Get Mystery Box with random crypto!

ከፍልስፍና አምዶች 'የጅረቶች ብዛትና የዝናብ መዓት የውቅያኖስ ጣዕም እንደማይበርዙት ሁሉ የመ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ከፍልስፍና አምዶች

"የጅረቶች ብዛትና የዝናብ መዓት የውቅያኖስ ጣዕም እንደማይበርዙት ሁሉ የመከራ ውርጅብኝም የቆራጥ ሰው ህሊናን በድን አያደርገውም እንዲህ ያለ ሰው የህያውነት ሚዛኑን ይጠብቃልና። "
ሴኒካ

"የደስታ ምንጭ የምትሞላውና ሳታቋርጥ የምትፈሰው ከውስጣችን በሚፈልቁ ብሩህ አስተሳሰቦችና ስሜቶች ነው።"
ዊሊያም ላዩምፊሊፕስ

"ቅንዓት ሲመገብ ያደገ ፍቅር አሟሟቱ ከባድ ነው።"
ላቭስ ኩዩር

‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ
አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን

በገንዘብህ የጥቅም ጓደኞችን ልታፈራ ትችላለህ በውበትህ የስሜት ጓደኞች ልታፈራ ትችላለህ በእምነትህና በስነምግባርህ ግን..
የህይወት ጓደኞችን ታፈራለህ።


"ህይወት ጨካኝ መምህር ነው!!! ምክንያቱም መምህር አስተምሮ ነው የሚፈትነው ህይወት ግን ፈትኖ ነው የሚያስተምረው።"
ስብሃት ገ/እግዚአብሔር

የራስህን የህይወት እቅድ ዲዛይን ካላደረግክ ዕጣ ፈንታህ የሚሆነው በሌሎች እቅድ ውስጥ መኖር/መውደቅ ይሆናል።
- ጂም ሮን

የወደፊቱን ለመተንበይ የተሻለው ዘዴ፤ ወደፊትን መፍጠር ነው።
- አለን ኬይ

ከጌታዬ ሶስት ነገሮችን አጥብቄ እፈልጋለሁ አንድ ጥበብ ሁለት ጥንካሬ ሦሥት ፍቅር። ከነዚህ ከሦስቱ የበለጠ የምሻው ግን ፍቅርን ነው።ፍቅር ሲኖረኝ  ሁሉም ነገር አለኝ ነፃነትም ቢሆን "
ማርቲን ሉተር ኪንግ

"ልብህ ይናገር ዘንድ ምላስህ ዝም ይበል። እግዚአበሔር ይናገር ዘንድ ደግሞ ልብህ ዝም ይበል።"
አባራሀኒ

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!
#share and join for more

@KenibabDaricha @KenibabDaricha