Get Mystery Box with random crypto!

The shortest Answer is just Doing it!! “Are you jealous of t | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

The shortest Answer is just Doing it!!

“Are you jealous of the ocean’s generosity?
Why would you refuse to give?
This love to anyone?
Fish don’t hold the sacred liquid in Cups!
They swim the huge freedom.”
- Rumi

ከነፃነት ባህር ውስጥ የወጣ ማንኛውም ነገር እድሜው በአጭሩ ይቀጫል።ሩሚ በግጥሙ እንዳለው አሳ ከውሃ በላይ የሚወደው ነገር የለም፤በውሃ ውስጥ ይኖራል እንጂ ውሃውን ስለሚወደው በእቃ ቆጥቦ አያኖረውም።እኛም በፍቅር ውስጥ በነፃነት መዋኘት እስካልቻልን ድረስ ጣዕሙን አናውቀውም።

ፍቅርን ስንቆጥበውና ስንሰስተው ትንፋሽ ያሳጥረናል።አንድ አሳ ውሃ በገንዳ ስላጠራቀመ ብቻ በህይወት አይሰነብትም፤በውሃው ውስጥ እስካልዋኘበት ድረስ ።እኛም ስለፍቅር ብዙ ስለሰማንና ስላወቅን ብቻ አንረካም፤በውስጡ እስካልዋኘን ድረስ።

ስለ ሰላምና ስለፍቅር፤ስለ እውነተና ስለ ፍትህ፤ስለ ይቅርታና ደስታ፤ ስለመልካም ነገሮች በሙሉ ከበቂ በላይ እውቀቱ አለን።እውቀቱ አለን እንጂ በምናውቀው ነገር ውስጥ አንዋኝበትም።

ማወቅና የሚያውቁትን መኖር የሰማይና ምድር ያህል ልዩነት አላቸው። አውቀን ከማንኖረው ይልቅ ሳያውቁ የሚኖሩት በጣም የታደሉ ናቸው።ማወቅ እና በሚያውቁት ውስጥ መኖር ለእኛ ለሰዎች ሁሌም ግራ ያጋባናል።ውሃ ማጠራቀምና በውሃው ውስጥ መዋኘት ልዩነት እንዳላቸው እንደማናውቅ ሁሉ።

"Don't try to understand life.
Just Live it! Don't try to understand love. Move into love. Then you will know -
and all that knowing will come out of your experiencing. The more you know, the more you knowthat much remains to be known.Osho

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!
#share and #join for more
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha