Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-12 08:11:05 ለእድገታችሁና ለስኬታችሁ ይህን ሚስጥር በሚገባ ተረዱና ተግብሩት! 

LIKE COMMENT SUBSCRIBE SHARE




2.4K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 07:31:40 ድጋሜ አታገኘውም!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
ተሳስተህ የምትማረውን ትምህርት ድጋሜ አትማረውም፤ ያመለጠህን ጊዜ ድጋሜ አታገኘውም፤ በብዙ ጥረት የምታካብተውን ልምድ እንደገና አታገኘውም። ምድርን መሰናበቻህ ሲቀርብ ከምትነቃ አሁን በጊዜ ንቃ፤ ድጋሜ ለማታገኛቸው ስጦታዎችህ ትኩረት ስጣቸው፤ ውድነታቸውን ውድ ነገር በማድረግ ግለፅላቸው፤ ልብህን ለማሞቅ ቁጭ ብለህ መቆዘም ሳይሆን ተነስተህ የፈለከውን አድርግ። ሽልማት እያሰብክ እራስህን አታድክም፤ ቁስ ባትሸለም ውስጣዊ ሃሴትን የሚሸልምህ፣ የማያልቀውን ደስታ የሚያድልህ ተግባር ውስጥህ አለ። የምትናፍቀው ለውጥ፣ የምትመኘው ከፍታ፣ የምታስበው ስኬት በጥረትህ ልክ የሚመጣ ጉዳይ ነው። ተስፋን በብዙ ተንከባከበው፤ ለእምነትህ ድጋፍ ሁነው፤ የታላቅነት አመለካከትህን አጥብቀህ ያዘው፤ በእራስመተማመንህን ከምንም በላይ ዋጋ ስጠው፤ ዛሬህ ላይ በሚገባ ሰልጥን። ታሪክ ሆኖ በኩራት የምታወራበትን ቅፅበት አሁን መፍጠር ጀምር።

አዎ! ጀግናዬ..! ድጋሜ አታገኘውም፤ እንደገና አይመጣምና እያንዳንዱን የህይወት ስጦታህን፣ ቀንህን፣ ጤናህን፣ ሰላምህን፣ እውቀትህን፣ ጥበብህን፣ ማስተዋለህን፣ ብለሃትህን እንደ ብርቅ፣ አላቂና ውድ ነገር በአግባቡ ተጠቀመው። እንዲሁ እንደ ቀላል የሚባክን፣ ዋጋ የሌለው፣ ተስፋህን የማያጎላ፣ ለምኞትህ የማያቀርብህ ስጦታ እንደማይሰጥህ አስብ። በብረሃናማው ጊዜህ በሚገባ መኖር ከቻልክ ፀሃይህ መጥለቅ ስትጀምር፣ የድካም ዘመንህ ሲመጣ፣ ተፈጥሮ ስትሰለጥንብህ አንዳች የሚያስቆጭህ ነገር አይኖርም። የአሁኗን ቅፅበት ድጋሜ የመኖር እድል እንደማታገኝ መረዳትህ ብቻ በሙሉ ስስት እንድትጠቀማት ሊያደርግህ ይገባል።

አዎ! አስቸኳይ ሃላፊነት፣ ጊዜ የማይሰጥህ ተጠያቂነት፣ ድጋሜ የማይፈፀም ግዴታ እንዳለብህ አስታውስ። ህይወትን በሙላት የመኖር ሃላፊነት፣ መኖርህን ትርፋማ የማድረግ ግዴታ፣ ለእያንዳንዱ ቅፅበቶችህ፣ ለእያንዳንዱ ስጦታዎችህ ዋጋ የመስጠት፣ ትርጉም የመፈለግ ተጠያቂነት አለብህ። የሚጠይቅህም ሌላ ማንም ሳይሆን የእራስህ እውነተኛ ማንነት፣ ውስጥህን በሃሴት ለመሙላት፣ ከፍታህን ለማምጣት የሚታገለው ድንቁ ማንነትህ ነው። ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በየትኛውም መንገድ ሊደረግ ይገባል። መጨረሻህ ቁጪት፣ ስቃይና የልብ ስብራት እንዲሆን ካልፈለክ አሁን ነቃ በል፤ ህይወትህን ሙሉ አድርጋት፤ በእያንዳንዱ ቀናት ውስጥ በመኖርህ፣ የእራስ ፍለጋ ጉዞ ውስጥ በመሆንህ፣ እራስህን ለማሳደግ በመጣርህ በእርግጥም ኩራት ይሰማህ፤ በምርጫህና በውሳኔህ ሃሴት አድርግ፤ በማንነትህ ሁሌም ደስ ይበልህ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.2K views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 07:30:57
1.9K views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 20:52:35 የሆነ ቦታ ይኖራል!
፨፨፨//////////፨፨፨
አዎ! የሆነ ቦታ በእራስመተማመንህ የመጨረሻ ምርጫህ ይሆናል፤ የሆነ ቦታ ጨክኖ መጀመር ብቸኛው እድልህ ይሆናል፤ የሆነ ቦታ እራስህን ከማገዝ ውጪ አማራጭ አይሆኖርህም። አንዳንድ ሁኔታዎች የተቀበረ ማንነትን ይገልጣሉ፤ እውነተኛ አቅምን ያሳያሉ፤ ልኬትን እስከ ጥግ ያስመለክታሉ። በጨለማ መከበብህ ብረሃንን አጥብቀህ እንድትፈልግ ያደርግሃል፤ በስራህ ደስተኛ አለመሆንህ አስደሳቹን ስራ እንድተፈልግ ያደርግሃል፤ ደጋግመህ መውደቅህ የውድቀትህን መንስኤ በጥልቀት እንድትመረምር ይገፋፋሃል። ማደግ ለሚፈልግ ሰው አማራጭ ከማጣት የተሻለ የሚያሳድገው ነገር አይኖርም። ይህን ሁኔታ ወስኖ የሚገባበት ደግሞ እርሱ ሁሌም ቢሆን የህይወቱ ጀግና፣ አዲስ ምዕራፍ ፈንጣቂና የህይወቱ ብርቱ መሪ የሆነ ሰው ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! የሆነ ቦታ ይኖራል፤ ጦርነትህ የማያበቃበት፣ ስቃይህ የማይቋጭበት፣ ችግርህ የማይፈታበት፣ መሰናክልህ የሚከብድበት፣ የተሸከሙህ እግሮች የሚብረከረኩበት፣ በእራስመተማመንህ የሚክድህ ጊዜ ይኖራል። በዛን ጊዜ ብቸኛው አማራጭህ ጦርነቱን ማሸነፍ ነው፤ ስቃይህን ማለፍ ነው፤ ችግርህን መፍታት ነው፤ መሰናክልህን ማለፍ፣ በእራስመተማመንህን ድጋሜ ማግኘት ብቻ ይሆናል። የትም ልትሔድ ትችላለህ፣ ለየትኛውም ትልቅ መዳረሻ እራስህን ልታዘጋጅ ትችላለህ፤ ነገር ግን በየትኛውም መመዘኛ ውድቀትህን እያሰብክ ለእርሱም አማራጭ እያስቀመጥክ የምትጓዝ ከሆነ ከውድቀትም በላይ ድጋሜ ለማገገም እስከምትቸገር ድረስ መውደቅህ አይቀርም።

አዎ! በጉዞ መሃል አደጋ ይኖራል፤ ለዛም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ጥንቃቄው ግን እንደ አማራጭ የሚያዝ ሳይሆን የአደጋው መቀልበሻ ብቻ ሆኖ ሊታሰብ ይገባል። አማራጭ ማስቀመጥ፣ ተለዋጭ መንገድ ማማተር፣ የትኩረት አቅጣጫን ማብዛት የፍረሃት መንገድ ነው። መውደቅ ካለብህ ትወድቃለህ፣ ድጋሜ መነሳት ደግሞ ብቸኛው አማራጭህ ይሆናል፤ አሰራርህ የሚያከስርህ ከሆነ ትከስራለህ፣ ለትርፋማነትህ ብለህ አሰራርህን ድጋሜ መመርመር ደግሞ ብቸኛው አማራጭህ ይሆናል፤ ሰዎቹ ባህሪያቸው ከሆነ ትከዳለህ፣ ለእራስህ መታመን ደግሞ ዋነኛው ከእነርሱ የምትማረው ትምህርት ይሆናል። ምርጫ በማጣት ውስጥ እድገትን አስተውል፤ በችግር መዋጥ መሃል ችግር ፈቺነትን በአስተውሎት ተመልከት። አማራጭ የለኝም ባልክበት ቅፅበት አዎንታዊውን አማራጭ ለመምረጥ ደፋር ሁን።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.4K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:43:12
ሰላም ውድ ቤተሰቦች እንዴት አመሻችሁ?

ነገ (ሰኞ) ጠዋት 2:00 ሰዓት በድንቁ መፅሃፍ THE ALCHEMIST ደራሲ Paulo Coelho ምርጥ አባባል መነሻነት ለመልካም ህይወታችን ስንቅ የሚሆን ጉዳይ ላይ እንወያያለን።
የነገ ሰው ይበለን!

ከወዲሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ቻናላችንን
SUBSCRIBE በማድረግና
የደውል ምልክቱን በማብራት ይጠብቁን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube LINK!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.5K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 07:11:43 አምላክህን ተመልከተው!
፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨
ምድር ድንቅ ነች፣ ብዙ ታሳያለች፣ ብዙ ታስመለክታለች። ከመልካምነት ጥግ እስከ ጭካኔ ጫፍ ብዙ ሆኗል፣ ብዙ እየሆነ ነው፤ ብዙም ተከናውኗል። በዚህ ሁሉ መሃል ግን እግዚአብሔር ነበረ፣ አምላክ ያይ ነበረ። በበጎዎቹ በሃል ሲመላለስ፣ ክፉዎቹም እስኪመለሱ እየጠበቀ ከአጠገባቸው ነበረ። ዛሬም እንደ አምናው እንደ ካቻምናው እንደ ትናንቱ እግዚአብሔር አብሮን አለ፤ ፈጣሪ በእኛ ውስጥም በዙሪያችንም አለ። ማስተዋል አለመቻላችን አለመኖሩን አያመላክትም፤ ልንፈልገው ፍላጎት ማጣታችን ህልውናውን አይከልለውም፤ መኖሩን አያደበዝዘውም፤ ስሙን አይሽረውም፤ ስራውን አያጠለሸውም። እግዚአብሔር በብዛት፣ ቸሩ አምላክ በመትረፍረፍ ነበረ፣ ዛሬም እንዲሁ በረቂቅ መገለፁ፣ በማራኪ ባህሪያቱ፣ በአስደናቂ ስራዎቹ አለ። የምናየውን መምረጥ ተስኖን፣ የሚገባንን ረስተን፣ መገለጫው ጠፍቶን እንጂ የአምላክ መኖሪያ በሁሉም ቦታ፣ በሁሉም ውስጥ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! አምላክህን ተመልከት! በተዓምራቱ የሚያኖርህ አምላክ፣ በድንቅ ስራው የሚባርክ ጌታ፣ ዘወትር በመግቦቱ የሚያኖርህ ፈጣሪ ደጋግሞ ደጅ እየጠናህ፣ እየፈለገህ፣ እርሱም በምትኩ እየተማፀነህ፣ ሰጪ ሆኖ ምፁአትን ካንተ እየፈለገ ነውና እግዚአብሔርን ተመልከተው፤ ፈጣሪህን አስታውሰው። ስንቶች በደጃፍህ ላይ ወድቀዋል? ስንቶች ውስጣቸው ቆስሏል? ስንቶችስ ግፍ ተፈፅሞባቸዋል? ስንቶች በእንባ ይማፀናሉ? ስንቶች አንገታቸውን ደፉ? ስንቶችስ አበርታችና ደጋፊ አጡ? እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር መገለጫዎች፣ የአምላክ ተምሳሌቶች ናቸው። እነርሱን ስታስታውስ አምላክህን ታስታውሳለህ፣ እነርሱን ስትመለከት አምላክህን ትመለከታለህ፣ ችግራቸውን መካፈል፣ ሰቃያቸውን ማቅለል ስታስብ ፈጣሪህ ለዚህ በጎ ተግባር እንደ መረጠህ ትገነዘባለህ።

አዎ! "ተርቤ አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም" ከመባል እራሳችንን የምንጠብቀው ደጃፋችንን በመቃኘት፣ ዙሪያችንን በመመልከት፣ ለወገናችን በመድረስ ነው። ውስጥህ ያለውን አምላክ በብዙ ባትረዳውም ውጪ ላይ ሊያስተምርህ የመጣውን፣ ሊባርክህ የሚጠራህን፣ ሊደግፍህ የሚማፀንህን ፈጣሪ ተመልከት። ምልከታህም በልብ እንጂ በዓይን ብቻ አይሁን፤ ለጊዜው ብቻ ሳይሆን እስከ መጨረሻው ነው። አምላካቸውን የተመለከቱ አይኖች፣ በፍቃዱ የሚገዙ ነፍሳት፣ በቃሉ የሚመሩ እግሮች፣ በስራው የሚባረኩ ፍጡራን እንዴት ብፁዓን ነቸው? እንዴትስ የተመረጡና የተወደዱ ናቸው? የሚችለው አምላክ ከነኀጢያታችን፣ ከእነክፋታችን፣ ከእነጭካኔያችን ለዘመናት ችሎናል፤ ሲጠብቀን ኖሯል፤ በምህረቱ ጎብኝቶናል፤ ከስራችን በላይ እኛን አስቀድሟል። ምስጋናውን ከማቅረብ በላይ ልባችንን እንመልስ፣ እርሱን እንመልከት፤ ውስጣችንን በቃሉ እናድስ፣ በህያው መንፈሱ እንታነፅ ሃሴትንም እናድርግ።
ምስጋናው ይቀጥል፤ ምህረቱም ይለምልም!
ብሩክ ቅዱስ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.1K views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 07:11:19
2.5K views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 22:35:54
የራሳችንና የሌሎችን ሳይኮሎጂ በመረዳት ስብዕናችንን የምናሳድግበት አስተማሪ እና ማራኪ የሆነ የሳይኮሎጂ ቻናል !! ተቀላቀሉን ትወዱታላችሁ

የኛ ሳይኮሎጂ

JOIN US

@yegna_psychology
@yegna_psychology
@yegna_psychology
@yegna_psychology
@yegna_psychology
632 views19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:55:29 ተዓምሩ ይቀጥል!
፨፨፨//////////፨፨፨
እልባት ያላገኙ ብዙ ጉዳዮች ይኖራሉ፣ ተዓምራቱ ግን ይቀጥል። የማይታወቁ፣ ጊዜ የሚፈልጉ፣ ያልተፈቱ እንቆቅልሾች ይኖራሉ፣ እነርሱ ቢኖሩም ግን ተዓምራቱ ይቀጥል። ፋታ የማይሰጡ፣ በየጊዜው የሚደራረቡ የህይወት ሸክሞች አይጠፉም፣ ቢሆንም አሁንም ተዓምሩ ይቀጥል። ትኩረት ያልተሰጣቸው ነገር ግን እያደር እየሸረሸሩን የሚሄዱ ነገሮች ይኖራሉ፣ በዚህም መሐል ቢሆን ግን ተዓምሩ ይቀጥል። ሁይወትን በስስት የመኖር ተዓምር፣ እያንዳንዱን ቅፅበታት የማጣጣም ተዓምር፣ ከምናውቀው ከእራሳችን በላይ የመኖር ተዓምር፣ ከሰማነው፣ ካየነው በተለየ የመበርታት ተዓምር። ሸክምህ ምንም ሊሆን ይችላል፣ ጭንቀትህ ምንም ሊሆን ይችላል፣ የሚያሳስብህ፣ እንቅልፍ የሚነሳህ፣ መልስ ያላገኘህለት፣ እያደር አዲስ የሚሆንብህ ጉዳይ ይኖራል ነገር ግን ከመኖርህ፣ በህይወት ከመቆየትህና እለት እለት በምድር ከመመላለስህ ሊበልጥ አይችልም።

አዎ! ጀግናዬ..! ተዓምሩ ይቀጥል! ከፈተናዎችህ ጋርም ቢሆን በህይወት ስላለህ ብቻ የምትሰራቸው ተዓምራት ይቀጥሉ፣ ሸክምህ እንዳለ ሆኖ የምትሰራቸው አስደናቂ ተግባራት ይቀጥሉ፤ ማሰብ መብሰልሰልህ እንደተጠበቀ ሆኖ አንተም ህይወትህን መኖርህ ቀጥል። ባልተፈቱ ችግሮችህ ምክንያት ህይወትህ አንድ ቦታ መቆም የለበትም፤ ባልተፈታልህ እንቆቅልሽ ምክንያት ኑሮህን መግታት አይጠበቅብህም፤ ከአንተ አቅም በላይ በሆነ ጉዳይ ዘወትር እየተብሰለሰልክ መቀጠል የለብህም። መፍትሔ የሌለው ጉዳይ ባይኖርም ጊዜው እስኪደርስ ግን ያንተም ህይወት መቀጠል ይኖርበታል። ድፍረትህ አሸናፊ እንደሚያደርግህ አስታውስ፤ ቆራጥነትህ ችግሮችህን አሽቀንጥሮ እንደሚጥል ተገንዘብ። ባንተ ህይወት የመጣ ጉዳይ በቅድሚያ በአምላክህና ባንተ ሃይል ብቻ እንደሚፈታ እወቅ።

አዎ! ህይወትህ አንተ ባልፈፀምከው ጀብድ፣ አንተ ባላደረከው ተዓምር፣ አንተ ባልተጋፈጥከው ከባድ ነገር ይስተካከላል ብለህ አትጠብቅ። ምንም ያህል ከባድ ነገር ቢገጥምህ ክብደቱን መረዳት የምትችለው አንተ ብቻ ነህ፤ ስታወርደውም የነፃነቱን ጠዓም፣ የቅለቱን ስሜት የምትገነዘበው አንተ ነህ። ማንም ያልበላውን ሊያክ ይችላል ያልታመመውን ግን መታከም አይችልም። ምክንያቱም ቢታከምም ሌላ በሽታ መሸመቱ አይቀርምና ነው። በጊዜ ሂደት ወደፊት በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ የሚስተካከሉ ነገሮች ይኖራሉና ለጊዜው ግን አሁን ላይ መገኘትን ተለማመድ፣ አሁን መኖርን ምረጥ፣ ከአሁን ጋር መጣበቅን ተለማመድ። ችግሮችህን ስታስብ የሚያመልጡህን አስደሳች ሁነቶች አስተውል፤ አስጨናዊዎችህን ስታስታምም ስጦታዎችህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ። የሆነው ከባድ ነገር ከሆነ፣ መሆን የሚገባው ሌላ አስደሳች ነገር ይኖራልና እርሱ ላይ አተኩር፤ በሂደትም የምትመኘውን ተዓምር ፍጠር።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
1.2K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 07:30:44 ለዛሬ ተቆጠቡ!
፨፨፨//////፨፨፨
ለዛሬ ተቆጠቡ እራሳችሁን ቆጥቡ፤ ነገሮች ላይ ጠንቃቃ ለመሆን ሞክሩ፤ ከተለመደው አድካሚ ውሎ ፋታ ውሰዱ፤ ከሚያሳስበችሁ ብሎም ከሚያስጨንቃችሁ ጉዳይ ገለል በሉ፤ እራሳችሁን ያዝ፣ ጠበቅ፣ ቆንጠጥ አድርጉት። የሁልጊዜ ሩጫችሁ ውጫዊ እይታን ለማግኘት ከሆነ ወደ እራሳችሁ ተመለሱ፤ የዘወትር ፀሎታችሁ ከሰው በታች ላለመሆን ከሆነ ከዛ በላይ ብቁ መሆን፣ ትርፋማ መሆን፣ እሴት መጨመር ላይ አተኩሩ። በምርጫችሁ ጎዳና ላይ በተለየ ብርታት ስለሚያስቀምጣችሁ፤ አዲስ ልዩ ብሩህ ውሎን ስለሚያድላችሁ፤ እድገታችሁን እንድትመለከቱ ስለሚያደርጋችሁ፣ ዋጋችሁን እንድትጨምሩና እንድታድጉ ስለሚያስችላችሁ በየጊዜው በፍቅር ለሚታደሏችሁ ቀናት ደስ ይበላችሁ።

አዎ! ጀግናዬ..! ለዛሬ ተቆጠብ! ለዘመናት አይተህ፣ ለረጅም ጊዜ ተከትለህ፣ ለጊዜያት አስበሀው ካልቀየረህ፣ እሴት ካልጨመረልህ፣ ዋጋህን ከፍ ካላደረገልህ ሰውና ጉዳይ እራስን ቆጥብ። ቁጠባ ጨርሶ እንደመተው አይደለም። እንደ ቀድሞ ሙሉ በሙሉ ማይጠቅሙ ነገሮች ውስጥ ተዘፍቆ ማስተዋልን ከማጣት ይልቅ በቅርብ ርቀት ሆኖ ነገሩን በአንክሮ መመልከት፣ በጥልቀት ማጥናትና በተለየ መንገድ መረዳት ነው። ቁጥብነት ያስከብራል፤ ቁጥብነት ጥንቃቄን ያላብሳል፤ ስሜታዊነትን ያስታግሳል፤ በሰዎች ዘንድ የተለየ ስፍራን ያሰጣል፤ ዋጋን ይጨምራል፤ ለመመርመር እድል ይሰጣል። እራስን መግዛት፣ እራስ ላይ መሰልጠን በጭፍን ከመነዳት፣ በጭፍን ከመፍረድ፣ በጭፍን ከመኮነን ይታደጋል።

አዎ! ዛሬ ለፍላጎትህ የምትቆምበት፣ ለውስጣዊ እርካታህ ቅድሚያ የምትሰጥበት፣ በማንም በጭፍን ከመነዳት የምትወዳውንና የሚያስፈልግህን የምትመርጥበት ቀን ነው። ጨከን ማለትን ተለማመድ፤ ከባዱን መንገድ ለመምረጥ እራስህን አዘጋጅ፤ አውቀህ ለመፈተን፣ በተለየ አቅጣጫ ለመጓዝ፤ እራስህ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እራስህን አደፋፍር። ጥራት ያለው፣ የተረጋጋ፣ በአንድ አቅጣጫ የሚጓዝ፣ ትርፋማና አስደሳች ህይወትን ስለመምራት ማሰብ ጀምር። የእስካሁኑ ሩጫህ ካልቀየረህ፣ የእስካሁኑ ድካምና ልፋትህ ስሜት ካልሰጠህ ቆም ብለህ እራስህን ጠይቅ፤ ምን እንደጎደለህ እወቅ፤ ለምን እንደሆነ ተረዳ። የምትለወጠውና የምታድገው ያለማቋረጥ ስለሮጥክ፣ ጠንክረህ ስለሰራህ፣ ያለእረፍት ስለደከምክ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ጠንክረህ ስላሰብክ፣ አስተውለህ ስለምትራመድና በየጊዜው እራስህን ስለምትመዝን እንደሆነ ተረዳ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.7K views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ