Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @yegna_psychology
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.15K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ አስተሳሰባችንን የሚያሳድጉ የሳይኮሎጂ እና የፓለቲካ ፅሁፎች ይቀርቡበታል።
የኛ ሳይኮሎጂ ይተነተናል እንዲሁም ታዋቂ የሥነ-ልቦና ሊሂቃን (theory) ይዳሰሳል።
🌟ማሳሰብያ ለውድ ተከተዮቻችን:➪አባላትን ለማብዛት በምናደርገው #የማስታወቂያ ልውውጦች እንዳትሰላቹብን ለማለት እንወዳለን።

[ ራሳችንን በመቀየር ድርሻችንን እንወጣ! ]

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-28 21:28:22 የሰው ልጅ ጠቢብ  ባልሆነ ቁጥር የአፈጣጠሩ ሚስጢራዊነት ብዙም አይታየውም!
     
-- Arthur Scopenhauer --
5.7K viewsABDU, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 19:29:18 The shortest Answer is just Doing it!!

“Are you jealous of the ocean’s generosity?
Why would you refuse to give?
This love to anyone?
Fish don’t hold the sacred liquid in Cups!
They swim the huge freedom.”
- Rumi

ከነፃነት ባህር ውስጥ የወጣ ማንኛውም ነገር እድሜው በአጭሩ ይቀጫል።ሩሚ በግጥሙ እንዳለው አሳ ከውሃ በላይ የሚወደው ነገር የለም፤በውሃ ውስጥ ይኖራል እንጂ ውሃውን ስለሚወደው በእቃ ቆጥቦ አያኖረውም።እኛም በፍቅር ውስጥ በነፃነት መዋኘት እስካልቻልን ድረስ ጣዕሙን አናውቀውም።

ፍቅርን ስንቆጥበውና ስንሰስተው ትንፋሽ ያሳጥረናል።አንድ አሳ ውሃ በገንዳ ስላጠራቀመ ብቻ በህይወት አይሰነብትም፤በውሃው ውስጥ እስካልዋኘበት ድረስ ።እኛም ስለፍቅር ብዙ ስለሰማንና ስላወቅን ብቻ አንረካም፤በውስጡ እስካልዋኘን ድረስ።

ስለ ሰላምና ስለፍቅር፤ስለ እውነተና ስለ ፍትህ፤ስለ ይቅርታና ደስታ፤ ስለመልካም ነገሮች በሙሉ ከበቂ በላይ እውቀቱ አለን።እውቀቱ አለን እንጂ በምናውቀው ነገር ውስጥ አንዋኝበትም።

ማወቅና የሚያውቁትን መኖር የሰማይና ምድር ያህል ልዩነት አላቸው። አውቀን ከማንኖረው ይልቅ ሳያውቁ የሚኖሩት በጣም የታደሉ ናቸው።ማወቅ እና በሚያውቁት ውስጥ መኖር ለእኛ ለሰዎች ሁሌም ግራ ያጋባናል።ውሃ ማጠራቀምና በውሃው ውስጥ መዋኘት ልዩነት እንዳላቸው እንደማናውቅ ሁሉ።

"Don't try to understand life.
Just Live it! Don't try to understand love. Move into love. Then you will know -
and all that knowing will come out of your experiencing. The more you know, the more you knowthat much remains to be known.Osho

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!
#share and #join for more
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha
6.7K views€£phâ (SânTos), 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 21:14:20 እውነት ልክ እንደአንበሳ ነው። ልትመክተው አትችልም ። ተሸነፍለት ራሱ መከታ ይሆንሃል!
-- Saint Augustine --
7.6K viewsABDU, edited  18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 22:34:13 ፍቅር ስለሚጠይቀው መስዋእትነት ካህሊል ጂብራን የፃፈውን ውብ እና ነፍስን የሚማርክ ፁሁፍ ልጋብዛችው

" ፍቅር በዓይኑ ጥቅሻ በጠራችሁ ጊዜ መንገዶቹ ምን ያህል አስቸጋሪ እና አቀበት ቢሆኑም ተከተሉት...ክንፎቹ ሲያቅፏችሁም ተሸጎጡበት ። በላባዎቹ መሀል የተደበቁ ሰይፎች ቢያቆስሏችሁም ወደኋላ አታፈግፍጉ ...

ሲያነጋግራችሁም እመኑት ። ድምፁ የሰሜን ኃይለኛ ንፋስ የአትክልትን ስፍራ እንደሚያወድም ሁሉ ህልሞቻችሁን ቢበታትንባችሁም እሱን ከማመን አታመንቱ..

ፍቅር ዘውድ የሚደፋላችሁን ያህል ይሰቅላችሁም ይሆናል ። የሚያሳድጋችሁንም ያህል ይከረክማችኋልም...እስከ ጫፍ ከፍ ብሎ በፀሃይ ውስጥ የሚወዛወዙትን እጅግ ለስላሳ ቅርንጫፎቻችሁን በፍቅር እንደሚደባብስ ሁሉ ፣ በመሬት ውስጥ ቁልቁል ወደ ስሮቻችሁ ወርዶም ተጠምጥሞ ከመሰረታቸው ይነቀንቃቸዋል..

እንደ በቆሎ ክምር ወደ ራሱ ይሰበስባችኋል ። እርቃናችሁን ሊያስቀራችሁም ይወቃችኋል ። ከላፋችሁ ሊያላቅቃችሁም ይነፋችኋል ። ነጭ ዱቄት እስክትሆኑም ድረስ ይፈጫችኋል ። እስክትለወጡም ያቦካችኋል ። ከዚያ ለአምላክ ቅዱስ ድግስ የምትቆረሱ ቅዱስ ዳቦዎች ትሆኑ ዘንድ ወደ ተቀደሰው እሳቱ ውስጥ ይጨምራችኋል....

ፍቅር እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያደርግባችሁ ፣ የልባችሁን ምስጢራት እንድታውቁ እና በዚያ ዕውቀትም የህይወት ልብ አንድ ግማድ እንድትሆኑ ነው...

፧ ይሁንና ፍርሃት አድሮባችሁ የፍቅርን ሰላም እና የፍቅርን ደስታ ብቻ የምትሹ ከሆነ፣ እርቃናችሁን ሸፍናችሁ ከፍቅር የመውቂያ ውድማ ወጥታችሁ ብትሄዱ ይሻላችኋል ። ወደዚያ የሄዳችሁበት ወቅቶች የማይፈራረቁበት ወቅት - አልባ ዓለም ውስጥም ትስቃላችሁ ። ነገር ግን ሳቃችሁን ሁሉ አትስቁትም ። ታላቅሳላችሁም፤ ግን እንባችሁን ሁሉ አታፈሱትም::

ደራሲ ካህሊል ጂብራን
ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!

#share and #join for more
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha
1.2K views€£phâ (SânTos), 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 07:03:46 ህፃናት ከምናስተምራቸው ይልቅ ከማንነታችን ብዙ ይማራሉ!
-- W. E. B du Bois
1.8K viewsABDU, edited  04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 22:40:49 እየተዋሸህ ነው!!

#እየተዋሸህ ነው፣ በተከታታይ፣ አንዳንዴ በራስህ አሉታዊ ሃሳብ፣ ሌላ ጊዜ በሰዎች ትክክል ያልሆነ ሃሳብ። ሁላችንም በማያልቅ የሐሰት መረጃ እየተነዳን ነው። እነዚህ ስለራስህ ያሉ ውሱን ሃሳቦች ውሸት ናቸው። ጂም ኪዊክ እነዚህን አስተሳሰቦች LIEs(Limited Ideas Entertained) ይላቸዋል።

*ካሮል ድዌክ በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሥነልቦና ፕሮፌሰር በቋሚና ለማሻሻል የሚቻል ዕውቀት ያለውን ልዩነት ስታስረዳ ችሎታዎቻችን በልምምድ ከፍ ሊሉ የሚችሉ እንጂ እንደአንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ተቀርፆ የተሰጡን አይደሉም። ማንኛውም ሯጭ ልምምድ በማድረግ ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚችል ሁሉ የአዕምሯዊው ችሎታችን በትምህርት፣ በልምምድና በጥረት ከፍ ማድረግ የሚቻል ነው።

#ውሸት ቁጥር 1: አዕምሮአዊ ዕውቀት ቋሚ እንጂ ማሻሻል የማይቻል ነው።

*ውሸት ቁጥር 2: የአዕምሮአችንን ፲ ከመቶ ብቻ ነው መጠቀም የምንችለው።

#ውሸት ቁጥር 3: ስህተቶች ውድቀቶች ናቸው።

*ውሸት ቁጥር 4: ዕውቀት ሃይል ነው።

#ውሸት ቁጥር 5: አዳዲስ ነገሮችን መማር አስቸጋሪ ነው።

*ውሸት ቁጥር 6: የሌሎች ሰዎች ነቀፋ ተፅዕኖ ሊያሳድርብን ይገባል።

#ውሸት ቁጥር 7: ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ሰዎች ይወለዳሉ እንጂ በልምምድና በጥናት አይመጡም።
ከ Limitless መጽሐፍ የተወሰደ
(Jim Kiwik) ፣ ትርጉም: ቃለአብ ተክሌ

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!
#share and join for more

@KenibabDaricha
@KenibabDaricha
1.6K views€£phâ (SânTos), 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 22:14:11 ስለ ፍቅር !

" በቦታም ሆነ በጊዜ አውታር የማይለካ፣ በሁሉም ስፍራና ጊዜ የሚኖር፣ የግራቪቲን ሕግ የሚደመስስ ክስተት አለ፣ እሱም" ፍቅር"ብቻ ነው።"
ኦሾ

"ፍቅር ከሚነደው የነፍስ ጉድጓድ በመመንጨት ምድሪቱን በብርሃን የሚሞላ አስማታዊ ጨረር ነው፡፡ፍቅር ሰው የአምላኩን ሀይል እንዲያይ የሚያስችለው ሰማያዊ ዕውቀት ነው፡፡"
ካህሊል ጂብራን

"በጥበብ ማፍቀርን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ ምንም ካለማፍቀር ግን በሞኝነትም ቢሆን ማፍቀሩ ይመረጣል"
ዊልያም ኤልቪስ

"በህይወት ውስጥ ካሉ ነገሮች ሞትን በብቸኝነት ሊያሸንፈው የሚችለው ነገር ፍቅር ብቻ ነው፡፡"
ኦሾ

"ፍቅር የተሟላ ህግ ነው።"
-ቅዱስ ጳውሎስ

" እርጅና ሁሉ በአንድ ውስጥ ቢታወር ከማፍቀር አያስጥልህም ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ፍቅር ከእርጅና ያስጥልሀል።"
ጂያን ሞሬታ

"ያልበሰለ ፍቅር ‹አፈቅርሻለሁ ምክንያቱም ታስፈልጊኛለሽ› ይላል የበሰለ ፍቅር ደግሞ ‹ታስፈልጊኛለሽ ምክንያቱም አፈቅርሻለሁ› ይላል"
~ኤሪች ፍሮም~

" በፍቅር ብትወድቁ፣ የመሬት ስበት ተጠያቂ አይደለም፤"
አልበርት አንስታይን

"ፍቅር ያዘኝ ማለት በጣም ቀላል ነዉ.. በፍቅር ዉስጥ መቆየት ግን ልዩ መሆንን ይጠይቃል፡፡"
ፌቡ~

"ፍቅር ራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም ፤ ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም ምንም አይቀበልም፤ ፍቅር ለፍቅር በቂ ነውና!! ፍቅር ምንም ንብረት የለውም፣ የማንም ንብረት ሊሆንም አይችልም።"
ካህሊል ጂብራን
ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!

#share and join for more
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha
1.1K views€£phâ (SânTos), 19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 22:15:45 ዛሬ የምጋብዛችሁ ቻናል ከ10 በላይ ምሁራን ያሉበት ድንቅ ቻናል ነው።

በየቀኑ በማይጠገቡ ምክሮቻቸው እየመከሩ ለቀጣዩ የህይወት ገፆችህ መሰረት ለመሆን ዝግጁ ሆነው እየጠበቁህ ይገኛሉ። ከእናንተ የሚጠበቀው "እለወጣለው" ብሎ ማመን ብቻ ነው።

ይቀለቀሉ
Join Now
@MentalCounsel
@MentalCounsel
@MentalCounsel
757 views€£phâ (SânTos), 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 14:52:34 ከፍልስፍና አምዶች

"የጅረቶች ብዛትና የዝናብ መዓት የውቅያኖስ ጣዕም እንደማይበርዙት ሁሉ የመከራ ውርጅብኝም የቆራጥ ሰው ህሊናን በድን አያደርገውም እንዲህ ያለ ሰው የህያውነት ሚዛኑን ይጠብቃልና። "
ሴኒካ

"የደስታ ምንጭ የምትሞላውና ሳታቋርጥ የምትፈሰው ከውስጣችን በሚፈልቁ ብሩህ አስተሳሰቦችና ስሜቶች ነው።"
ዊሊያም ላዩምፊሊፕስ

"ቅንዓት ሲመገብ ያደገ ፍቅር አሟሟቱ ከባድ ነው።"
ላቭስ ኩዩር

‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ
አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን

በገንዘብህ የጥቅም ጓደኞችን ልታፈራ ትችላለህ በውበትህ የስሜት ጓደኞች ልታፈራ ትችላለህ በእምነትህና በስነምግባርህ ግን..
የህይወት ጓደኞችን ታፈራለህ።


"ህይወት ጨካኝ መምህር ነው!!! ምክንያቱም መምህር አስተምሮ ነው የሚፈትነው ህይወት ግን ፈትኖ ነው የሚያስተምረው።"
ስብሃት ገ/እግዚአብሔር

የራስህን የህይወት እቅድ ዲዛይን ካላደረግክ ዕጣ ፈንታህ የሚሆነው በሌሎች እቅድ ውስጥ መኖር/መውደቅ ይሆናል።
- ጂም ሮን

የወደፊቱን ለመተንበይ የተሻለው ዘዴ፤ ወደፊትን መፍጠር ነው።
- አለን ኬይ

ከጌታዬ ሶስት ነገሮችን አጥብቄ እፈልጋለሁ አንድ ጥበብ ሁለት ጥንካሬ ሦሥት ፍቅር። ከነዚህ ከሦስቱ የበለጠ የምሻው ግን ፍቅርን ነው።ፍቅር ሲኖረኝ  ሁሉም ነገር አለኝ ነፃነትም ቢሆን "
ማርቲን ሉተር ኪንግ

"ልብህ ይናገር ዘንድ ምላስህ ዝም ይበል። እግዚአበሔር ይናገር ዘንድ ደግሞ ልብህ ዝም ይበል።"
አባራሀኒ

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!
#share and join for more

@KenibabDaricha @KenibabDaricha
1.5K views€£phâ (SânTos), 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 21:56:13
ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት  10 ምልክቶች እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተሽ ተመልከቻ
1.1K views€£phâ (SânTos), 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ