ መቀየር በማትችለው ታሪክህ ምክንያት አብዝተህ ትብሰለሰላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ቁጪትህን ቀንስ፤ ታሪክህን ቀይር፤ አዲስ ማንነትን ፍጠር፤ የሚያኮራህን ስብዕና ገንባ። የአሁኑን ማንነትህን ካልወደድከው ልታደርግ የምትችለው ብቸኛ ነገር እለት እለት በእርሱ መበሳጨት አይደለም፤ በየቀኑ በእርሱ ማዘን አይደለም፤ ለሰዎች ማሳየትና ማስገምገም አይደለም፤ አንድና አንድ መቀየር ነው፤ ማደስ ነው። ካልፈለከውና ስሜት ካልሰጠህ፣ ካላደክበት፣ ሁሉ ነገሩ ካልተመቸህ ስለምን ተሸክመሀው ትዞራለህ? የማትወደው ልማድ ካለብህ ቀይረው፤ Just Change it. የሚያሳፍርህ አቋም ካለህ ስራበትና ለውጠው፤ የሚያስቆጭህ ታሪክ ካለ አዲስ የሚያኮራህን ታሪክ መስራት ጀምር። ለምንም ነገር ጊዜው አሁን ነው። መቁረጥ ያለብህ ግንኙነት ካለ በሚገባ ተረጋግተህ አስበህበት ቁረጠው። የትኛውም ቁስል ካልዳነ አካልህን እየጎዳና እያመናመነው ይመጣል። የሚያስቆጭህና ማንነትህን እንድትጠላ የሚያደርግህ ነገርም ካለ በጊዜ ካልተወገደና ካልተቀረፈ ከአጭሯና ውዷ እድሜህ ላይ አስደሳቿን ጊዜ እየቀነሰ ይሔዳል።

አዎ! ቀላል ስራ አይደለም፤ በትንሽ ጊዜ የሚፈፀም ነገር አይደለም፤ ስለፈለክ ብቻ የምታደርገውም አይደለም። ከፍላጎት በላይ ህመመህን በቃሀኝ ልትለው ይገባል፤ ከሃፍረትና መሸማቀቅ በላይ ዘወትር በአንድ ጉዳይ መጨነቅንና መብሰልሰለን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልታስወግደው ይገባል። ዙሪያህን በአፅንዖት ተመልከት ተመችቶሃል አልተመቸህም? እያሳደገህ ነው ወይስ እያሳነሰህ? እየቀየረህ ነው ወይስ ወደ ባሰ አዘቅት እየከተተህ? በእራስህ ሚዛን የሚበጅህን የለውጥና የእድገት ውሳኔ ወስን። ነገሮችን በማወሳሰብ ይበልጥ አታክብዳቸው። ካሳመመህ፣ ካስጨነቀህ፣ እረፍት ከነሳህ፣ ሰላምህን ካሳጣህ ተላምደሀውና ተስማምተሀው ብትኖር እንኳን አንድ ቀን ዳግም በቁጪት መልክ መገለጡ አይቀርምና ከአሁኑ በትንሹ እርምጃ ውሰድበት፣ በሂደትም አዲሱን ተወዳጅ ማንነትን ገንባበት።
ግሩም ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
596 views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 20:41:46 ሁለት ሰዓት ይበቃሃል!
፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨
ብዙ ሰዓት መስራት አይጠበቅብህም፤ ረጅሙን ጊዜህን እርሱ ላይ ማጥፋት አይኖርብህም። በቀን ስምንት የስራ ሰዓት አለህ፣ ሌላው ስምንት ሰዓት የእንቅልፍ ነው፤ ቀሪው ስድስት ሰዓት ለምግብ፣ ለመጠጥና ለመዝናናት ሊውል ይችላል ሁለቱ ቀሪ ሰዓት ግን ህልምህን የምትኖርበት ነው፤ ራዕይህን አቅጣጫ የምታሲዝበት ነው፤ የህይወት ትርጉምህን የምታገኝበት ነው። ህይወት ከፈተናዋና ከችግሯ ብዛት ህልምን ለመኖር ጊዜ ላትሰጥህ ትችላለች፤ በፈለከው መንገድ እንድትኖራት ላትፈቅድልህ ትችላለች። የሆነ ሰዓት የገባህበት ስራ መፈናፈኛ ያሳጣሃል፤ ሳታስበው የጀመርከው ትምህርት እረፍት ይነሳሃል፤ በአጋጣሚ የተዋወከው ጓደኛህ አጉል ልማድ ውስጥ ይከትሃል። ህልምህ ግን ሳይታሰብ የሚደረግ፣ ያለእቅድ የምትከውነው፣ በአጋጣሚ የሚሆን ነገር አይደለም። ከዘፈቀደው አኳሃን በተለየ በሚያስበው የአዕምሮ ክፍል ተመዝኖ ቦታና ጊዜ የሚመደብለት ብርቱ ጉዳይ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁለት ሰዓት (2:00) ይበቃሃል፤ ህልሜ የምትለውን ነገር ለማሳካት፣ ህይወትህን አቅጣጫ ለማስያዝ፣ ደስተኛና የተረጋጋ ህይወት ለመኖር ገንዘብ አያስፈልግህም፤ የሰው እርዳታ አያስፈልግህም፤ የመንግስት ድጎማ አስፈልግህም። አንድ በዋናነት ሊያስፈልግህ የሚችለው ነገር ካለህ ሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ሁለቱን ሰዓት ብቻ ለህልምህ መስጠት ነው። ምናልባት ከህልምህ ጋር የሚገናኙ መፅሃፍትን ማንበብ ሊሆን ይችላል፤ ምናልባት በራዕይህ ዘርፍ ሰዎችን ማገልገል ይሆናል፤ ምናልባት ከህልምህ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ሁን ብሎ ማግኘትም ሊሆን ይችላል። ስለ ህልምህ ስታወራ እህ.. ብሎ የሚሰማህን ሰው ከገኘህ እራሱ እርሱ በጣም ትልቅ ነገር ነው። ከሰማህ ቦሃላ ማረጋገጫ ባይሰጥህ እንኳን ህልምህን በቃላት ሰድረህ መግለፅ መቻልህ በእራሱ ግልፅነቱን እንድትረዳው ያደርግሃል።

አዎ! ወጥነት ያላቸው፣ በየቀኑ የማይቋረጡ የሁለት ሰዓት ድርጊቶች አሁን ሙሉ ህይወትህን እንድትመራበት ካስቻለህ የስምንት ሰዓት ስራ ነፃ እንደሚያወጣህ አትጠራጠር። የምትኖረው ህይወት ነው። መኖር ውስጥም ጠዓም አለ። ጠዓሙም የሚጎላው በምትወደውና በምትፈልገው ነገር ውስጥ ነው። የምትወደው ነገር ደግሞ ሙሉ በሙሉ ህልምህ ውስጥ አለ፤ ራዕይህ ውስጥ አለ፤ አላማህ ውስጥ አለ። ህልምህን መኖር ለመጀመር አሁን ከምትማረው ትምህርት ጋር መጋጨት አያስፈልግህም፤ ስራህን ማቆም አይጠበቅብህም፤ ሰዎች እንዲያምኑብህ መጣር አይጠበቅብህም፤ እርዳታ ከየአቅጣጫው መጉረፍ አይኖርበትም። ህልሜ ለምትለው ነገር ተገቢውን ጊዜ ስጠው፤ በየቀኑ ሁለት ሰዓት ብቻ ስራበት፣ በእርሱ ዙሪያ ግንኙነትህን አስፋ፤ እንደ ትግል ሳይሆን እንደ አስደሳች ሁነት ተመልከተው፤ በውስጡ እራስህን አድስ። በስተመጨረሻም ከምታስበው በላይ ዋጋህን እንደሚከፍልህ እመን።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
1.8K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 13:35:56
ልዩ Online ስልጠና ለተማሪዎችና ለትምህርት ፈላጊዎች
በMental Counsel ETH: ምክረ-አዕምሮ


በእርግጥ ትምህርት መማር እንደሚባለው ጊዜ ማባከን ወይም Scam ነውን?
ለምንድነው የምንማረው?
ትምህርታችንንስ እንዴት ለህይወት አላማችን በመጠቀም ትርጉም ያለው ነገር እናደርግበታለን?
የመማራችን ዋናው ጭብጡና ግቡ ምንድነው?

በነዚህና ከነዚህ ጋር በተያያዙ ትምህርት ተኮር፣ እንዲሁም ፈተና ተኮር ጉዳዮች ላይ በሰፊው እንወያያለን። ብዠታዎችንም እናጠራለን።
ተማሪዎች እንዲሁም ለመማር ሃሳብ ያላችሁ ቤተሰቦች እንዳያመልጣችሁ።
አስቀድመው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተቀመጠውን አድራሻ ይጠቀሙ!
@merryyeab
+251963831491
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.2K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 07:45:37 አትመካ!
፨፨//፨፨
እየተከታተለ ድክመትህን ከሚነግርህና ደካማ ጎንህን፣ ማሻሻል የሚገባህን፣ መጨመር ያለብህን ነገር ከሚነግርህ የትኛውን ትመርጣለህ? በእርግጥ ከስርስርህ ትንሿን ተግባርህን እያገነነ መሬት እንዳይበቃህ የሚያደርግህን፣ ከተግባርህ በላይ የገዢነት ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርግህን፣ አንዳንዴም ከሆንከው በላይ ሊያሞግስህ የሚጥርን ሰው ከወረጥክ የትምክህተኝነት መንገድ ላይ እንደሆንክ አስተውል። ትምክህት እንድትታበይ፣ በሰራሀው ትንሽ ስራ እንድትመፃደቅና እጅግ የተጋነነ ስፍራን ለእራስህ እንድትሰጥ ያደርግሃል። ከሰዎች በሚዘንብልህ ተከታታይ የአድናቆት ቃል ብትመካና ብትታበይ ከማንም በላይ ውድቀትህን የምታፈጥነው አንተ ነህ። አንዳንዴ የሚገነቡህ አስተያየቶች አሉታዊ ተብለው የሚፈረጁ አስተያየቶች ናቸው። አንተ አዎንታዊ ከሆንክ አሉታዊ ሃሳብና አስተያየቶችን በአዎንታዊነት በመመልከት ለተሻለው ጥንካሬና ብርታት ልትጠቀማቸው ትችላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! አትመካ! ባለህ ነገር አትመካ፤ በተሰጠህ መክሊት አትታበይ፤ በደረስክበት ደረጃ አትዘናጋ። ህይወት የት እንደምታደርስህ አታውቅም። ትምክህት አንድም ለውድቀት ሌላም ለመታለል ይዳርግሃል። ምናልባት እንደምትባለው አይነት ሰው ላትሆን ትችላለህ፤ ምናልባት የተሰጠህ ስም የሚገልፅህ ላይሆን ይችላል። ባልሆንከው መመካት ሸክም እንጂ ፀጋ አይደለም። በማይገልፅህ ማንነት መኩራራት የእራስን ክብር አለማወቅ እንጂ ምንም አይደለም። የማይታይህን ድክመትህን ወዳጆችህ አይተው ቢነግሩህ ምንም ክፋት የለውም፤ ክፍተትህን አሉታዊ ከተባሉ አስተያየቶች በመነሳት ብትሞላቸው ብታተርፍ እንጂ አትጎዳም። የክፉ ቀን ወዳጅ አለ፤ ውድቀትህን አይፈልግምና ለጊዜው ቢያናድድህም የሚጠቅምህን አስተያየት ከመስጠት ወደኋላ አይልም፤ ለጊዜው ቅራኔ ቢፈጥርብህም ከጊዜያዊው ቅራኔ በላይ የሚታየው ያንተ በአስተያየቱ መታነፅና መቀየር ነው።

አዎ! ምድራዊ ነገር በሙሉ ጊዜያዊ ነው። መቼ እንደሚጠፋ አይታወቅም፤ ነገሮች መቼ እንደሚቀየሩና እንዳልነበሩ እንደሚሆኑ አይታወቅም። በሚያልፍ ነገር ብትመካ ትምክህትህም አብሮት ያልፋል፤ ባልሆንከው ማንነት ብትመፃደቅ ካለህበት ስፍራ አትንቀሳቀስም። ለውጥን ከፈለክ ባለህ ነገር አትመካ፤ እንደገትን ከተመኘህ በሰዎች ሸንጋይ ቃላት አትታበይ፤ በሚነገርህ ጊዜያዊ ማሞካሻዎች አትመፃደቅ፤ አትዘናጋ። ማደግ ለሚፈልግ፣ ለሚሰራ ሰው ከከንቱ ውዳሴ ይልቅ ቁንጥጫና ደካማ ጎኑን የሚገልፁ አስተያየቶች ይጠቅሙታል። ከአምላክህ በቀር በእራስህም አትመካ። መመካት ስትጀምር እራስህን ታካብዳለህ፤ ካንተ በላይ ሰው ያለ አይመስልህም፤ ማንም አንተን የሚፎካከር እንደሌለ ታስባለህ፤ ምንም ሳታደርግ ትልቅ ነገር እንዳደረክ እራስህን ትመለከታለህ። አትመካ፤ በገዛ መሰናክልህ እራስህን አትጣል።
ድንቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.4K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 20:40:42 አትናቅ!
፨፨//፨፨
የሰው ልጅ ደክሞ የሚያጣውን ትንሽዬ ገንዘብ አትናቅ፤ የሰው ልጅ ህይወትን ለማሸነፍ ዝቅ ብሎ የሚሰራውን ስራ አትናቅ፤ የሰው ልጅ ብዙ ዋጋ ከፍሎ የደረሰበትን ደረጃ አትናቅ፤ የሰው ልጅ የሰው ፊት እየገረፈው፣ ብዙ እየተባለ የገነባውን ቤት አትናቅ። ምንም ቢሆን መናቅና ማንቋሸሽ የመጨረሻ ምርጫህ ሊሆን አይገባም። ሰዎች ነን በሰውነታችን ብቻ ሁላችንም ክብር ይገባናል። የምንናገረው፣ የምናደርገው ነገር፣ የምናጠፋው ጥፋት ከሰውነታችን ቦሃላ የሚመጣ ነገር ነው። ማንንም ወድቆ ብታየው በመውደቁ ልትንቀውና ክብርን ልትነፍገው ትችላለህ፤ ነገር ግን ነገ የት መድረስ እንደሚችል አታውቅም። ሰውን በሰውነቱ ከመለካት ይልቅ ባለው ነገር፣ ባለበት ሁኔታ፣ በገጠመው ችግር፣ በደረሰበት ነገር ለመለካት እንቸኩላለን። ሰምተህ እንዳልሰማህ ማለፍ የሚገባህ ነገር ይኖራል፣ ሰው ግን በጊዜያዊ ማንነቱና ባጣው ነገር ምክንያት ሊናቅና ሊንቋሸሽ የሚችል ፍጡር አይደለም።

አዎ! ጀግናዬ..! አትናቅ! ያጣ፣ የገረጣ፣ ከፈጣሪና ከእራሱ በላይ ምንም የሌለው ሰው ብታገኝ ከመናቅ በላይ ሃዘኔታን አስቀድም፤ በመልካምነት እጅህን ዘርጋለት። ማንም ሰው ሸክም አለበትና በሸክሙ ላይ በንቀት ውስጡን አትጉዳው። ነገሮች በምክንያት ይሆናሉ፤ ሰውን እየናቅክ ክብርን ልታገኝ አትችልም፤ ሰውን እያንቋሸሽክ በሰው ዘንድ ቦታ ሊኖርህ አይችልም። የሰጠሀው መመለሱ ሳይታለም የተፈታ ነገር ነው። ንቀት መናቅን ይወልዳል፤ ማንቋሸሽ መንቋሸሽን ያመጣል፤ መጠየፍ መገለልን ያስከትላል። ባናደርገው እንኳን ውስጣችን ያለው መጥፎ ስሜት በብዙ መልኩ ይገለጣል። አንደኛውም መገለጫ ንቀት ነው፤ ለሰዎች ክብር አለመስጠት ነው። የሰዎች ታሪክ ይቀየራል። እድሜ ልክህን አለቃ ሆነህ አትኖርም፤ እድሜህን ሁሉ መሪ ሆነህ አትቀጥልም። አንድ ቀን ከአለቅነትህ ትወርዳለህ፣ የመሪነት ስፍራህን ትለቃለህ። በተራህ አለቃ ይሾምብሃል፤ በሌላ መሪም ትመራለህ።

አዎ! በሔድክበት ሁሉ ለሰው ልጅ ክብር ይኑርህ፤ አዛኝ ልብ ይኑርህ። ውስጥህን በሚገባ አፅዳው። ውስጥህ የሚመላለሰው ሃሳብ ሁሌም ይከተልሃል። አሉታዊ አስተሳሰብ በውስጥህ ቢመላለስ ውጪም የምታገኘው የዚህኑ አስተሳሰብ ነፀብራቅ ነው። አምላክ ሰውን የሚደግፈው እራሱ ከሰማይ ወርዶ አይደለም። ይህን ሊያደርግ የሚችለውም በሰው በኩል ባንተ ነው። ሰውን ብትንቅ የምትንቀው እራስህን እንደሆነ እወቅ። አጎንብሶ የሚያገለግልህ ሰው አንድ ቀን ቀና ይላል፤ አንተ ካለህበት ስፍራም ከፍ ይላል። በደና ጊዜ ብታከብረውም ያከብርሃል፤ በደጉ ወቅት ጊዜ ብትሰጠውም ሳይሰስት ጊዜ ይሰጥሃል። የሰጠሀው መመለሱ ላይቀር እንዲደረግብህ የማትፈልገውን ነገር በማንም ላይ አታድርግ፤ በብዙ እጥፍ ማግኘት የምትፈልገውንም ለሰው ስጥ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.7K viewsedited  17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 18:31:15 Watch "ለ15 ደቂቃ ብቻ በማዳመጥ ህይወቶን ያድሱ! Revive your life by listening for just 15 minutes! inspire ethiopia" on YouTube


2.5K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 07:15:52 ውሃ አጠጣው!
፨፨፨///////፨፨፨
እንዲያድግ የምትፈልገውን፣ አድጎም ጥላ እንዲሆንህ፣ ለማረፊያነትና ለመዝናኛነት እንዲያገለግልህ የምትፈልገው ተክል ካለ በየጊዜው ውሃ አጠጣው፤ መግበው፤ ተንከባከበው። እርሱን ሳይሆን ከእርሱ የምታገኘውን ጥቅም ብቻ መፈለግህ የምትፈልገውን ነገር በበቂ ሁኔታ ላያስገኝልህ እንደሚችል እወቅ። ያስደስተኛል፤ ስሜት ይሰጠኛል፤ ወደፊትም ያሳርፈኛል ብለህ የምታስበው ሙያ ካለህ፣ ክህሎት ካለህ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም በፍጥነት ስራበት፤ በሚገባ እወቀው፤ አሳድገው፤ አንተም እደግበት። እያሳመመህም ቢሆን ከፈለከው ዋጋ መክፈል ይኖርብሃል። ክህሎቱን ያወቀ፣ እርሱም ላይ የሰራ፣ እለት እለት 1% እላዩ ላይ እየጨመረ የሚጓዝ ሰው የጊዜ ጉዳይ እንጂ እስካላቆመ ድረስ እንደሚያልፍለት ምንም ጥርጥር የለውም።

አዎ! ጀግናዬ..! እችለዋለሁ፤ ይሳካልኛል፤ ያሳልፍልኛል ብለህ የምታስብ ከሆነ በየሰዓቱ ውሃ አጠጣው! ተንከባከበው፤ ጠንክረህ ስራበት። መማር እስካለብህ ጠንክረህ ተማር፣ መስራት እስካለብህ ጠንክረህ ስራበት። እራስ ላይ መስራት፣ ክህሎትን ማዳበር፣ በየቀኑ አንድን ነገር እየደጋገሙ መገኘት፣ ለረጅም ጊዜ ውጤት የማያሳይ ነገር ላይ ረጅም ጊዜ ማሳለፈ እጅግ ከባድና አሰልቺ መሆኑ አይቀርም። ነገር ግን ይህ የሚሆነው ተግባሩን ካልወደድከው፣ ክህሎትህ እንደሆነ ካልተቀበልክና በሂደቱ ደስተኛ ካልሆንክ ብቻ ነው። በዚም ሆነ በዛ ጊዜ ማለፉ ላይቀር አንተም ሳትሰራበት፣ እራስህን ፈልገህ ሳታገኝ፣ እራስህ ላይ ሳትሰራ እንዲያልፍ አትፍቀድ። ለእራስህ ጉዳይ እራስህ ሃላፊነት ትወስዳለህ፤ የእራስህን ተግባር እራስህ ትከውናለህ፤ እየቻልከው ስለምን ሌሎች በማድረጋቸው ቀናተኛ ትሆናለህ? እየቻልክ ስለምን እንደማይችል ትኖራለህ?

አዎ! ቆመህ የምታይበት፣ በአላፊ አግዳሚው የምትደነቅበት፣ በምኞት አለም የምትዋትትበት ጊዜ አብቅቷል። ከጆሮህ አልፈው ወደ አዕምሮህ የሚገቡትን፣ ከአዕምሮህ አልፈው ደምስርህን የሚቆጣጠሩ፣ ማንነትህን የሚገሩ፣ ስብዕናህን የሚቀይሩ ንግግሮች ላይ ጥንቃቄ አድርግ። ማደግ የሚፈልግ ሰው ስሩን በሚያደርቁ፣ ውሃ በሚከለክሉት፣ ከአዎንታዊነት በሚነጥሉት ነገሮች እራሱን አያጥርም። እራስህ ላይ የምትሰራው በመጀመሪያ ለእድገትህ ከማይጠቅሙህ ሰዎችም ሆነ ሌሎች ነገሮች በመራቅ ነው። ከዛም ያለማንም ከልክይና አሰናካይ እለት እለት እራስህን መመልከት ትጀምራለህ፤ እራስህን ትንከባከባለህ፤ እራስህን ታስተምራለህ፤ ታሰለጥናለህ። የሚባለው ላይ ሳይሆን በእርግጥም የሚጠቅምህ ላይ ታተኩራለህ። ያለማቋረጥ ውሃ ያጠጣሀው፣ የተንከባከብከው ማንነትህም በጊዜው ፍሬ አፍርቶ፣ ለብዙዎች ተርፎ፣ ሌሎችንም አስጠልሎ ትመለከተዋለህ።
ድንቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.1K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:54:05 አውጥተው ይጥሉሃል!
፨፨፨፨///////////፨፨፨፨
ምንም ያክል የዋህ ልትሆን ትችላለህ፣ ምንም ያክል የፍቅር ልብ ሊኖርህ ይችላል፣ ምንም ያክል ልትታመን፣ ቃልህን ልትጠብቅ፣ እንዲሁም እንደፍቃዳቸው ልትሆንላቸው ትችላለህ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አንድ ቀን ትቀየራለህ፤ አንድ ቀን የተሻለ በሚሉት ሰው ይተኩሃል፤ አይንህን ለአፈር ይሉሃል፤ ፊታቸውን ያዞሩብሃል። ቢያምም እውነታው ግን ይሄው ነው። ምክንያቱም ሰዎች ስንባል እራስወዳዶች ነንና ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች ስንባል ከሚወደን ይልቅ የምንወደውን መከተል የሚቀናን ሚስጥር የሆንን ፍጥረቶች ስለሆንን ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች ስንባል ከእኛ ስሜት በላይ ለማንም ስለማንጨነቅ ነው። ተቀይረው ባሳመሙህ ሰዎች ላይ አትናደድ፤ ምክንያቱም ለእራሳቸው ታምነው ስለሚኖሩ፤ ቢያንስ በጊዜ ስለተለዩህ፣ የእራስህን መንገድ ለእራስህ ስለተውልህ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ቀን ትቀየራለህ፤ አንድ ቀን እንደ ሸንኮራ ታኝከህ ትተፋለህ፤ አንድ ቀን እንደፈለጉት ተጠቅመው አውጥተው ይጥሉሃል። ለእራስህ የምትሰጠውን ክብር ጠንቅቀህ እወቅ፤ ለእራስህ የምትሰጠውን ጊዜ በሚገባ አስተውል። ነገ ለሚጥልህ ሰው እራስህን አሳንሰህ አትሽቆጥቆጥ። ከማንም ጋር ሰላም መሆን ደግ ነው፤ ሰውን መውደድ፣ መፈለግ፣ ማፍቀር መልካም ነው። ነገር ግን ተመጣጣኝ ስሜት በሌለበት ሁነት ውስጥ አንድ ቀን የመተውና የመቀየሩ ነገር የማይቀር ጉዳይ ነውና ለእራስ የሚገባው ፍቅር ሊጎድል አይገባም። አንዳንዴ የዋህነትህ ዋጋ ያጣል፤ አሳቢነትህ ትርጉም አያገኝም፤ ፍቅርህ ከቁብነገር አይቆጠርም፤ እንክብካቤህ እንደ ጂል ያስመለክትሃል፤ ደግነትህ በሞኝነት ያስፈርጅሃል። የትኛውንም ግንኙነትህን ለማዳን ያንተ እረፍት አልባ ጥረት ብቻ ምንም ሊያመጣ አይችልም።

አዎ! ሰው የሚፈልገውን በመፈለግ ተጠምዷል፤ የሚወደውን በማሳደድ እረፍት አጥቷል፤ የሚያፈቅረውን በማስጨነቅ ለእራሱም ተጨንቋል። በተቃራኒው እርሱን የሚፈልገውን፣ ለእርሱ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ የሆነውን ዞር ብሎ መመልከት ቢችል ምን ነበረበት? የሚፈልግሽን አሻፈረኝ ብለሽ ሄደሽ የምትፈልጊው ሲጫወትብሽ መመለከቱ ምን ያስገኝልሽ ይሆን? ለአይን የምትሳሳልህን ገፍተህ ልታይህ እንኳን የምትጠየፍህ ላይ መጣበቅህ፣ እርሷ ስርስር ማለትህ ምን ይረባህ ይሆን? የምትፈልጊውን በቀየርሽበት አኳሃን አንቺም አንድ ቀን ይህ እጣ ይደርስሻል፤ የቀረበልህን ሲሳይ ገፍተህ በሔድክበት ማግስት የመገፋትን ልክ በተራህ ትቀምሳለህ። ለእራስህ የምታስብ ከሆን የሚበጅህን በጥንቃቄ ምረጥ፤ የአምላክን ፍቃድ ጠይቅ። እንደ ንጉስ ተወደህና ተከብረህ መኖር እየቻልክ ስለምን ተገፍተህና ተዋርደህ እንደ ባሪያ እንደምትኖር እራስህን ጠይቅ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.2K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:04:59
ነገ (ሐሙስ) ምሽት 12:00 ሰዓት
ህይወቶን ለማደስ የተዘጋጀ ቪድዮ!


ከወዲሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ቻናላችንን
SUBSCRIBE በማድረግና
የደውል ምልክቱን በማብራት ይጠብቁን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube LINK!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.2K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 08:09:08 መዳረሻህ በእጅህ ነው!
፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨
መነሻህ የትም ይሁን፣ የመጣሀው ከየትም ይሁን፣ ውልደትህ ከየትኛውም ቤተሰብ ይሁን፣ አሁን ያለህበት ሁኔታ ምንም ይሁን ነገር ግን አሁንም መዳረሻህ በእጅህ ነው፤ መጨረሻህን የምታሳምረው አንተ ነህ። ታሪኮቻችን መገለጫችን ሳይሆኑ መሸጋገሪያ ድልድዮቻችን ብቻ ናቸው፤ ገደባችን ሳይሆኑ ግፊቶቻችን ናቸው። የሆነ ጊዜ ምንም እንዳልነበሩ ጥለናቸው እንወጣለን፤ በእነርሱ ማለፋችንንም እንረሳዋለን፤ በእነርሱ ተሰርተን ፍፁም የተለየውን ማንነት እንፈጥራለን። የት ነበርን? ዛሬስ የት ነን? ነገስ የት እንሆን ይሆን? የረጅም ጊዜ ጥረት፣ እልህ አስጨራሽ ትግል፣ የሚታክት ውጣውረድ ቢሆንም የተሻለውን እስከ ፈለግን፣ የሚልቀው እንደሚገባን ካመንን ማቆም የሚባለውን ነገር በመርሳት የሃሳባችን ስፍራ መድረሳችን አይቀርም።

አዎ! ጀግናዬ..! መዳረሻህ በእጅህ ነው፤ የምትደርሰው ግን ካላቆምክ ብቻ ነው። በሚመጥንህ ደረጃ፣ በሚወክልህ ሁኔታ ግብህን የምታዘጋጀው፣ ውጥኑን የምታስቀምጠው አንተ ነህ። የእራስህ ግብ እስኪኖርህ የመስሪያ ቤትህን ግብ፣ የአሰሪዎችህን ራዕይ፣ የመንግስትን እቅድ ለመምታትና ለማሳካት መጣርህ ክፋት የለውም። ያንተ ላልሆነው ይህን ያክል ከጣርክ የእራስህ ሲሆን፣ ትርኩም የሚሰጥህና በብዙ እጥፍ አስደሳችና የሚያረካ ሲሆን ደግሞ ምን ያክል እንደምትጥር አስበው። ውጪ ላይ በማስተዋል የሚከታተልህ፣ የት እንደነበርክ የሚያውቅ፣ አሁን የት እንደሆንክ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው አለ። ምናልባትም ክትትሉ ሊያበረታታህ ወይም ሊማርብህ ወይም አደናቅፎ ሊጥልህ ይሆናል።

አዎ! እራስህን እየጠበክ ወደ መዳረሻህ ተጠጋ፤ ለእራስህ በቂ ጊዜ እየሰጠህ ራዕይህ ላይ ጠንክረህ ስራ፤ እራስህን እየተንከባከብክ እቅዶችህን ወደመከውን፣ ህልምህን ወደመኖር ግባ። እያንዳንዱን ውሳኔዎችህን የምታከብረው፣ ለገዛ ቃልህ የምትታመነው ሌላ ለማንም አይደለም፤ ለእራስህ ነው፤ እለት እለት እንዲሆንልህ ለምትመኘው መዳረሻህ ነው፤ ለትልቁ ህልምህ እውንነት ነው። መጋፈጥ ያለብህ ብዙ ጉዳይ ይኖርብሃል፤ ብዙ ማሰር፣ መፍታ ያለብህ እንቅፋት ይኖርሃል። ከመዳረሻህ በላይ ሂደቱ እንደሚያስፈልግህ እንዳትዘነገጋ። የአሸናፊነት አስተሳሰብ በውስጥህ እንዲሰርፅ አድርግ፤ ከተሸናፊዎች ራቅ፤ እንዳንተው ለመዳረሻቸው ከማይተጉ፣ ባንተ የእሳቤ ደረጃ ከማይመላለሱ፣ ህይወታቸውን በአላስፈላጊ ወሬና ንትርክ ከሚያባክኑ ሰዎች ተነጠል፤ የእራስህን ስኬትም እራስህ ወስን።
ድንቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.7K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ