Get Mystery Box with random crypto!

እየተዋሸህ ነው!! #እየተዋሸህ ነው፣ በተከታታይ፣ አንዳንዴ በራስህ አሉታዊ ሃሳብ፣ ሌላ ጊዜ በሰ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

እየተዋሸህ ነው!!

#እየተዋሸህ ነው፣ በተከታታይ፣ አንዳንዴ በራስህ አሉታዊ ሃሳብ፣ ሌላ ጊዜ በሰዎች ትክክል ያልሆነ ሃሳብ። ሁላችንም በማያልቅ የሐሰት መረጃ እየተነዳን ነው። እነዚህ ስለራስህ ያሉ ውሱን ሃሳቦች ውሸት ናቸው። ጂም ኪዊክ እነዚህን አስተሳሰቦች LIEs(Limited Ideas Entertained) ይላቸዋል።

*ካሮል ድዌክ በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሥነልቦና ፕሮፌሰር በቋሚና ለማሻሻል የሚቻል ዕውቀት ያለውን ልዩነት ስታስረዳ ችሎታዎቻችን በልምምድ ከፍ ሊሉ የሚችሉ እንጂ እንደአንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ተቀርፆ የተሰጡን አይደሉም። ማንኛውም ሯጭ ልምምድ በማድረግ ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚችል ሁሉ የአዕምሯዊው ችሎታችን በትምህርት፣ በልምምድና በጥረት ከፍ ማድረግ የሚቻል ነው።

#ውሸት ቁጥር 1: አዕምሮአዊ ዕውቀት ቋሚ እንጂ ማሻሻል የማይቻል ነው።

*ውሸት ቁጥር 2: የአዕምሮአችንን ፲ ከመቶ ብቻ ነው መጠቀም የምንችለው።

#ውሸት ቁጥር 3: ስህተቶች ውድቀቶች ናቸው።

*ውሸት ቁጥር 4: ዕውቀት ሃይል ነው።

#ውሸት ቁጥር 5: አዳዲስ ነገሮችን መማር አስቸጋሪ ነው።

*ውሸት ቁጥር 6: የሌሎች ሰዎች ነቀፋ ተፅዕኖ ሊያሳድርብን ይገባል።

#ውሸት ቁጥር 7: ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ሰዎች ይወለዳሉ እንጂ በልምምድና በጥናት አይመጡም።
ከ Limitless መጽሐፍ የተወሰደ
(Jim Kiwik) ፣ ትርጉም: ቃለአብ ተክሌ

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!
#share and join for more

@KenibabDaricha
@KenibabDaricha