Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-19 20:54:48 አዕምሮህን አሰልጥን!
፨፨፨፨///////////፨፨፨፨
አነቃቂ ንግግር ባትሰማ፣ አነቃቂ ፅሁፍ ባታነብ፣ አይዞህ በርታ የሚልህ ሰው ባታገኝ፣ ከጎንህ የሚቆም አጋዥ ባታገኝ ህይወትህን ሙሉ በሙሉ በእራስህ አነቃቂነትና በችግሮችህ አስገዳጅነት የምትቀይረው ይመስልሃል? ሁሌም ንቁ አትሆንም፤ ሁሌም ዝግጁ አትሆንም። ነገር ግን ከምንም በላይ ንቁና ዝግጁ የሚያደርግህን ተግባር በመፈፀም ንቃትን መላበስና ዝግጁ መሆን ትችላለህ። ያለህበት የገንዘብ እጦት የሚጠበቅብህን ሁሉ እንድታደርግ ካላነሳሳህ አንድ አነቃቂ ንግግር ወይም ፅሁፍ ሊያነቃና ሊያነሳሳህ አይችልም። አንተ ካለህበት ሁኔታ በተሻለ ጠንካራ ሰው እንድትሆን የሚያደርግህ ነገር የለም። የህመምህን ስሜት ታውቀዋለህ፤ የማጣት ስቃይ ደርሶብሃል፤ የመናቅ፣ የመገፋት ሃፍረት አጋጥሞሃል። በሌለህ ነገር መለካት ምንያክል እንደሚያም ታውቀዋለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! አዕምሮህን አሰልጥን! እራስህ ላይ ሰልጥን፤ ማንነትህ ላይ ንገስ። ማድረግ ያለብህን ለማድረግ፣ መገኘት የሚገባህ ቦታ ለመገኘት ቆራጥ ሁን። ማመንታት የስኬትህ ጠላት ነው። መወሰን ባለብህ ነገር ላይ በፍጥነት ወስን። ህልምህን ለመኖር ብዙ ያልተሟሉ ነገሮች ይኖራሉ፤ ነገር ግን አዕምሮህን ካሰለጠንክ፣ ማንነትህን ከህልምህ ጋር ካዋሃድክ፣ በአዎንታዊ አመለካከት ከተሞላህ ባለህ ነገር ህልምህን መኖር ትችላለህ። ስልጡን አዕምሮ አነቃቂ (motivation) አይጠብቅም፤ ህልመኛ ማንነት ሰበብ (excuse) አያበዛም፤ አዎንታዊ ስብዕና የአላማውን መሰናክሎች (obstacles) አይቆጥርም። ወደፊት የምትሔደው ሲመችህና የሚገፋህ ስታገኝ ብቻ አይደለም፤ ጉዞህን የምትቀጥለው አበረታች ድጋፍ ስታገኝ ብቻ አይደለም።

አዎ! ማድረግ ላለብህ ነገር የሚያስፈልግህ ምክንያት ሳይሆን ምግባር ነው። እያስጠላህ ጠንክሮ የመስራት ምግባር፤ እየታመምክ እስከጥግ የመታገል ምግባር፤ በማጣት ውስጥ የመፍጨርጨር ምግባር፣ እየተገፉ፣ እየተጠሉ፣ እየተሰደቡና እየተተቹ ህልምን የመኖር ምግባር። ማንም ቢሆን ሰው የሚያወጣው አዕምሮው ውስጥ ያለውን ሃሳብ እንጂ አንተን የሚገልፀውን ነገር አይደለም። እንደምታስጠላ ሲናገር እራሱን እየሰደበ እንደሆነ አይረዳም፤ አትችልም ሲልህ ለእራሱ እንደማይችል እያረጋጋጠ መሆኑ አይገባውም። የምትባለውን እንዳልሆንክ አምነህ ለእራስህ በሰጠሀው ልክ መጓዝም እራሱን የቻለ አንድ ትልቅ ምግባር ነው። በህልሙ ጉዳይ ከማንም የማይደራደር፣ ለራዕይው እውንነት ምንም ምክንያት የማያቀርብ፣ አላማውን ለማሳካት ማንንም የማይጠብቅ መሪ የሆነ ስልጡን አዕምሮ አለህ። በምንም ሁኔታ እንዲረበሽና በአሉታዊ አስተሳሰብ እንዲመረዝ አትፍቀድ። ስልጡኑን አዕምሮ ተጠቅመህ በምትፈልገው መንገድ፣ የምትፈልገውን ህይወት ኑር።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.7K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 14:15:57
ሰላም ውድ ቤተሰቦች!

ስንቶቻችሁ የዩትዩብ (YouTube ) ቻናላችንን SUBSCRIBE አድርጋችኋል?

SUBSCRIBE ያላደረጋችሁ ውድ ቤተሰቦች ከታች ባስቀመጥንላችሁ ማስፈንጠሪያ (LINK) በመግባት አሁን SUBSCRIBE በማድረግና የደውል ምልክቱን በመጫን ጠቃሚ ቪድዮዎችን ይከታተሉ።

እንዲሻሻሉ፣ እንዲሁም ቪድዮ እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉት ጥያቄ ካለም COMMENT አድርጉልን!
ቤተሰባችን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
እንወዳችኋለን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube Address LINK!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.7K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 07:34:01 በሚያድንህ ታመም!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
እለት እለት በስራህ ላይ በሰዓቱ የመትገኘው በወሩ መጨረሻ የሚከፈልህን ደሞዝ ታሳቢ አድርገህ ነው። ለአመታት ሳታቋርጥ ጠንክረህ ትምህርትህን የምትከታተለው ህይወትህን በፈለከው መንገድ እንደሚመራልህ ታሳቢ በማደረግ ነው። ህልሜ ለምትለው ነገር ወዳጆችህን የምትለው፣ ገንዘብህን ወጪ የምታደርገው፣ ጊዜህን የምትሰዋው፣ የምትገፋው፣ የምትሰቃየውና የምትታመመው አንድም ለውጣዊ እርካታህ ሁለትም እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ ወገኖችህን ለማገልገል ነው። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ጉዞህ ውስጥ ምንም ነገር በነፃ የምታደርገው ነገር የለም፤ ምንም ነገር በቀላሉ የሚያልፍ ነገር የለም፤ ምንም ነገር ዋጋ ሳትከፍልበት አይመጣም። እያዳንዱ ትልቅ ግኝት የእራሱ ውድ ክፍያ አለው፤ የትኛውም የተሻለ ውጤት አደጋ (Risk) አለው። ማግኘት ከፈለክ የማጣትንም ሪስክ መውሰድ ይኖርብሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! በሚያድንህ ታመም! ሔዶ ሔዶ ዋጋህን በሚመልሰው፣ ጥረትህን በሚያስተካክለው፣ የህይወት ደረጃህን በሚጨምረው ታመም። ደስታ ያለው ህመም ምን አይነት ነው? በእርግጥም ስሙ ብቻ ህመም የሆነ ነገር ግን ህመም የሌለው፣ በተቃራኒው እረፍታና ሰላምን የሚያድለው ህመም ምንድነው? ጂም ስትገባ ህመም እንዳለው፣ ስቃይ እንዳለው፣ ፈታኝ እንደሆነ፣ ላብህን እንደሚያንጠፈጥፈው ታውቀዋለህ ነገር ግን ስቃዩንም ጭምር ከልብህ ወደሀዋል፤ ከማንነትህ ጋር እንዲዋሃድ አድርገሀዋል፤ በሂደትም ለውጡን በሰውነትህ ላይ መመልከት ጀምረሃል። ቁጭ ብሎ፣ ጊዜ ወስዶ፣ እራስን ገዝቶ፣ ከሌሎች ማራኪና አጓጉዊ ነገሮች ተቆጥቦ አንድን መፅሐፍ አንብቦ መጨረስ ትግል አለው፤ ህመም ይኖረዋል፤ ዋጋም ያስከፍላል፤ ነገር ግን ከፈተናውና ከህመሙ በላይ የሚሰጥህ የተለየ ስሜት፣ የሚጨምርልህ እውቀትና እሴት ከልብህ እንድትወደውና እንድትዋሃደው አድርጎሃል።

አዎ! ሂደቱን እስከ ጥግ መውደድህ ህመሙን ያስረሳሃል፤ ሃላፊነትን መውሰድህ ውጤቱን ያማረ ያደርገዋል፤ ዋጋ ባለው ነገር መልፋትህ በእርግጥም ህመምህን ያቀለዋል። በምትወደው አለምና በማትወደው አለም ውስጥ ያለሀው አንተ እንድ አይነት ልትሆኑ አትችሉም። ህይወትህን ስትወዳት ምርጫዎችህን ታከብራለህ፤ በድግግሞሽህ ታድጋለህ፤ በተግባሮችህ ደስ ትሰኛለህ፤ እራስህ ላይ እሴትን ትጨምራለህ፤ ለምስጋና የፈጠንክ፣ ሌሎችንም ለማገዝ የተዘጋጀህ ትሆናለህ። ከወትሮው የተለዩት ውሳኔዎችህ ያስፈራሉ፤ ያስጨንቃሉ፤ ህመም ይኖራቸዋል። ነገር ግን መወሰናቸው የግድ ነው፤ መደረጋቸው፣ ወደ ምድር መውረዳቸው የግድ ነው። ህመም በተባለው እልህ አስጨራሽ ጉዞ መደሰት ስትጀምር በህመምህ መፈወስ ትጀምራለህ፤ በስቃይህ እየዳንክ፣ ህይወትህን እያሻሻልክና እያደክ ትመጣለህ። በሚያድንህ ታመም፤ በእርሱም ነፃ ውጣ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.9K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 20:55:48 በምርጫህ ድከም!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
ሰው በመሆንህ ብቻ ሰውነትህን ስታሳርፍና ከጡዘትህ ፋታ ስትወስድ ደስታን የምታጣጥምበት ወቅት ይኖራል፤ እንዲሁም ህይወትን ለማሸነፍ ስትጥር ስትለፋ ሰወኛው ድካምም አይተውህም። እንኳን ለአላማና ለህልምህ ይቅርና እንዲሁ ለማያይጠቅምህና ለማይመለከትህ ነገርም እራስህን ትሰጣለህ፤ ብዙ ዋጋ ትከፍላለህ፤ እጅጉንም ትደክማለህ። በተርጉም አልባው ድካም በመዋጥህ ብቻ ለጊዜውም ፋታ የምታጣበት ወቅት ይኖራል። ነገሩ ግን ይህን ያክል ቀላልና አልጋ በአልጋ አይደለም። የትም ብትሔድ ድካም አብሮህ አለ። ምንም ሳትሰራ በመቀመጥ የሚደክምህን ጊዜ አስታውስ፤ ሃሳብ ስታወጣ ስታወርድ ሙሉ ሰውነትህ የዛለበትን ወቅት አስበው። ስለሰራህ ከድካም አታመልጥህም፤ አርፈህ መቀመጥህም ከእርሱ አያስጥልህም።

አዎ! ጀግናዬ..! መድከምህ ካልቀረ በምርጫህ ድከም፤ መልፋትህ ካልቀረ ለምትወደው ነገር ልፋ። እንዲሁ እንደዋዛ የሚያልፉ ስንት ቀናት አሉ? ያለምንም ትርፍና ጥቅም የሚባክን ስንት ነገር አለ? ያለጥቅም ለሚባክነው ቁስና ገንዘብ ካዘንክ ስለራስህ ከንቱ ድካምና ብክነት ስታስብ ምን ይሰማህ ይሆን? እርግጥ ነው ህይወት ፋታ ካልሰጠችህ እራስህን መመልከት አትችልም። ነገር ግን የህይወትህ መሪ እንደሆንክ አትርሳ። ባንተ ህይወት ለሚከሰት ነገር ሁሉ ሃላፊነት አለብህ። በተለይ ለእያንዳንዱ ለምታወጣው ወጪ፣ ለምታባክነው ጊዜና ለምትደክምበት ነገር ትርጉም ልታገኝለት ይገባል። አሁን የምትኖረው ህይወት የትናንሾቹ እርምጃዎችህ ውጤት ነው። ትርጉም ያለው እርምጃ ስትራመድ ከነበረ፣ ዋጋ ያለው ነገር ላይ ትንሹን ጊዜህን ካሳለፍክ፣ በምትወደው ስፍራ ለተወሰኑ ሰዓታት ከተገኘህ፣ ስለህልምህ በትንሹ ማሰብ ከቻልክ በ80/20 መርህ (Pareto Principle) መሰረት አብዛኛው (80%) የህይወትህ ክፍል ደስተኛ፣ የተረጋጋና ትርጉም ያለው ይሆናል።

አዎ! ህይወትህ ትርጉም እንዲኖረው ቀንህን በሙሉ በቁብነገር ማሳለፍ አይጠበቅብህም። በየእለቱ ለተወሰነ ሰዓት ስለምትፈልገው ህይወት ማሰብ፣ ለተወሰነ ሰዓት ሃሳብህን መኖር፣ ለተወሰነ ሰዓት እራስህን መገምገም እጅጉን በጣም በቂ ነው። ቀኑን ሙሉ ስትደክም ብትውል ማታ ልታርፍ አካባቢ ስለምትፈልገው ነገር ደጋግመህ ማሰብህ ብቻ በሒደት ወደእርሱ እያቀረበህ ይመጣል። ከስጦታዎች ሁሉ የላቁት ስጦታዎችህ ጤናህና ጊዜህ ናቸው። እነርሱ ደግሞ እንዲሁ ለማይረባ፣ ለነገህ እንኳን በማይተርፉህ ነገሮች ይባክናሉ፤ ይጠፋሉ። ጤናህን ለምንም ብለህ ማጣት አይኖርብህም፤ ነገር ግን ብታጣ እንኳን እንዲ ነው ብለህ ለምታወራው፤ በህይወትህ ትርጉም ላለው፤ ከአላማህ ጋር ለሚገናኝ፣ ለሰው ልጆች ጠቃሚ ለሚያደርግህና ከአምላክም በረከትን ለሚያሰጥህ ነገር መሱዓት አድርገው። ጊዜህን አታባክን፤ ነገር ግን ቢባክን እንኳን ሊክስህ በሚችለው፣ ትርፍ በሚያስገኝልህ፣ በማይቆጭህና ሰዎችን በሚጠቅም ነገር ላይ አውለው።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.1K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 19:19:06 Watch "ምሽት ከመተኛቶ በፊትና ጠዋት ቀንዎን ከመጀመሮ በፊት ያዳምጡት! inspire ethiopia | impact seminars |@MentalCounsel" on YouTube



ለኛ ትልቅ ዋጋ አለውና አባኳን ቪድዮውን
LIKE
COMMENT
SHARE ማድረጎን እንዳይረሱ!
2.9K viewsedited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 07:29:33 በመንጋ አታስብ!
፨፨፨////////፨፨፨
አሁን ያለህበት ሁኔታ፣ የገጠመህ ችግር፣ ያለህበት አጣብቂኝ፣ የደረሰብህ በደል፣ ያባከንከው ጊዜ ካንተ ቁጥጥር ውጪ አይደለም። አንዳች ካንተ አቅም በላይ የመጣብህ የማትችለውና የማትወጣው ነገር የለም። ግራ የሚያጋቡ፣ ውስጥን የሚረብሹ፣ ስሜትህን የሚጎዱ ንግግሮችን ብትሰማ መዝኖ አመዛዝኖ ለእራስህ በሚጠቅምህና በሚመጥንህ ደረጃ መቀበል ትችላለህ። ብዙ ሰው የተቸውን ነገር ለመተቸት አትሩጥ፤ ብዙ ሰው የተቀበለውንም ለመቀበል አትጣደፍ። አንተ ብዙ ሳትሆን አንድ ሰው ነህ። የእራስህ ደረጃ አለህ፤ ማንነት አለህ፤ አቋም አለህ፤ ልክ አለህ፤ አስተሳሰብ አለህ። በመንጋ ማሰብህ፣ በመንጋ መቃወምህ፣ በመንጋ መደገፍህ ከመደበኝነት የዘለለ ትርጉም አይሰጥህም።

አዎ! ጀግናዬ..! በመንጋ አታስብ! የእራስህ አቋም እንዳለህ አስተውል፤ የእራስህ ልክ እንዳለህ እወቅ። ማንም በፈለገው መንገድ የሚነዳህ አይደለህም፤ ማንም በእራሱ አመለካከት መዓቀፍ የሚያስርህ አይደለህም። ሰውን ሰው የሚያስብለው ከማንነቱና ከአስተሳሰቡ ባሻገር የማይደራደርበት የእራሱ የግል አቋሙ ነው። የተባለውን ሁሉ እየተቀበልክ፣ ለተቃውሞ ሁሉ እየተፋጠንክ፣ ለስድብና ስም ለማጥፋት እየተንደረደርክ እንዴት የእራስህ መገለጫ ሊኖርህ ይችላል? አብዛኛው ሰው በሚመጥነው ሳይሆን በሚመስለው መንገድ እየተጓዘ፣ የሚመስለውን እያደረገ በሚኖርበት ጊዜ ያንተ አቋም አልባነት፣ ያንተ ወደ ነፈሰው መንፈስ ቢያጠፋህ እንጂ ወደ ወደ እራስህ መንገድ አያስገባህም።

አዎ! ሰዎች ያሉትን ስለደገምክላቸው ሊወዱህ ይችላሉ፣ አንተ ግን ያንን በማለትህ እራስህን ትወደው ይሆን? መንጋው አንድ ሰሞን ደጋፊ ነው፤ አንድ ሰሞን ደግሞ በተቃራኒው የሚያንቋሽሽና የሚሳደብ ተቃዋሚ ነው። በዚህ መሃል ከሆንክ ግር ብለህ ትወስናለህ፤ ግር ብለህ ስም ታጠፋለህ፤ ግር ብለህ በማያገባህ ጉዳይ ጊዜህን ታጠፋለህ። በቀጥታ አንተን የማይመለከትና ምንም ልታደርገው ስለምትችለው ነገር ሰምተህ ምንያክል የመጨነቅ ልማዱ አለህ? ምንያክል ከስራ በላይ ወሬ ላይ ታተኩራለህ? ምንም ያልሰራ የሚሰራውን ከላይ እስከታች የሚተችበትና የሚያብጠለጥልበት መንጋ ውስጥ ተቀምጠህ እንዴት ሰውን በስራው ልትዳኘው ትችላለህ? እራስህን ተመልከት፤ የት ነህ? በአጨብጫቢነተና የተባለውን ሁሉ የምታጎላበት ስፍራ ወይስ የእራስህ፣ የሚመጥንህና አንተነትህን የሚገልፅ ቦታ? በመንጋ አታስብ፤ በመንጋ አትፍረድ፤ በመንጋ አትኮንን። እራስህን እወቅ፤ ነገሮችን አመዛዝን፤ የሚመለከትህ ላይ ብላ አተኩር፤ በእራስህ ማንነት እውቅናን አግኝ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.5K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 20:40:06 ዶፓሚንህን ተቆጣጠር!
፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨
ከረጅም ጊዜ ጥበቃና ናፍቆት ቦሃላ ያገኘሀውን የምትወደውን ምግብ ሰትመገብ የሚሰማህን ስሜት አስታውስ፤ ጠቃሚና ጎጂነቱን ሳታስተውል እንዲሁ ልማድ ያደረከውን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስቂኝ ነገሮችን ስትመለከት ውስጥህ የሚሰጠውን ምላሽ አስተውል። በዚህ ሰዓት ደስታ እንዲሰማህ የሚያደርገው ሰውነትህ ለሚለቀው ዶፖሚን የተባለ ሆርሞን አዕምሮህ ሽልማት ሲሰጠው ነው። ይህ ሆርሞን ጠቃሚ ልማድንም ለመገንባት አይነተኛ ሚናን ይጫወታል። ምክንያቱም ግንኙነቱ ከደስታ ጋር ነውና። ልማዱ የምትፈልገውና አዕምሮህ ያመነበት ከሆነ ከቀድሞ ልማድህ ለመለየት ቢያታግልህም አንዴ ልማድ ከሆነ፣ ከተዋሃድህና የደስታህ ምክንያት ከሆነ የዶፓሚንህ ማመንጪያ ምክንያት ይሆናል ማለት ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ዶፓሚንህን (dopamine) ተቆጣጠር! እንዲኖሩ የማትፈልጋቸው፣ እየጠቀሙህ ያይደሉ፣ በስሜትህ እየተጫወቱ የሚገኙ፣ ይህን ሆርሞን በየጊዜው እያመጩ የእነርሱ ባሪያ ያደረጉህን ለጊዜው ጣፋጭ ቦሃላ ግን እጅግ መራርና ጎምዛዛ ከሚሆኑ ልማዶች ተላቀቅ። ዶፓሚን ከዘላቂውና ከጠቃሚው ይልቅ ከጣፋጩ ጋር ያስርሃል፤ ከሚያተርፍልህ ያርቅሃል፤ ከጤናህ በላይ በጊዜያዊ እርካታ ይሸውድሃል፤ በሳቅ በጫወታ ጊዜህን ይበላል። ሁሉም ሰው ትግል ውስጥ ነው። ለምን የማይጠቅመውን ነገር ደጋግሞ ሲያደርግ እራሱን እንደሚያገኝ አያውቅም፤ ለምን እንደሚያቆመው የወሰነውን መጥፎ ተግባር ሲያደርገው እንደሚገኝ አልተረዳም። ዋናው ምክንያት ሌላ ምንም ሳይሆን ባንፈልገውም በሰዓቱ ደስታን እንድናገኝ የሚያደርገው ዶፓሚን መመንጨቱ ነው።

አዎ! ዘላቂውና ጊዜያዊው ነገር ከፊትህ ነው። የሚበጅህን አንተ ታውቃለህ። በሚያስደስትህ፣ ነገር ግን በማይጠቅምህ ልማድ መታሰር ወይም በጊዜው ከማይመችህ፣ ነገር ግን ወደፊት ከምቾት በላይ መደላደልን የሚያድልህን ማድረግ። ዛሬ እያስደሰተህ ነገ ችግርን የሚልክብህ አለ፤ ዛሬ እያለፋህ፣ ዛሬ እያሳመመህ ነገ የሚያሳርፍህና ሰላም የሚሰጥህ ነገርም እንዲሁ አለ። ጣፋጩን የምትመርጠው ጠዓሙ ስለሚጥም እንጂ ጠቃሚነቱን አስበህ፣ ለጤናህ ተጨንቀህ አይደለም። አቁም አቁም የማይልህ መጠፎ ልማድህም የእራሱ ጠዓም አለው፤ በጣፋጭ ነገር የሚያስፈነጥዝህን፣ አንድን ነገር ደጋግመህ እንድታደርገው የሚገፋፋህን፣ ካላደረከው ምቾት እንድታጣ የሚያደርግህን በውስጥህ የተቀመጠ የምተቾትህን አለቃ፣ በጊዜያዊ ደስታ እያሳሳቀ ወደ ገደል የሚወስድህን ዶፓሚንህን በፍቃድህ ስር አውለው፤ እራስህንም ከመጥፎ ልማዶችህ ጥላ ስር አውጣ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.6K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 14:58:34
ሰላም ውድ ቤተሰቦች!
ነገ (ሐሙስ) ምሽት 12:00 ሰዓት
ለሰላማዊ
እንቅልፍና ለብሩህ ቀን በተዘጋጀ ቪድዮ ይጠብቁን!

ከወዲሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ቻናላችንን
SUBSCRIBE በማድረግና
የደውል ምልክቱን በማብራት ይጠብቁን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube LINK!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.4K viewsedited  11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:48:43 ሸክምህን ቀንስ!
፨፨፨////////፨፨፨
እለት እለት ከሚያደቡበህ፣ ውድቀትህን አጥብቀው ከሚሹ፣ ኪሳራህን ከሚጠባበቁ፣ በወጣህ በገባህ ቁጥር ጥፋትህን ከሚቆጥሩ፣ እንዲሁ በባዶ ቀልባቸው ከማይወድህ፣ ያለምክንያት ሊርቁህ ከሚፈልጉ ሰዎች ምን ህብረት አለህ? የምትፈልገውን እየሰጡህ ነውን? ወደምትፈልገው ስፍራ እየመሩህ ነውን? አንዳች ከእነርሱ ያተረፍከው፣ ለህልምህ እውንነት ያበረከቱት አስተዋፅዖ ምንድነው? የምትበርበትን ከፍታ ለመጨመር ግዴታ የያዝከውን ሸክም መጣል ይኖርብሃል፤ ከሸክሞችህ ዋንኞቹ ደግሞ በሃሳብ፣ በምኞት፣ በተግባር የሚጠሉህ ሰዎች ናቸው። የሚጠየፉህን፣ ወደኋላ የሚጎትቱህን፣ ክፉ የሚመኙልህን ሰዎች ተሸክመህ እስኬት መጓዝ የምትችል ይመስልሃል? ምንያክል ርቀት የምትሔድ ይመስልሃል? ከመጥፎ ልማዶችህ መለየት እንዳለብህ ሁሉ የሚጠሉህን ሰዎች የመለየት ግዴታ አለብህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሩቅ ለመሔድ ሸክምህን ቀንስ፤ የሚጠሉህን ችላ በል፤ ከህይወትህ ዞር አድርጋቸው፤ አስወግዳቸው። መልካም የማያስቡልህን አርቅ፤ በብርታት ቦታ እንቅፋት የሚሆኑህን ሰዎች ከዙሪያህ አስወግድ። ጠላትህን ውደድ፣ የሚረግምህንም መርቅ የሚለውን የአምላክ ቃል ለመፈፀም መልካም እያደረክላቸው፣ እያሰብክላቸው፣ በፍቅርህ እየማረካቸው መቆየት ትችላለህ ነገር ግን በእነርሱ አሰናካይ ሃሳብ፣ በእነርሱ የምቀኝነት ደባ፣ በእነርሱ ቅስም ሰባሪ ንግግር የመጎዳትና የመሰበር ግዴታ የለብህም። ብትወዳቸውም ከህይወትህ ታስወጣቸዋለህ፤ ብታስብላቸውም አስተያየታቸውን አትቀበልም፤ ብታከብራቸውም ንግግራቸውን አትሰማም። ክፋት አስበህ፣ ተናደህባቸው ወይም አዝነህባቸው አይደለም። እራስህን ለማዳን፣ ጠንካራ ጎንህን ለማጎልበት፣ በብርታት ወደፊት ለመጓዝ፣ ፍጥነትህን ለመጨመር፣ እራስህን ነፃ ለማውጣት ያለህ ብቸኛ አማራጭ እርሱ ስለሆነ ነው።

አዎ! እስከ መቼ ከህይወት ሸክምህ ቅንጣት ከማይቀንሱልህና ከማይካፈሉህ ሰዎች ጋር ትደክማለህ? እስከ መቼ ውድቀትህን አጥብቀው ከሚመኙ ሰዎች ጋር ትቀጥላለህ? እስከመቼ ከመንገድህ ከሚያስቀሩህ፣ ሃሳብህን ከሚቃረኑ፣ እቅድህን ከሚያምታቱ፣ ህልምህን ከሚያጨናግፉ ሰዎች ጋር ትጓዛለህ? የሚደግፉህ ከሆነ ይደግፉሃል፤ የሚያግዙህ ከሆነ ያግዙሃል፤ የሚረዱህ ከሆነ ይረዱሃል ካልሆነ ግን ውድ ጊዜህን እያባከኑብህ፣ አቅምህን እያሳነሱብህ፣ ተነሳሽነትህን እየቀበሩት፣ መነቃቃትህን ውሃ እየደፉበት ልትመርጣቸውና አብረሃቸው ልትሰራ አትችልም። እራስህን ለማዳን አትችልም ለሚሉህ መልስ መፈለግ አይጠበቅብህም፤ አሉታዊ ንግግርን የሚያቀርቡልህን መጥላት አይኖርብህም። እራስህ ላይ ማተኮር፣ ከእነርሱ ዞር ማለት፤ ፊትህን ማዞር፣ ቀስበቀስ ከህይወትህ ማስወጣት፤ በምትኩ የልብ ወዳጆችህንና ደጋፊዎችህን ማስገባት እጅግ በጣም በቂ ነው።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
451 viewsedited  04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 20:48:24 ሩቅ ነው!
፨፨///፨፨
የምትፈልገው፣ የምትመኘው፣ የምትናፍቀው ትልቅ ነገር ከምቾት ቀጠናህ እጅግ በጣም ሩቅ ነው፤ ዘወትር በልብህ የሚመላለሰው፣ በተደጋጋሚ የምትመለከተው፣ ከአዕምሮህ አልጠፋ ያለው ህልምህ ያለው ከምቾትህ በተቃራኒ አቅጣጫ ነው። ችግር ስለተደራረበ፣ ስቃይ ስለተፈራረቀ፣ ማጣት ስላጎሳቆለህ፣ መገፋት ስላሰቃየህ አታልቅስ፤ አትጨነቅ፤ ፈጣሪህንም አታማር። ጠንከር በል፣ የማያልፍ ነገር የለም፤ ሁሉም ያልፋል። ማለፉ ግን በዋዛ እንዳይሆን ብቻ ተጠንቀቅ። ሲያልፍ ቀይሮህ፣ አሳድጎህና ባርኮህ መሆን እንዳለበት ተረዳ። እያለቀስክ ሳይሆን እየተማርክ ወደፊት ተጓዝ፤ እያማረርክ ሳይሆን እያመሰገንክ መንገድህን ቀጥል፤ እያነስክ፣ እየሰነፍክ ሳይሆን ከፍ እያልክ፣ እየበረታህ መጪውን ጊዜ በተስፋ ተመልከት። በፈተናህ መሃል ዋጋህን ጨምር።

አዎ! ጀግናዬ..! ሩቅ ነው! ተመችቶኝ እቀየራለሁ፤ ከችግር ነፃ ሆኜ አድጋለሁ፤ በነፃነት እለወጣለሁ ብለህ የምታስብ ከሆነ አሁንም ስኬትህ በጣም ሩቅ ነው፤ ደስታህ ገና ነው፤ እውነተኛው ውስጣዊ ሰላምህ አልመጣም፤ ፈጣሪህን ከልብህ አላገኘሀውም። ምቾት ውስጥ እንደሆንክ ሲሰማህ መቅለጥ ትጀምራለህ፤ ወደ ኋላ መጓዝ፣ አቅምህን ማሳነስ፣ ለውጥን መሸሽ፣ በአንድ ነገር መወሰን ትጀምራለህ። ችግር ቢመጣ ካልገደለህ ሌላ ምን ልትሆን ትችላለህ? ግፋ ቢል አለኝ የምትለውን ነገር ቢያሳጣህ ነው፤ የሰዎች መዘባበቻና መጠቋቆሚያ ቢያደርግህ ነው፤ ግፋ ቢል ጭንቀት ውስጥ ቢከትህ፣ በሃሳብ ቢወጥርህ ነው። ነገር ግን ከዚያ በላይ ማየት ከቻልክ የለውጥህን ቁልፍ፣ የእድገትህን በረከት በእርሱ ውስጥ ታገኘዋለህ። "የማልወጣው አዘቅት ውስጥ ገብቼያለሁና ዋጋ የለኝም" ብለህ ከማሰብህ በፊት አዘቅት ያልከው ችግርህ ምን ይዞ እንደመጣ በጥሞና ተመልከት።

አዎ! ከዚም ከዛም ይንፈስ፣ ከላይም ከታችም ያስጨንቅህ፣ ገንዘብ ይጠርህ፣ የምትረዳው ነገር እጣ፣ ኑሮው ይወደድብህ ያኔ ለውጥ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነ ትረዳለህ፤ ያኔ እድገት ለደርድር የሚቀርብ ነገር እንዳልሆነ ትገነዘባለህ፤ ያኔ በጨለማ ውስጥ ብረሃንን ማሳደድ ትጀምራለህ። እንደፈለከው እየኖርክ፣ ሁሉን እያገኘህ፣ በሁሉ ተደግፈህ አዲስ ነገር አያለው፣ ትክክለኛው ማንነቴን እረዳለሁ፣ እራሴን አውቃለህ፣ ወደፊት እጓዛለሁ ብለህ እንዳታስብ። ከማጣት ቦሃላ የሚመጣ ማግኘት ብዙ ያስተምራል፤ ብዙ ከመገፋት ቦሃላ የሚገኝ ፍቅር ብዙ ዋጋን ይጨምራል። ባለህበት የተደላደለ ህይወት አትታለል፤ ዞር ዞር ብለህ እራስህን ፈትሽ፣ በችግርህ ውስጥ ማንነትህን አጉልተህ አሳይ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
1.7K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ