Get Mystery Box with random crypto!

መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው

የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የሰርጥ አድራሻ: @wetaderlifeoffishly
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው ከተለያዩ ታማኝ ሚድያዎች የሚሰሙ
የሀገር መከላከያ እና
የፌደራል ፖሊስን
የሚመለከቱ ዜናዎች ያገኙበታል በተጨማሪም የወታደር Life መዘናኛዎችን ልዩ ልዩ የወታደር ጀብዶች እና ታሪኮች የሚለቀቁበት የቴሌግራም ቻናላችን ነው
https://t.me/wetaderLifeOffishly

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-12-05 17:01:36
2 ህፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው የቤት ሰራተኛ በሞት እንድትቀጣ  ተወሰነ

2 ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባት ህይወት መኮንን የተባለችው የቤት ሰራተኛ በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ተወስኗል።

የቅጣት ውሳኔውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም  በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን አፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ  አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በማጥፋት በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ በጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ/ም የወንጀል  ክስ ተመስርቶባት እንደነበር ይታወሳል።

@EthioipaNews
797 views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 17:01:36
ከሕወሃት ታጣቂዎች 65 በመቶዎቹ ከውጊያ ግንባሮች ወጥተዋል ሲሉ የሕወሃት ኃይሎች ዋና አዛዥ ጀኔራል ታደሠ ወረደ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ጀኔራል ታደሠ "ሰላም አዋኪዎች" አሁንም በክልላችን ስላሉ፣ የተወሰኑ ኃይሎቻችን በግንባር እንዲቆዩ አድርገናል ብለዋል። ፌደራል መንግሥት የኤርትራ ወታደሮችንና የአማራ ክልል ታጣቂዎችን ከክልሉ እንዲያስወጣ ጀኔራል ታደሠ ጠይቀዋል። የስምምነቱን አፈጻጸም ለመከታተል የተቋቋመው አካል ገና ወደ ክልሉ እንዳልገባ የጠቀሱት ጀኔራል ታደሠ፣ የሕወሃት ኃይሎች ግን ስምምነቱን ተግባራዊ እያደረጉ ነው ብለዋል።

የሕወሃት ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ "የትግራይ ሕዝብን ደኅንነት ግምት ውስጥ ያስገባ" እንደሚሆንም ጀኔራሉ ገልጸዋል።

@EthioipaNews
683 views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 16:59:52 የጀርመኑ መሪ፤ ዓለም በቡድን ተከፋፍላ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት እንዳይፈጠር አስጠነቀቁ

የጀርመኑ መሪ ኦላፍ ሾልዝ ጀርመን የአውሮፓ ደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ ዝግጁ ናት ብለዋልhttps://am.al-ain.com/article/germany-warns-of-another-cold-war
650 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 16:59:52 በአዲስ አበባ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ግለሰብ የሞት ቅጣት ተፈረደባት
ተከሳሿ ድርጊቱን አልመፈጸሟን ብትክድም የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን መከላከል አልቻለችም። አለመማሯን እና ለፖሊስ እጇን መስጠቷን በማቅለያነት ብታቀርብም ፍርድ ቤቱ ማቅለያዋን አልተቀበለውም።
https://am.al-ain.com/article/women-who-killed-two-kids-sentenced-to-death
638 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 16:59:52 ኢራን ለእስራኤል ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸውን 4 ሰዎች በስቅላት ቀጣች

የሞሳድ የስለላ መረብ አባል ነበሩ የተባሉት ግለሰቦች ትናንት ጠዋት ነው በስቅላት የተቀጡት።ሌሎች ሶስት ግለሰቦችም ከ5 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።
https://am.al-ain.com/article/iran-executes-4-working-for-israel
660 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 12:37:05 የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በኳታር ጉብኝት እያደረጉ ነው

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ወደ ዶሃ ያቀኑት በኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃሚድ ግብዣ ነው። በጉብኝቱ ወቅት የሁለቱን ሀገራት ግንኙት የሚያሳድጉ ስምምነቶች እንደሚደረሱ ይጠበቃል።
https://am.al-ain.com/article/uae-president-official-visit-to-qatar
359 views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 12:37:05 “በራሪው” ቢ21 ሬይደር ስውር የኒውክሌር ቦምብ ጣይ አውሮፕላን

አሜሪካ ለዓመታት በሚስጥር የሰራችውን አዲሱን ቢ21 ሬይደር የጦር አውሮፕላን ይፋ አድርጋለች። የኒውክሌር አረር የመሸከም አቅም ያለው አውሮፕላኑ ያለ አብራሪ መጓዝ ይችላል።
https://am.al-ain.com/article/us-b-21-nuclear-bomber
347 views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 12:37:05
የትናንትናው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ውጤት

የኳታሪ የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በትናንትናው እለትም ቀጥለው የተካሄዱ ሲሆን፤ በተካሄደው ጨዋታ እንግሊዝና ፈረንሳይ ወደ ሩብ ፍጻሜው ማለፍ ችለዋል።

አፍሪከዊቷ ሴኔጋል እና ፖላንድ ደግሞ ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
311 views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 12:37:05
ሴኔጋል በእንግሊዝ ተሸነፈች፤ ወደ ሩብ ፍጻሜው ሳታልፍ ቀረች

በኳታር እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በእንግሊዝ በመሸነፏ ወደ ሩብፍ ፍጻማ ሳታልፍ ቀረች፡፡ ሴኔጋል 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በእንግሊዝ ተሸንፋለች፡፡
ፖላንድም በፈረንሳይ ተሸንፋ ወደ ሩብ ፈጻሜው ሳታልፍ ቀርታለች፡፡እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ወደ ሩብ ፍጻሜው ማለፍ ችለዋል፡፡
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
264 views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:35:06
ወለጋ

በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ባለው የፀጥታ ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለዋል ፤ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል።

ተፈናቃይ ወገኖች / ህይወታቸውን ለማትረፍ የሸሹ ወገኖች ሰላምን ፍለጋ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ በእግር ታጉዘው ጊዳአያና ወረዳ መግባት ችለዋል።በወረዳው በ19 ቀበሌዎች ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ነቀምቴና ጊዳ አያና ወደሚገኙ አካባቢዎች ለመሸሽ ተገደዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፥ " እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " ያሉ ሲሆን ብዙ ህዝብ መፈናቀሉን ፣ ተፈናቃዮች ሰላምን ፍለጋ በሸሹበት ወቅት እየራባቸው ፤ እየደከማቸው በእግር ለመጓዝ መገደዳቸውን ገልፀዋል።

መንግሥት በአፋጣኝ የመከላካያ ሠራዊት ወደ ከተማዋ በመላክ ህይወታቸውን እንዲታደግ በአከባቢው በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች ጠይቀዋል፣ በኦሮሚያ ልዩ ሀይልም እምነት እንደሌላቸው ከስፍራው አሳውቀዋል።

ወደ ከተማዋ የገቡት የታጠቁ ኃይሎች በፓትሮል ተሸከርካሪዎች ከነፍስ ወከፍ መሳሪያ በተጨማሪ ሌሎች የቡድን መሳሪያዎችንም ይዘው ጥቃቱን ሲፈፅሙ እንደነበር ነዋሪዎች ገልፀዋል። ነዋሪዎቹ በጥቃቱም ንጹሃን ሰለባ ሆነዋል፣ አቅማቸው የፈቀደ ወደ ጫካ ገብተዋል እና አቅመ ደካሞች እና ህጻናት ግን በቦታው ቀርተዋል፣ ብዙዎችም በማንነታቸው ተገድለዋል ሲሉ ገልፀዋል።
 
@EthioipaNews
497 views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ