2022-12-03 08:51:21
ካሜሮን በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብራዚልን ያሸነፈች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆነች
በኳታር የዓለም ዋንጫ ካሜሮን ብራዚልን ብታሸንፍም ወደ ቀጣዩ ዙር ግን ማለፍ አልቻለችም።
በምድብ ሰባት በተደረጉ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ካሜሮን ከብራዚል የተጫወቱ ሲሆን፤ ጨዋታውም በካሜሮን 1ለ0 አሸናፊነት ነበር የተጠናቀቀው።
ካሜሮን ጨዋታውን በበላይነት ብታጠናቅቅም ጥሎ ማለፉን ግን መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች።
በአንጻሩ ብራዚል ቀድማ በሰበሰበችው ነጥብ ወደ ጥሎ ማፍ መቀላቀሏን ቀድማ አረጋግጣ ነበር።
በምድቡ ስዊዘርላንድ ከሰርቢያ ያደረጉት ጨዋታ ስዊዘርላንድ 3ለ2 ማሸነፏን ተከትሎ ስዊዘርላንድ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላች።
በኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ የተጠናቀቁ ሲሆን፤ ከነገ ጀምሮ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች መካሄድ ይጀምራሉ።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
492 views05:51