Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-06-05 07:35:37 አውቀህ ተሰቃይ!
፨፨፨/////////፨፨፨
ልታድግ የምትችልበት ብቸኛው ጊዜ ምቾት የሌለህ፣ ስቃይህ የበዛ፣ የመረረህና ፈተና ውስጥ በወደክበት ጊዜ ነው። አንድ አስደጋጭ አጋጣሚ ሲፈጠር የሚመጣልህን ሃይልና ጉልበት አስታውስ። በህይወት ፈተናም ይህ ጉልበት በብዙ እጥፍ ውስጥህ ተቀምጧል። እድገትን ከፈለክ ውስጥህ ሊረበሽ ይገባል፤ ለውጥን ከተመኘህ ሁኔታህ መናወጥ አለበት፤ ምቾት ከማጣት፣ ከእራስ ጋር ከመታገል ጋር ፍቅር ሊይዝህ ይገባል። ረጅሙን ጊዜ በመኝታ እያሳለፍክ፣ የበለጠውን ሰዓት በመዝናናትና ዶፓሚንህን ለመመገብ እየተጠቀምከው፣ ብዙ ሰዓት በቀልድና ጫወታ ላይ እያሳለፍክ፣ ምቾት እስኪያሰክርህ እየጠበክ ለውጥን መናፈቅ፤ እድገትን መመኘት ቅዠት ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ምቾትህን አሳልፈህ ስጥ፤ መደላደለህን መሱዓት አድርገው፤ ጥለሀው ውጣ፤ እለት እለት ምቾት የሚነሳህና የሚጎረብጥህ ሁኔታ ውስጥ እራስህን አስገባ፤ ለእራስህ ስትል፣ እድገትህን መርጠህ አውቀህ ተሰቃይ፤ ገብቶህ ዋጋ ክፈል፤ እየመረረህ እራስህን አድን። ማንም ተመችቶት ስኬታማ የሆነ እንዳይመስልህ። የስኬት ጉዞ መራርና ፈታኝ ባይሆን ብዙ ስኬታማ ሰዎችን ታገኝ ነበር። ነገር ግን አይደለም፤ ስኬት ብዙ ሰው የሚጠላውን ምቾት ማጣት፤ ምቾት ማጣትን በእራሱ የመውደድን ሃይል፣ አስደሳቹን ስቃይ የመምረጥን ብርታ ይፈልጋል። ጠቃሚና ዋጋ ያለው ነገር ሆኖ ሳለ አንተ ግን ምቾት ስላልሰጠህና ፋታ ስለነሳህ ብቻ ደጋግመህ እያቆምክ ምቾትህን የምትጠብቅ ከሆነ የጉዞህ ማብቂያ ቅርብ እንደሚሆን አትጠራጠር።

አዎ! አትክልት ለማደግ ውሃና ፀሃይ ይፈልጋል፤ ላንተም እድገት ምቾት ማጣትና ፈተና እንደ ውሃና የፀሃይ ብረሃን እጅግ ወሳኝ ነው። ምቾት በእርግጥም ደስ ይላል፤ እረፍት አለው በዛው ልክ ግን እያሳነሰ፣ እያደከመ፣ ልፍስፍስና በቀላሉ ተሰባሪ እያደረገ ይመጣል። እድገትን ከፈለክ ፈተና፣ ስቃይ፣ መከራ የግድ ነው። የማትወደውን ስራ መስራትህ ስቃይ ከሆነ የምትወደውን ለመፈለግ እንደ ብርታት ተጠቀመው፤ የማይጠቅምህ ስፍራ መገኘትህ ሰላም ከነሳህ ሌላ ቦታ ለመቀየር ያንን ሁኔታ እንደ ሃይል ተጠቀመው። በአሁን ሰዓት ያለኝ ይበቃኛል፤ ማደግ አልፈልግም፤ የዛሬ ገቢዬ ህይወቴን ለመምራት እጅግ በቂ ነው ብሎ በምቾት የሚናገር ሰው አይኖርም። ምክንያቱም መሬት ላይ ያለው ሁኔታ በእራሱ ይህን ለማለት አይፈቅድምና ነው። በየእለቱ ችግር ወዳንተ እየተጠጋ ነውና ቁጭ ብለህ ከምታየው ተነስተህ ሳይደርስብህ ሔደህ ተጋፈጠው፤ ምቾትህን ለእድገትህ መሱዓት አድርገው።
ግሩም ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.3K viewsedited  04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 07:34:59
1.9K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 20:52:09 ከተከታይነት ወደ አስከታይነት!
፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ ሀገር ኢንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስቴር ማርጋሬት ታቸር እንዲህ የሚል አባባል አላቸው:- "አብዛኛውን ህዝብ አትከተል፣ በምትኩ ህዝቡ አንተን እንዲከተል አድርግ።" ሃሳብህ ምንም ሊሆን ይችላል፣ ምርጫህ የትኛውንም አይነት ሊሆን ይችላል፣ እንደሚያዋጣህና እንደሚያስደስትህ ካመንክ ማንም እንዲከተልህ አትጠብቅ። ልዩነትህ የሚከተሉህን ሰዎች መፍጠር እንጂ በሔድክበት ሁሉ የማንም ዝግጅት አድማቂ፣ የማንም መድረክ አሟሟቂና የማንም ተከታይ መሆን እንዳልሆነ እወቅ። ልክ እንደ ብዙዎች ማጨብጨብና የተባለውን መደጋጋም ትልቅ ተዓምር የሚፈልግ ነገር አይደለም። ተዓምሩ በእራስህ መንገድ ወጥቶ መታየት፣ ድንቅ የሚያስብልህ ምንም ብትባል የሆንከውን ሆነህ መገኘት ነው፤ የተለየ የሚያደርግህ በምርጫህ ምክንያት አንገትህን ሳትደፋ በልበሙሉነት መቆምህ ነው፤ የሚያስከብርህ በእራስመተማመንህን በተለየው ተግባርህ መግለፅ መቻልህ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ከተከታይነት ወደ አስከታይነት፤ ከአድናቂነት ወደ ተደናቂነት፣ ከአጨብጫቢነት ወደ አስጨብጫቢት ለመቀየር የምትወስንበት ጊዜ አሁን ነው። ትላልቅ ነገሮችን መመኘት ጀምር፤ ስትጀምረው ቅዠት ስለሚመስልህ ነገር ዳጋግመህ አስብ፤ ለዘመናት እንደማይሆንልህ የሚሰማህን ነገር ለማድረግ ተንቀሳቀስ። ፍራቻ ከጅማሬህ ቦሃላ አይኖርም፤ ጭንቀትህ እርምጃ ከወሰድክ ቦሃላ አይመጣብህም፤ ይሉኝታህ እራስህን መሆን ስትጀምር ይርቅሃል። ቀላል መንገድ እንዳልመረጥክ አንተም ታውቀዋለህ። ነገር ግን ከባድ ሰው ለመሆን ከባዱ መንገድ ብቸኛው አማራጭህ ነው። እድሜ ልክህን በተከታይነት አትኖርም፤ ዘመንህን በሙሉ የተባለውን እየደገምክ፣ የተወራውን እያስተጋባህ አትቀጥልም። የእርስህ መለያ መፍጠር ትችላለህ።

አዎ! አላማህን ግልፅና በቀላሉ የምትረዳው አድርገህ አስቀምጥ፤ ለትግበራ የሚመች እቅድ ይኑርህ፤ እንደ አብዛኛው መንጋ መከተልና እራስን በበታችነት የመመልከትን ጊዜ እንዲያበቃ አድርግ። ከምንም ከማንም የምታስቀድም አንድ አላማ ይኖርሃል፤ እርሱም ቀና ያደርግሃል፤ ያሳልፍልሃል፤ ከተከታይነት ወደ አስከታይነት ያሸጋግርሃል። ብቻህን በምታራምደው አዎንታዊ ሃሳብ እምነት ይኑርህ፤ በእርሱ ምክንያት ለሚመጣብህ የትኛውም ነገር ሃላፊነት ለመውሰድ እራስህን አዘጋጅ። ጂም ሮን እንዳለው "ምቾትን ሳይሆን ውጣውረድን ጠይቅ። መቶ አመት ያለምንም እድገት በምቾት ከመኖር ሰላሳ አመት በውጣውረድ ውስጥ በጀብዱ መኖር ይሻላል።" የትኛውንም አዲስ ነገር መፍጠር ከፈለክ፣ በየትኛው መንገድ ተፅዕኖ መፍጠር ምኞትህ ከሆነ ከመንጋው የመውጣት ጉዳይህ አጠያያቂ አይደለም። ወደ እራስህ መዳረሻ ተጠጋ፤ እምነትን ከእራስህ ጀምር፤ በምርጫህ ተፅዕኖ ወደመፍጠር ተሸጋገር።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.7K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 19:03:21 ከነገው ስራ የተቀነጨበ!

(አይናችሁን ጨፍናችሁ Earphone, Headset ተጠቅማችሁ በተመስጦ እንድታዳምጡት ይመከራል።)

ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ቻናላችንን
SUBSCRIBE በማድረግና
የደውል ምልክቱን በማብራት ሙሉውን መከታተል ይችላሉ!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube LINK!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.5K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 18:39:28
ሰላም ውድ ቤተሰቦች! እንዴት አመሻችሁ?

ለነጋችሁ መልካምና አስደሳች ውሎ በአምላካችሁ ድንቅ ስራ የምትታደሱበትን አዲስ ስራ አዘጋጅተናል።
ነገ (ሰኞ) ጠዋት 02:00 ሰዓት በዩትዩብ ቻናላችን እንገናኝ።

ከወዲሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ቻናላችንን
SUBSCRIBE በማድረግና
የደውል ምልክቱን በማብራት ይጠብቁን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube LINK!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.4K views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 07:19:25 ስራው ግሩም ነው!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
እርሱም ፍጥረትን ሁሉ ውብ አድርጎ ሰራው፤ በመንፈሱም እፁብ ድንቅ እንከን አልባ አድርጎ ፈጠራቸው። እኛም ድንቅ የእጆቹ ስራ፣ ብሩካን የመንፈስ ልጆቹ ነንና እግዚአብሔር አምላክ ፍፁም ይወደናል፤ ፍፁም ያስብልናል፤ ፍፁም ይሳሳልናል፤ ከምህረት እጆቹ ከልክሎን፣ ከፀጋው መዳፉም አጉድሎብን አያውቅም። ለሰከንዳት በህይወት መኖራችን በእርሱ ምህረት፣ በእርሱ እዝነትና ርህራሔ ነው። በማለዳው የአዕዋፍ ዝማሬ፣ በጠዋቱ ኩልል ባለ ሰማይ፣ ከምግብ በሚልቀው ንፁው አየር በየእለቱ መንፈሳችንን ሲያድሰው እንዴት ደስ ይላል። አምላክ አብሮህ እንዳለ፣ እግዚአብሔር እንደሚጠብቅህ ካመንክና ካሰብክ የህይወትህ ድንቅነት ለአፍታም መንገድ አይስትም፤ ለአፍታም አቅጣጫ አይቀይርም።

አዎ! ጀግናዬ..! እርሱ ስራው ግሩም ነው፤ ስራው እጅግ ድንቅ ነው። አንተም አንዱ ድንቅ ስራው ነህ። ከህፃንነት ጀምሮ በጥበብ በሞገስ ባርኮ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን አድሎ፣ በስስት አይኖቹ እየተመለከተ፣ በብዙ ስቃይ፣ በብዙ መከራ መሃል ይዞህ የወጣ፣ እነሆ ለዛሬዋ ውብና አስደሳች ቀን ያደረሰህም እርሱ ነው። ፈጣሪ ስራው ብዙ ነው፤ ሰርቶ አያልቅበትም፤ ጀምሮም አይተወውም። ልብህ ውስጥ እርሱ እንዳለ አስብ፤ መንፈስህ በእርሱ ሃይል እንደሚመራ እወቅ። በሰላም መንቃት፣ ቀንን በሰላም በፍቅር ማሳለፍ፣ ዳግም ለዘመናት ደጋግሞ በሰላም ወደ መኝታ ማምራት አንድ ሰው ብቻውን በፍቃዱ ለእራሱ ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይደለም። በእድሜህ ቁጥር በሰላም የነቃህበትን ቀን አስታውስ፤ ለመታደስ በሰላም ያረፍክበትን ቀን አስታውስ። ያለምንም ችግር በነፃነት ከምግብ የሚልቀውን፣ ከመጠጥ የሚገዝፈውን ንፁውን አየር የተመገብክበት፣ እስከ ውስጥህ የተጎነጨህበትን ሰከንዳት ቁጠር።

አዎ! የሰጠህን ሳይሆን የሰጠህን ነገር የተጠቀምክበትን ሰዓትና ቀን መቁጠር በእራሱ እጅግ ከባድ ነው፤ ብዛቱ እልፍ ነው፤ ቁጥሩ በቀላሉ አይደረስም። ዋጋው ግን በዛው ልክ አልታሰበም፤ በብዛቱ ልክ ስፍራ አልተሰጠውም። የአምላክህን ውለታ መመለስ ባትችል እንኳን ቁጠረው፤ ዋጋ ስጠው፤ ደጋግመህ አስበው፤ በእርሱ መንገድ በረከትህን ተመልከት። የጤና ሰጪም ነሺም እርሱ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አልወሰደብህም፤ አልነሳህም። የቀኑ ባለቤት እርሱ ሆኖ ሳለ አንዳች አላጎደለብህም። ምንም ቢፈጠር የእግዚአብሔር ስራ ፍፁም ነው፤ ፍፁምነቱም ላንተ በሚበጅህ፣ ላንተ በሚሆንህ ልክ ነው። እለት እለት ማዳኑን ተመልከት፣ በረከቶቹን ቁጠር፣ ስጦታዎቹን አስታውስ፣ ስራውን አድነቅ። ባለህ ላይ ይጨመርልህ ዘንድ ምስጋናህን አታጉድል፤ ከውዳሴህ አትታጎል።
ብሩክ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.6K views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 07:18:47
2.4K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 20:37:40 በተስፋህ አትጨክን!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
ተስፋ ነፃ ነው፤ በዛውም ልክ ተስፋ ማድረግ ከባድ፣ ተስፋ መቁረጥ ደግሞ እጅጉን ቀላል ነው። አይተህ የማታውቀውን ነገር በተስፋ ትመለከተዋለህ፤ ያልሆነውን ነገር በተስፋህ እገዛ እንደሚሆን ታምናለህ፤ ያላገኘሀውን ነገር እንደምታገኘው በሙሉ ልብህ ትጠብቃለህ። ተስፋ አጥተህ ትንፋሽ አይኖርህም፤ እስትንፋስህ አይታዘዝህም፤ ከሰከንዳት አታልፍም፤ ምንም ነገር አታይም። ህይወት በሙሉ በተስፋ ተሞልታለች፤ ምክንያቱም ያለተስፋ ምንም ነችና። " እኔ ተስፋ የለኝም፤ እኔ አልረባም፤ እኔ የምሆን ሰው አይደለሁም።" የሚል ሰው በእርግጥም ተስፋ ስሌለው ሳይሆን በተስፋው ስለማያምን ነው። አውቀሀውም ይሁን ሳታውቀው ዛሬ በደረጃህ የምትለፋው፣ ጠዋት ወተህ ማታ የምትገባው፣ ደፋ ቀና የምትለው፣ ግንኙነት የምትጀምረው፣ ከሰዎች የምትወዳጀው ተስፋ ስላለህ ነው፤ ነገን ስለምታስብ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ተስፋ ስንቅህ ነው፤ ተስፋ ስጦታህ ነው፤ ተስፋ በረከትህ ነው። እንዴትም ከህይወትህ እንዲወጣ አትፍቀድ፤ በምንም ተዓምር ለተስፋህ ጀርባህን አትስጠው። የምር ህይወት ቢከብድህ፣ ነገሮች አልሆን ቢሉህ፣ ችግሮች ቢደራረቡብህ አንድ ያለህ ማምለጫ ተስፋህ ነው፤ ከአምላክ የምትጠብቀው ስጦታ ነው። ከመሰበር ቦሃላ መጠገን እንዳለ ተስፋ አድርግ፤ ከማጣት ቦሃላ ማግኘት እንደሚኖር ተስፋ አድርግ፤ ከመከዳት ማግስት ታማኝ እንደሚገኝ ተስፋ አድርግ። አንዴ የተበላሸ ነገር ቢኖርም ዳግም እንደሚስተካከልና እንደሚታረም መጠበቅ ሰላምን ለማግኘትና መንፈስን ለማረጋጋት እጅግ ወሳኝ ነው። ጉዳይህ ምንም ያክል ከባድ ቢሆን ተስፋህን በአምላክህ ላይ መጣልህን እንዳትረሳ፤ ምንም ያክል ህይወት ትርጉም ብታጣብህ አንድ ቀን ትርጉሟን እንደምታገኝ አስብ።

አዎ! በተስፋህ አትጨክን፤ ነገህን አታክብደው፤ ይበልጥ አታወሳስበው። ዛሬ ያልሆነው ነገ ይሆናል፤ ዛሬ ያልተሳካ ነገ ይሳካል፤ ዛሬ ያላስደሰትህ ነገ ያስደስትሃል፤ ዛሬ ብትታመም ነገ ትድናለህ፤ ዛሬ ብትከስር ነገ ታተርፋለህ። ህይወትህ ዛሬ እንደምታበቃ አታስብ። ዛሬ ባለህበት አጣብቂኝ አትቀጥልም፤ ዛሬ በሚሰማህ ስሜት ውስጥ ዘላለም አትኖርም። ተስፋህ ፋታ እንዲሰጥህ ፍቀድ፤ ነገን ማሰብ፣ መጪውን ጊዜ አርቆ መመልከት፣ የተሻለውን መጠበቅ እንዲያረጋጋህ ፍቀድ። ስለ አሁኑ ችግር ተጨንቀህ ምንም አታመጣም፤ ደጋግመህ በእሱ እየተብሰለሰልክ ምንም አትፈጥርም። ይልቅ ነገ መልካም እንደሚሆን አስብ፤ ነገ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ ተመልከት። በሚታይህ ብሩህ ቀን፣ በሚታይህ ስኬታማ ቀን አትደራደር። ምንም ቢቀሙህ ዝም ልትል ትችላለህ፣ በተስፋህ ሲመጡ ግን እምቢ ማለትን ልመድ። ብሩህ ነገን በተስፋ ጠብቅ፤ ዛሬን በሙላት ኑራት፤ አሁንን በሚገባ አጣጥም።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.2K views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 13:39:42 የህይወት አላማን የመፈለግና በአላማ የመኖርን ጉዞ ቀላልና አስደሳች ለማድረግ ይህን ቪድዮ ተመልከቱ! 

ፍላጎታችሁን ከግባችሁ ጋር አስማሙ
እሴቶቻችሁን ከምኞቶቻችሁ ጋር አዋህዱ
የተረጋጋና አስደሳች ህይወትንም በፍቅር ኑሩ።

LIKE COMMENT SUBSCRIBE SHARE




3.1K views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 07:21:34 ዛሬ ያ ቀን ነው!
፨፨፨//////፨፨፨
ዛሬ ያ ህይወት ቀያሪ ተግባራትን የምትፈፅምበት ቀን ነው፤ ዛሬ ያ ወደፊት እንደምትጓዝ እርግጠኛ የምትሆንበት ቀን ነው፤ ዛሬ በውሳኔዎችህ የምትኮራበት፣ እርምጃዎችህን የምታደንቅበት፣ እራስህን የምታበረታታበት፣ እራስህን በተለየ መንገድ የምትመለከትበት፣ ተስፋህን በብዙ እጥፍ የምትጨምርበት፣ የአምላክህን ድንቅ ተግባር የምትመለከትበት ቀን ነው። ለብዙ ጊዜ ይህን ቀን ጠብቀሀው ይሆናል፤ ከዛሬ ቦሃላ ግን ልትጠብቀው አትችልም። ምክንያቱም አሁን ተከስቶ አይተሀዋልና ነው። ሃሳብህን የምትኖርበት፣ ተግባርህን የምትፈፅምበት፣ ገና ከጅምሩ በድል የምትነሳበት ቀን ነው። የቀጠሮህ ብዛት ብዙ አያስኬድህም፤ እቅዶችህን ማሸጋገሩ፣ ውጥኖችህን መቀያየሩ ትርጉም አይሰጥህም። ወደፊት መጓዝ ካለብህ ትናንት ወይም ነገ ሳይሆን ዛሬ ትጀምራለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ ያ ቀን ነው! ከብዙ በጥቂቱ ለለውጥ የምትፋጠነው፣ የልብ መሻትህን፣ ምኞትህን ለማሳካት የምትነሳው፣ ከተለመደው ተግባርህ ዞር በማለት ትኩረትህን ወደምትፈልገው ተግባር የምታዞርበት፣ በሚያስደስተህ ምርጫ ፋታ የምትወስድበት፣ ጠዓሙን የምትለይበት፣ ቃናውን የምታጣጥምበት ዛሬ ያ ቀን ነው። ውድድሩ ይበቃሃል፤ የሌላውን እግር መከተሉ ይበቃሃል፤ ከማታውቀው ሰው ጋር አንገት ለአንገት መተናነቁ አይጠቅምህም። ዛሬ የእራስህን እቅድ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ የምታስኬድበት ቀን ነው። ዙሪያህን ትቃኛለህ ነገር ግን እራስህ ላይ ብቻ ታተኩራለህ፤ ለአከባቢህ ትርጉም ለመስጠት ትሞክራለህ፣ በዛው ልክ ለእራስህ ጊዜ ትሰጣለህ፤ እራስህን ታዳምጣለህ፤ ውስጥህን ታንፃለህ።

አዎ! ተፎካካሪ ስለበዛ የሚቆም ተግባር የለም፤ ጫና ውስጥ ስለገባህ ተስፋ የምትቆርጥበት ምክንያት አይኖርም፤ የተባልከውን ሳይሆን የሆንከውን እንደሆንክ ዛሬ ማሳየት ትጀምራለህ፤ ካሉህ ብዙ ነገሮች የትኛውን እንደምታስቀድም፣ ለየትኛው ይበልጥ ትርጉም እንደምትሰጥ ግልፅ ታደርጋለህ። ለረጅም ጊዜ ስታስብ ከነበረ፣ በተደጋጋሚ እቅድ እያወጣህ ከነበረ ዛሬ ሃሳብህን ወደ መሬት አውርደው፤ እቅድህን ፈፅም፤ ያንተ ስለሆነው ውሳኔህ አንድ ተጨባጭ ነገር አሳይ። የሚታዩ ነገሮች ብዙ ያደክማሉ፤ በጥረትህ ልክ እንዳትታይ ያደርጉሃል፤ እንዳሰብከው ለውጤት እንዳትበቃ ያግዱሃል። ችሎታው እንዳለህ፣ ብቃቱ እንደተሰጠህ ካመንክ ግን ከውጤቱ በላይ ያንተ ውስጣዊ ስሜት እንዲመራህ ማድረግ ትችላለህ። ዛሬ ይህን አድርገህ አሳልፍ፤ ለእውነተኛው ፍላጎትህ ታመን፤ ውስጣዊ ስሜትህን አክብር፤ የዘወትር ምኞትህን እውን ለማድረግ ትልቁን እርምጃ ውሰድ።
ግሩም ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.3K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ