Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ስለሚጠይቀው መስዋእትነት ካህሊል ጂብራን የፃፈውን ውብ እና ነፍስን የሚማርክ ፁሁፍ ልጋብዛ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ፍቅር ስለሚጠይቀው መስዋእትነት ካህሊል ጂብራን የፃፈውን ውብ እና ነፍስን የሚማርክ ፁሁፍ ልጋብዛችው

" ፍቅር በዓይኑ ጥቅሻ በጠራችሁ ጊዜ መንገዶቹ ምን ያህል አስቸጋሪ እና አቀበት ቢሆኑም ተከተሉት...ክንፎቹ ሲያቅፏችሁም ተሸጎጡበት ። በላባዎቹ መሀል የተደበቁ ሰይፎች ቢያቆስሏችሁም ወደኋላ አታፈግፍጉ ...

ሲያነጋግራችሁም እመኑት ። ድምፁ የሰሜን ኃይለኛ ንፋስ የአትክልትን ስፍራ እንደሚያወድም ሁሉ ህልሞቻችሁን ቢበታትንባችሁም እሱን ከማመን አታመንቱ..

ፍቅር ዘውድ የሚደፋላችሁን ያህል ይሰቅላችሁም ይሆናል ። የሚያሳድጋችሁንም ያህል ይከረክማችኋልም...እስከ ጫፍ ከፍ ብሎ በፀሃይ ውስጥ የሚወዛወዙትን እጅግ ለስላሳ ቅርንጫፎቻችሁን በፍቅር እንደሚደባብስ ሁሉ ፣ በመሬት ውስጥ ቁልቁል ወደ ስሮቻችሁ ወርዶም ተጠምጥሞ ከመሰረታቸው ይነቀንቃቸዋል..

እንደ በቆሎ ክምር ወደ ራሱ ይሰበስባችኋል ። እርቃናችሁን ሊያስቀራችሁም ይወቃችኋል ። ከላፋችሁ ሊያላቅቃችሁም ይነፋችኋል ። ነጭ ዱቄት እስክትሆኑም ድረስ ይፈጫችኋል ። እስክትለወጡም ያቦካችኋል ። ከዚያ ለአምላክ ቅዱስ ድግስ የምትቆረሱ ቅዱስ ዳቦዎች ትሆኑ ዘንድ ወደ ተቀደሰው እሳቱ ውስጥ ይጨምራችኋል....

ፍቅር እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያደርግባችሁ ፣ የልባችሁን ምስጢራት እንድታውቁ እና በዚያ ዕውቀትም የህይወት ልብ አንድ ግማድ እንድትሆኑ ነው...

፧ ይሁንና ፍርሃት አድሮባችሁ የፍቅርን ሰላም እና የፍቅርን ደስታ ብቻ የምትሹ ከሆነ፣ እርቃናችሁን ሸፍናችሁ ከፍቅር የመውቂያ ውድማ ወጥታችሁ ብትሄዱ ይሻላችኋል ። ወደዚያ የሄዳችሁበት ወቅቶች የማይፈራረቁበት ወቅት - አልባ ዓለም ውስጥም ትስቃላችሁ ። ነገር ግን ሳቃችሁን ሁሉ አትስቁትም ። ታላቅሳላችሁም፤ ግን እንባችሁን ሁሉ አታፈሱትም::

ደራሲ ካህሊል ጂብራን
ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!

#share and #join for more
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha