Get Mystery Box with random crypto!

መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው

የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የሰርጥ አድራሻ: @wetaderlifeoffishly
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው ከተለያዩ ታማኝ ሚድያዎች የሚሰሙ
የሀገር መከላከያ እና
የፌደራል ፖሊስን
የሚመለከቱ ዜናዎች ያገኙበታል በተጨማሪም የወታደር Life መዘናኛዎችን ልዩ ልዩ የወታደር ጀብዶች እና ታሪኮች የሚለቀቁበት የቴሌግራም ቻናላችን ነው
https://t.me/wetaderLifeOffishly

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 68

2022-07-13 17:23:27 የብሪታኒያ መንግስት በሞ ፋራህ ዜግነት ጉዳይ ምን አለ?

ሞ ፋራህ ታዳጊ እያለ በአንዲት በማያውቃት ሴት ተገዶ ከጅቡቲ ወደ ብሪታንያ በህገ ወጥ መንገድ መግባቱን መናገሩ ይታወሳል
https://am.al-ain.com/article/what-did-the-british-government-say-about-mo-farah-s-citizenship
857 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:27 በአማራ ክልል በ1 ጀንበር 250 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በባህር ዳር የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ
******************


በአማራ ክልል በአንድ ጀንበር 250 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል አረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰባታሚት ተካሂዷል።

በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ጌታቸው ጀንበር የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራው አንድ አካል የሆነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የውሀ ሀብትንም ለመጠበቅ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0mJ39TRvAxKmFGB77SXZbu35qMn61yZqSJ89zt4zCrGamUcc2DvUqMJAbAeM2ERHvl
863 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:27
የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በፌደራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቲቪ እንዳሉት ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጅል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

Via EBC
866 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:27
"ግብፅ ኢትዮጵያን ከውሃ ሙሌት ለማቀብ ባደረገችው ጥረት ክፉኛ ተሸንፋለች። ደቡብ ሱዳናዊው #DengBolAruaiBol በደቡብ ሱዳን የ #RedArmy #Foundation ሊቀመንበር የሆነው #DengBolAruai ግብፅ የህዳሴ ግድብን ጉዞ ለመግታትና ኢትዮጵያን ለማተራመስ በደቡብ ሱዳን በቀጣይ ልትወስዳቸው ስለምትችለው ነፍስ ቀጣፊ እርምጃዎች ለ #SudanTribune ፅፏል።

በዚህም ግብፅ ኢትዮጵያን ከውሃ ሙሌት ለማቀብ ባደረገችው ጥረት ክፉኛ ተረታለች ሲል ምልከታውን ገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ "ኢትዮጵያ ሁለት ወሳኝ ሀይል አላት። ንቁ ወታደር እና ሰፊ ህዝብ ። ኢትዮጵያን ለማዳካም የምትችለውን ሁሉ የምታደርገው ግብፅ ደም አፋሳሽ በሆነ የውክልና ጦርነት በኩል ጥቅሟን ለማስከበር ቢሊዮን ዶላሮችን ለደቡብ ሱዳን መንግስትና ግለሰቦች ለመስጠት ቆርጣ ተነስታለች ይለናል።

ምንም እንኳን ግብፆች ሀገሪቱን ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት ከሞላ ጎደል በሁሉም የደቡብ ሱዳናውያን ህዝብ ውድቅ ሆኖባቸዋል። ይህን ካወቁ በኋላ ግራ ተጋብተዋል ሲል ፅሁፉን አስፍሯል። ፀሃፊው ግብፅ የጁባን ፖለቲካ ተቆጣጥራ ጥቅሟን ለማስከበር ሶስት አይነት መንገዶችን ልትከተል ትችላለች በማለት የቢሆን ትንተና (scenario analysis) አስቀምጧል።
883 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:27
ልዩ መረጃ

የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል።

#Ethiopia : የኮሚቴው አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባ ማካሄዱን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። አምባሳደር ሬድዋን እንዳሉት ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለሚካሄደው ንግግር የራሱን የአሰራርና ሥነ ምግባር አካሄድ ተወያይቶ ወስኗል።

በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጀት ኃላፊነት ተከፋፍሎ ሥራውን እንደጀመረም አስታውቀዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰብሳቢነት የሚመሩት በአጠቃላይ ሰባት አባላት ያሉት የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል።
890 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ