Get Mystery Box with random crypto!

መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው

የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የሰርጥ አድራሻ: @wetaderlifeoffishly
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው ከተለያዩ ታማኝ ሚድያዎች የሚሰሙ
የሀገር መከላከያ እና
የፌደራል ፖሊስን
የሚመለከቱ ዜናዎች ያገኙበታል በተጨማሪም የወታደር Life መዘናኛዎችን ልዩ ልዩ የወታደር ጀብዶች እና ታሪኮች የሚለቀቁበት የቴሌግራም ቻናላችን ነው
https://t.me/wetaderLifeOffishly

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 67

2022-08-29 10:28:59
#ቆቦ
ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቆቦን መልሶ ተቆጣጥሯል።

በትናንትናው እለት ቆቦን ለቆ ወጥቶ የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መልሶ ከተማዋን ተቆጣጥሯል። የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎች ይዞ የነበረ ቢሆንም ሰራዊት ወደፊት በመገስገስ ቆቦ ከተማ እና አከባቢውን በቁጥጥሩ ስር አውሏል። በሂደቱም ብዛት ያለው የወራሪው ሀይል አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአሁኑ ሰአት ሰራዊቱ በከፍተኛ ወኔ እና ብቃት ወደ ፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

@bbc_amharic1
2.4K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:34:10
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጎረቤት አገራት መደበቁን መንግሥት ገለጸ

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከመዳከም አልፎ ወደ ጎረቤት አገራት በመሸሽ መደበቁን መንግሥት አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሸበሪ ቡድኑን ማዳከም መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ እየተወሰደበት ባለው እርምጃ እየተዳከመ ቢሆንም የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨት ለጥፋት ሀይሉ ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን ሁኔታው በሕዝብ ዘንድ መጠራጠርን ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በወለጋ አሸባሪው ቡድን ጥቃት ላደረሰባቸው ዜጎች መንግሥት አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የአሸባሪዎቹ አላማ ከውጭ ባንዳዎች ጋር በመተባበር ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቆም የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@bbc_amharic1
554 views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:53:24
ከ14ኛ ዙር የ20/80 እንዲሁም ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ስም ዝርዝር

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-
1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን :_ዳይሬክተር
3ኛ. ሀብታሙ ከበደ :_ሶፍትዌር ባለሙያ
4ኛ. ዬሴፍ ሙላት :_ሶፍትዌር ባለሙያ
5ኛ. ጌታቸው በሪሁን :_ሶፍትዌር ባለሙያ
6ኛ. ቃሲም ከድር :_ሶፍትዌር ባለሙያ
7ኛ. ስጦታው ግዛቸው :_ሶፍትዌሩን ያለማ
8.ኛ. ባየልኝ ረታ ፡_ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ
9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፡_የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ
10ኛ .ኩምሳ ቶላ ፡_ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

በቀጣይም ሂደቱን እየተከታተልን ለህዝባችን ማድረሳችንን የምንቀጥል ይሆናል፡፡
1.4K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:28 በኢትዮጵያ እና በጃፓን መንግስት መካከል 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት “የምግብ እርዳታ ፕሮግራም” ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ተፈራርመዋል።ዕርዳታው 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች በተከሰተው ድርቅና በሰሜኑ ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው ተብሏል።ጃፓን በመሠረተ ልማት ፣በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
1.3K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:28
ሰበር ዜና

በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ ተደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
1.2K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:28
ኤልሻዳይ” ግብረ ሰናይ ድርጅት ከኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ጋር በመመሳጠር የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀሎች ፖሊስ ይፋ አደረገ

ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን መንግስትዊ ያልሆነ ገብረሰናይ ድርጅት በተረጂዎች ስም ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለእርዳታ የተዘጋጀን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን አላግባብ ወስዶ ለግልጥቅም አውሏል በሚል ተጠርጥረው ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ፖሊስ ባደረገው የማጣራት ስራ የተሰበሰበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በተለይ ለኢቲቪ አስታውቋል።

በምርመራ ሂደቱ የተገኙ ግኝቶችም፦

1ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን በየጊዜው አሉ ተብሎ እርዳታ የሚጠየቅላቸው ዜጎች በትክክል ስለመኖራቸው እና አለመኖራቸው በተደረገ ምርመራ፡-

ድርጀቱ በክልል ካሉት ማዕከል ውስጥ በ3 ማዕከላት ማለትም በአማራ ክልል ቁጭት ለልማት ማዕከልከ 2010 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር፤ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2019 ማእከሉ 14 ተረጂዎች ብቻ እያለው ዓመቱን ሙሉ በ2 ሺህ 631 ተረጂዎች ስም የእርዳታ ስንዴ ጠይቆ ከኮሚሽኑ የተሰጠው መሆኑን በማስረጃ ተረጋግጧል።

ድርጅቱ በአፋር እና ደቡብ ክልል ማዕከል የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር የጠየቀ እና የወሰደ መሆኑን፣ በጋምቤላ ክልል ማዕከል ስም የጠየቀው ተፈቅዶለት ያልወሰደ እና በሙከራ ደረጃ የቀረ መሆኑን በማስረጃ ለማረጋገ ጥተችሏል

2ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን በተለይ ከ2009 ዓ.ም ጀ... https://www.facebook.com/100063883683426/posts/pfbid02iPdo8vrdpKqkVG97fFpf7irA1vgm33ed8Vi1eieEXmz5z1xkXG7Nudbo4RK16HBul/?d=n
1.1K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:28 ሩሲያ፤ ባይደን ጉብኝታቸውን “ሪያድን ጸረ-ሞስኮ ለማድረግ እንደማይጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ” አለች

የክሬምሊን ቃል አቀባይ፤ በዓለም የነዳጅ አምራቾች ማዕቀፍ ውስጥ ሩሲያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ለምታደርገው ትብብር ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለች ብለዋል።
https://am.al-ain.com/article/russia-hopes-jo-biden-will-not-turn-ryad-against-moscow
976 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:28
#AddisAbaba

የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ !

ከነገ ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትራንስፖርት ታሪፍ ይፋ ተደርጓል።

አዲሱ ታሪፍ የሚኒባስ ታክሲ እና የሚድ ባስ (ሃይገርና ቅጥቅጥ) የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚመለከት ነው።

በሚኒባስ ታክሲ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር ድርስ የጨመረ ሲሆን በሚድ-ባስ ላይ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 2 ብር ድርስ ጨምሯል።

የሸገር እና አንበሳ ከተማ አውቶብስ ታሪፍ በዚህ ወር መጨረሻ ይስተካከላል ተብሏል።
931 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:28
ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ሆኑ

ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል እንደሆነና ከዚህ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ዩሮ 12 በመቶ መቀነሱ ተገለጸ።

በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በተፈጠረው የኃይል አቅርቦት አለመመጣጠን የተነሳ አውሮፓ የኢኮኖሚ ውድቀት እንዳጋጠማት ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ከጦርነቱ በፊት 40 በመቶ የሚሆነውን ጋዝ በሩሲያ የቧንቧ መስመር ያገኝ የነበረው የአውሮፓ ኅብረት ከጦርነቱ በኋላ በሩሲያ ዘይት እና ጋዝ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ሲሞክር ሩሲያ በበኩሏ ለአንዳንድ የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት የጋዝ አቅርቦትን አቋርጣለች።

የኢነርጂ ቀውሱ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ያስከተለ ሲሆን የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለማውረድ ፖሊሲውን በበቂ ሁኔታ ማጥበቅ ስለመቻሉ ጥርጣሬን ፈጥሯል ነው የተባለው።

በዚህም የዩሮ ዋጋ ከዶላር እኩል በመሆኑ የወርቅ ግብይት ላይ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

የዩሮ ዞን የዋጋ ግሽበት በ8 ነጥብ 6 መቶ ላይ በመቀመጡ ከአውሮፓዊያኑ 2011 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ወር የወለድ ምጣኔን እንደሚያሳድግ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል።
916 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:28
በአዲስ አበባ በቀጣዩ ወር በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል

በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ገበያዉ ለማስገባት ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ በሆነዉ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከ ከግሪንቴክ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን በቀጣዩ አንድ ወር በኤሌትሪክ በሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በዛሬዉ እለት ባደረገዉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ የማስተዋወቅ መድረክ ላይ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደተናገሩት በቀጣዮቹ አስር አመታት በኢትዮጵያ 4ሺህ 800 የኤሌክትሪክ አዉቶብሶችን እንዲሁም 148 ሺህ የኤሌክትሪክ አዉቶሞቢሎችን ለማስገባት እንደታቀደም አስታዉቀዋል። ኢትዮጵያ ለነዳጅ በአመት የምታወጣዉን 4 ቢሊዮን ዶላር ወጪን ለማዳን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸዉም አብራርተዋል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ ፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን ከመገንባት አንጻር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸዉ የግሪን ቴክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሲትራ አሊ ተናግረዋል። በቀጣይም ተቋሙ አዉቶሞቢሎች ፣ ሚኒባስ እና ሚዲባሶች ፣ አምቡላንሶች ፣ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች የተሽከርካሪዎች አይነቶችን ለማምረትም እቅድ እንዳላቸዉ አስታዉቀዋል።

በቀጣይም አንድ ወር የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስተዋወቅ 60 በሆኑ ተሽከርካሪዎች በአዲስአበባ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽት 1 ሰዓት እሁድ እና የበዓል ቀናትን ጨምሮ ነጻ የትራንስፖርት አግልግሎት እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

ለዚህም በአዲስአበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የተተከሉ 40 የሚሆኑ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች እንደተዘጋጁም ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።
894 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ