Get Mystery Box with random crypto!

መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው

የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የሰርጥ አድራሻ: @wetaderlifeoffishly
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው ከተለያዩ ታማኝ ሚድያዎች የሚሰሙ
የሀገር መከላከያ እና
የፌደራል ፖሊስን
የሚመለከቱ ዜናዎች ያገኙበታል በተጨማሪም የወታደር Life መዘናኛዎችን ልዩ ልዩ የወታደር ጀብዶች እና ታሪኮች የሚለቀቁበት የቴሌግራም ቻናላችን ነው
https://t.me/wetaderLifeOffishly

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-12-07 08:20:18
ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን 6ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች!!

ሴሌሳኦቹን ባለድል ያደረጉትን ሶስቱን ግቦች ጎንካሎ ራሞስ ከመረብ ሲያሳርፍ ቀሪዎቹን ግቦች ፔፔ ፣ራፋኤል ጉሬሮ እና ራፋኤል ሊያኦ  በስማቸው አስመዝግበዋል። የስዊዘርላንድን ብቸኛ ግብ አካንጂ አስቆጥሯል።

በጨዋታው ፔፔ በ39አመት ከ283 ቀኑ በአለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ግብ በማስቆጠር አንጋፋው ተጫዋች ሲሆን በተቃራኒው ጎንካሎ ራሞስ  ደግሞ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች ለመሆን ችሏል። ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድሩ በአምስት  ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ከ1966 በኋላ በአንድ የአለም ዋንጫ በበርካታ ግቦች ላይ ተሳትፎ ያደረገ የመጀመሪያው ፖርቹጋላዊ ተጫዋች ለመሆን ችሏል። ብሩኖ በኳታሩ የአለም ዋንጫ ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ ሶስት ግብ የሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በትልቅ ውድድር ከፖርቹጋል ቋሚ አሰላለፍ ውጪ ሲደረግ ከ2008 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በጨዋታው  እሱን ተክቶ የገባው ጎንካሎ ራሞስ ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ ግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ያቀበለ ሲሆን ከ2002  በኋላ በአለም ዋንጫ በቋሚነት በጀመረበት የመጀመሪያ ጨዋታው ሃትሪክ የሰራ ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል።

@EthioipaNews
67 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 08:20:18
ሞሮኮ ስፔንን በማሸነፍ ሩብ ፈፃሜውን ተቀላቀለች።

ስፔን ከሞሮኮ ባደረጉት ጨወታ በተጨማሪ ሰዓት ጎል ማስቆጠር ተስኗቸው በፍፁም ቅጣት ምት ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈችው።

ሞሮኮ በቀጣይ ወደ ግማሽ ፈፃሜ ለማለፍ ከ ፖርቹጋል እና ሲውዘርላንድ አሸናፊ ጋር የምትፋለም ይሆናል።

ምሽት አራት ሰዓት ፖርቱጋል ከሲውዘርላንድ የማያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨወታ ተጠባቂ ነው።

@EthioipaNews
69 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 08:20:18
የመቀሌ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተገናኘ!

በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ከዓመት በላይ ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተቋርጦ የቆየው የመቀሌ ከተማ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል (ግሪድ) ጋር ተገናኝቷል መገናኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር መስመሩ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር የተገናኘው ከአላማጣ መሆኒ በተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ነው ብለዋል።

በመስመሩ ፍተሻና የጥገና ሥራ ላይ በሰሜን ምስራቅ ሪጅን አስተባባሪነት ከሁሉም ሪጅን የተውጣጡ የማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር የጥገና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።የመስመሩ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመር በትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ መልሶ ሥራ ለማስጀመር የተጀመረውን ሥራ የሚያፋጥነው ይሆናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሁመራ እስከ ሽሬ ድረስ የተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቋል።ይሁንና ለሽሬ ኃይል የሚሰጠው ከተከዜ እስከ አክሱም በተዘረጋው መስመር ስምንት ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማጋጠሙ ጥገናው ወደ ተከዜ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ መቀጠሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@EthioipaNews
63 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 08:20:18
"የፋኖ ታጣቂዎች ከኦሮሚያ ክልል እንዲወጡ ይደረግ" ሲሉ አቶ ጃዋር መሀመድ ገለፁ!

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ጃዋር መሀመድ "የፋኖ ሚሊሻዎችን ከኦሮሚያ ክልል ማስወጣት" በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት መደረግ አለባቸው ካሏቸው መፍትሄዎች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባጋሩት ኃሳብ በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ይጠቅማሉ በማለት ያሰፈሯቸው ነጥቦች “መንግስት ራሱን "የአሮሞ ነፃነት ግንባር" ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር ወደ ተኩስ አቁም የሚያመራ ድርድር ማድረግ፣ የፋኖ ሚሊሻዎችን ከኦሮሚያ በማስወጣት ተፈናቃዮችን መመለስ እንዲሁም አካታች የሆነ የብሔራዊ እርቅ ሂደትን በመቀበል ለተፈፃሚነቱ እቅድ ማስቀመጥ” የሚሉት ናቸው።

Addis Zeybe
@EthioipaNews
62 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 17:13:24 የጃፓን ደጋፊዎች ሀገራቸው ከዓለም ዋንጫ ውጪ ብትሆንም ስታዲየም ማጽዳታቸውን ቀጥለዋል

ጃፓን በትናትናው እለት በፍጹም ቅጣት ምት በክሮሺያ ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆናለች። የጃፓን ደጋፊዎች ከሀገራቸው ውጪ የሌላ ብሄራዊ ብድን ጨዋታ ሲመለክቱም ስታዲየም ያጸዳሉ።
https://am.al-ain.com/article/japan-fans-clean-stadium
920 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 17:13:23 የአውስትራሊያ ሕግ አውጪዎች የቤጂንግ ማስጠንቀቂያን ችላ በማለት ታይዋን ገቡ

ጉብኝቱ ራሷን ለማስተዳደር በምትፈልገው ደሴቲቷ ታይዋንና ቻይና መካከል ውጥረት እንዲጨምር ያደርጋል ተብሏል
https://am.al-ain.com/article/australian-lawmakers-land-in-taiwan
872 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 17:13:23 በኢትዮጵያ የሩስያ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበች

የኢትዮጵያና የሩስያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። በስብሰባው ከዚህ ቀደም በሀገራቱ መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚረዳ መሆኑን ሩሲያ አስታውቃለአች።
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-russia-joint-ministerial-meeting
814 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 13:49:52 በምስራቅ ወለጋ ዞን የተፈጸመው ግድያ እና መፈናቀል ጉዳይ

በምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች በአስቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፍርሃት መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ተናገግረዋል።ስለጉዳዩ የአካባቢውን ነዋሪዎች አነጋግረናል፡፡ሙሉውን ለማንበብ፡-https://am.al-ain.com/article/many-killed-in-east-wellega-zone
977 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 13:49:52 የሩሲያን ጥቃት ተከትሎ ግማሽ የሚሆነው የኪቭ ግዛት አሁንም ኤሌክትሪክ አልባ ነው ተባለ

ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ያሏት ኪቭ በጭለማ የተዋጠችው የሚሳይል ጥቃቱ ወሳኝ የሆኑትን የኃይል መሰረተ ልማቶችን ላይ ኢላማ ያደረገ ስለነበር ነው ተብሏል፡፡https://am.al-ain.com/article/half-of-kyiv-region-remains-without-power
849 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 13:49:52 የሞሮኮን የድል ጉዞ ለመደገፍ የተጫዋቾች እናቶች ስታዲየም ተገኝተዋል

ሞሮኮ ሲያሸንፉ አሽራፍ ሃኪሚ ጎል እንዳስቆጠረ ተንደርድሮ ሄዶ እናቱ አቅፎ ስሟል። ዛሬም ስፔንን በጥሎ ማለፉ ሲገጥሙ ይሄው በስታዲየም የሚመለከተው የእናቱና የደጋፊዎቹ የሞራል ድጋፍ ይጠበቃል።
https://am.al-ain.com/article/morocco-s-football-moms-and-fans-inspiration
779 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ