Get Mystery Box with random crypto!

መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው

የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የቴሌግራም ቻናል አርማ wetaderlifeoffishly — መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው
የሰርጥ አድራሻ: @wetaderlifeoffishly
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው ከተለያዩ ታማኝ ሚድያዎች የሚሰሙ
የሀገር መከላከያ እና
የፌደራል ፖሊስን
የሚመለከቱ ዜናዎች ያገኙበታል በተጨማሪም የወታደር Life መዘናኛዎችን ልዩ ልዩ የወታደር ጀብዶች እና ታሪኮች የሚለቀቁበት የቴሌግራም ቻናላችን ነው
https://t.me/wetaderLifeOffishly

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-12-07 16:13:54 የአውሮፓ ግማሹ ህዝብ የጤና ማገገሚያ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

በሁለቱ አህጉራት በእድሜ የገፉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል
https://am.al-ain.com/article/who-says-half-europe-population-needs-rehabilitation
853 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:54
የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉ ሀገራት

በኳታር እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ 5 የአውሮፖ፣1 የአፍሪካ እና 2 የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል። ሞሮኮ ከአፍሪካ ያለፈች ብቸኛ ሀገር ሆናለች።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
816 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:54 ፖላንድ  የጀርመን  ፓትሪዮት ሚሳይል ባትሪዎችን  በግዛቷ ላይ ለመትከል ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች


ፓትሪዮት ሚሳይል ባሊስቲክ ሚሳይሎችንና የጦር አውሮፕላኖችን ለመቋቋም  የሚስችል የአየር መከላከያ ዘዴ ነው
https://am.al-ain.com/article/poland-allows-german-patriot-missiles-on-its-territory
761 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:54 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሰሜን ኮሪያ ጋር ግንኙነት ካለው ኩባንያ እዳ ደብቀዋል በሚል "ተከሰሱ"

ትራምፕ በፕሬዝዳንትነት ዘመቻቸው ወቅት እና ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ሰነዶቹን ለፌደራል ባለስልጣናት እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸው ነበር
https://am.al-ain.com/article/trump-accused-concealing-a-debt-to-a-company-linked-to-north-korea
739 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:54 የሁለቱ ኮሪያዎች ድንበር በመድፍ ጩኸት መታወኩን ቀጥሏል

ትናንት ከ130 በላይ መድፎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ የተኮሰችው ፒዮንግያንግ ዛሬም ተጨማሪ መድፍ ሲተኮስ እንዲውል ትዕዛዝ ሰጥታለች
https://am.al-ain.com/article/north-korea-orders-new-missiles-to-be-fired-into-s-korea-sea
721 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:54
በኳታር የዓለም ዋንጫው ኮኮብ ተጫዋች እና አግቢ ማን ሊሆን ይችላል?

በስድስት ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ ያሉ ተጫዋቾች ይሄንን ሽልማት የመውሰድ እድል እንዳላቸው ጎል ስፖርት በድረገጹ አስነቧል

ፈረንሳዊ የ23 ዓመት ተጫዋች ክሊያን ምባፔ ሌላኛው ፈረንሳዊ ኦሊቨር ዥሩድ ስፔናዊ አልቫሮ ሞራታ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ቡካዮ ሳካ፣ ሀሪ ኬን ፣ ጁድ ቤሊንግሀም እና ራሽፎርድ ሀገራቸው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ እንዲሁም ፖርቹጋላዊው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከቀድሚዎቹ ተርታ ተሰልፈዋል።

በእርስዎ ግምት የወርቅ ጫማውን ማን እሚወስድ ይመስልዎታል?
https://am.al-ain.com/article/who-could-win-golden-boot
712 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:54
ሩሲያና ኢትዮጵያ በኒኩሌር በሌሎች መስኮች በጋራ ለመሥራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተገለጸ

ሩሲያና ኢትዮጵያ፤ ኒኩሊየርን ለሰላማዊ አገልግሎት ለማዋልና በሌሎች መስኮች በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተመላክቷል።

የሩሲያ እና የኢትዮጵያ በይነ መንግስታት የኢኮኖሚ፣ የሳይንስ፣ የቴክኒክ እና የንግድ ትብብር የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን ፤50 የሩስያ ሉዑክ አባላት፣ የኢትዮጵያ ተቋማት ተወካዮች እና የግሉ ዘርፍ እየተካፈሉ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ይቭጌኒ ቴሬኪን፤ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው የጋራ ኮሚሽን ስብሰባው ከዚህ ቀደም የተፈረሙ ስምምነቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር፣ የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ እና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምክክር የሚደረግበት እንደሆነ ተናግረዋል።
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-russia-joint-ministerial-meeting
696 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:53
ኪም ጆንግ ኡንሰሜን ኮሪያ የዓለም ትልቁ የኒውክሌር ኃይል ባለቤት ትሆናለች አሉ

ኪም ጆንግ ኡን ይህን ያሉት አዲሱን የሃዋሶንግ-17 አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ከተመለከቱና የሚሳኤል ማስወንጨፉ ላይ የተሳተፉትን በደርዘን የሚቆጠሩ የጦር መኮንኖችን የማበራተቻ እድገት በሰጡበት ወቅት መሆኑን ኬሲኤንኤ ዘግቧል።

ኪም ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካ በኩል ሊቃጣ የሚችለውን የኒውክሌር አደጋ በኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመከላከል ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

የኪም ንግግር በቻይና መሪ ዢ ጂንፒንግ በደብዳቤ ካቀረበቡላቸው የትብብር ጥሪ ከሰዓታት በኋላ የተደረገ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።
https://am.al-ain.com/article/kim-north-nuclear-power
694 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:53
የአብርሃም ስምምነት ለቀጠናችን ስጦታ ነው- የእስራኤል ፕሬዝዳንት

የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን መክረዋል።

ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ በዚሁ ወቅት "አስደናቂው የአብርሃም ስምምነት ለቀጣናችን ትልቅ ስጦታ ነው” ያሉ ሲሆን፤ በቀጣይም በመካከላችን ያለውን አጋርነት ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

ከሁለት ዓመት በፊት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ፣ እስራኤልና ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በዋይት ሀውስአመቻችነት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።
https://am.al-ain.com/article/uae-president-sheikh-mohamed-receives-president-of-israel
689 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:13:53
ፖርቹጋል ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች


በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው የተካሄዱ ሲሆን ምሽቱን ፖርቹጋል እና ስዊዘርላንድ ተጫውተዋል።

በጨዋታውም ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን 6ለ1 ሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።

በዛሬው እለት ለሀገሩ ለመጀመሪያ ጊዘየ ተሰልፎ የተጫወተው ጎንሳሎ ራሞስ በመጀመሪያ ጨዋታው ሶስት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሞሮኮ ስፔንን በፍጹም ቅጣት ምት በመርታት ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች።

ይህንን ተከትሎ በሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ሞሮኮ ከፖርቹጋል የሚጫወቱ ይሆናል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
705 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ