Get Mystery Box with random crypto!

🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

የቴሌግራም ቻናል አርማ wbfqr — 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷
የቴሌግራም ቻናል አርማ wbfqr — 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷
የሰርጥ አድራሻ: @wbfqr
ምድቦች: ሽያጭ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 507

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-21 09:08:29 #የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 4

ከወራቶች በኀላ #ወገን እንዳናግራት አደፋፈረኝና ላናግራት ወሰንኩ፡፡ በሰዓቱ እንደሷ የምፈራው ሰው አልነበረም፡፡ በሆነ አጋጣሚ ሳያት ከያዘችኝ የምገባበት ነበር የሚጠፋኝ፡፡ ነገር ግን የሚሰማኝን በውስጤ አምቄ ከምሰቃይ ልተንፍሰውና ይለይለት ብዬ ወሰንኩ፡፡ እንደነገ ላወራት እንደዛሬ አዳር ላይ የምላትን እና ከእሷ ሊመጡ ይችላሉ የምላቸውን ምላሾች በመገመት በድጋሚ የምላትን ከእራሴ ጋር ስለማመድ አደርኩ፡፡

አይነጋ የለም ነግቶ ት/ት ቤት ገባን፡፡ ላናግራት የወሰንኩት ምሳ ሰዓት ስለነበር እስከዛ ያለው ሰዓት በጣም እራቀኝ። ሙሉ ሰውነቴን የፍራት ካባ ሲለብሰኝ ተሰማኝ፡፡ ምሳ እንደበላን ከትምርት ቤታችን ባለ 4 ፎቅ ህንፃ እራሱን እንደሚያጠፋ ሰው 4ኛው ላይ ሁኜ አስጠራዋት፡፡ ቦታውን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ተማሪዎች በምሳ ሰዓት ስለማይበዙበት ነበር። ሌላው ደሞ በሰዓቱ ሴትን ቀጥሮ ስለማውራትም ሆነ ምቹ ስለሆኑ ቦታዎች እውቀቱ ስላልነበረኝ ነው፡፡

ከትንሽ መንቆራጠጦች በኀላ በደም ፈንታ በደም ቧንቧዎቼ የምትዘዋወረው ቆንጆ ከህንፃው መወጣጫ ደረጃዎች በአንዱ በኩል መጣች፡፡ ልክ እንዳየዋት ውስጤ ይረበሽ ጀመር፤ ማታ የተዘጋጀውበት በሙሉ እንደ ጉም ተኖ ጠፋ፡፡ አጠገቤ እንደደረሰችም ልብን በሚያቀልጠው ፈገግታዋ ሞቅ ያለ ሰላምታ ከሰጠችኝ በኀላ እንዳላወቀ ሰው "ለምን ነበር የፈለከኝ?" አለች ትኩር ብላ እያየችኝ፡፡ አይኖቼ ከአይኖቿ ጋር ሲላተሙ ይባስ እፈራትና እረበሽ ጀመር፡፡

ትንፋሽ እንዳጠረው ሰው እያቃሰትኩ "እየውልሽ #ፀጊ አፍቅሬሻለው፤ ጓደኛ እንሁን" አልኳት አንዴ እሷን አንዴ መሬቱን እያየው፡፡

"አይ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር ማሰብ አልፈልግም፤ አልችልም፡፡" አለች እጥር ምጥን ብሎ ለጆሮ በሚከብድ አማርኛ፡፡

"እሺ፤ ቻው" ብያት እኔ በአንዱ ደረጃ እሷ በሌላኛው ዳግም ላንገናኝ በሚመስል መልኩ እየተጣደፍን ሄድን፡፡ ቀጥታ ክላሴ ገባውና እራሴን ካረጋጋው በኀላ ለምን ልናገር ያሰብኩትን እንዳልተናገርኩና "አልችልም" ስትለኝ "ለማስረዳት በመሞከር ፈንታ ለምን "እሺ" የምትለው ቃል ከአፌ እንደወጣች እራሴን ጠየኩት፡፡ ለካ ከሚያፈቅሩት ሰው ፊት መቆም ለሞት ፍርድ ከመቆም ባልተናነሰ ልብን ሰልቦ በፍርሀት ይለውሳል፡፡

..... ይቀጥላል
7 views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 07:18:39 #የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል3
ከዛን ቀን ጀምሮ በእየቀኑ ስለሷ ማሰብና መጨነቅ ስራዬ ሆነ፡፡ ት/ት ቤት፣ ሰፈር፣ ማታ አልጋዬ ላይ ተኝቼ የማስበውም የማልመውም እሷኑ ሆነ፡፡ በሰዓቱ ገና የ14 አመት ልጅ ስለነበርኩ በተጨማሪም ለእንደዚህ አይነት ስሜት አዲስ በመሆኔም ስሜቱ ምን እንደሆነ አላቅም ነበር፡፡ ነገር ግን ህንድ ፊልም ላይ እንደምናየው ነገሩ ቀስ በቀስ ፍቅር መሆኑ እየገባኝ መጣ፡፡

በእየቀኑ ምሳ ስትበላ፣ ስትጫወት፣ ወደ ቤቷ ስትሄድ በቅርብ ዕርቀት እከታተላታለው፡፡ ነገር ግን በዛ በልጅነት አንደበት ማን ቀርቦ ያውራ? ዝም ብቻ፡፡

ይህ ስሜት ቀስ በቀስ የውስጥ መንፈሴን እየጎዳኝ መጣ፡፡ ለወትሮው ተጫዋች የነበርኩ ልጅ አሁን መቆዘም ትልቁ ስራዬ ሆነ፡፡ ትምርቴንም እየደከምኩ መጣው፡፡ በፍቅሯ መነደፌን ከጓደኛዬ #ወገን በስተቀር ማንም እንዳያውቅብኝ ብጥርም የማሳያቸው ያልተለመዱ ባህሪያት ሚስጥሬን አደባባይ አወጡት፡፡ አብዛኞቹ የክላሴ ልጆች እንዲሁም የፀጊ ጓደኞች እና እራሷ ፀጊ ጭምር እሷን ማፍቀሬን ደረሱበት፡፡ ይህ ደሞ ይበልጥ ኑሮን አከበደብኝ፡፡

ማንኛውም ሰው እኔን እያየ ከተጫወተና ከሳቀ በፍቅሬ ያፌዘና ያላገጠ መስሎ ይሰማኝ ጀመር፡፡ በቃ በሰዓቱ እራሴን ሙሉ በሙሉ እሷን በማለምና በመፈለግ ውስጥ አጣውት፡፡

ከወገን ውጪ ቀርቤ የማወራውም የማማክረውም ጓደኛ አልነበረኝም፡፡ ት/ት ቤት ስሆን ከእሱ ጋር እቤት ስሆን ከግጥም ደብተሬ ጋር ሆነ ግዜዬን የማሳልፈው፡፡ በሰዓቱ የግጥም ደብተሬ የምለው አሁን ላይ ግጥም የሚለውን መጠሪያ ለመያዝ ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በእዛን ወቅት ስለሷ የሚሰማኝን እና ለእሷ መንገር አለብኝ ብዬ የማስበውን በሙሉ ለእኔ ብቻ ትርጉም በሚሰጡ ቃላት የማሰፍርበት፣ የምተነፍስበት ጓደኛዬ ነበር፡፡......4
@Yewqetabugida67
8 views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 10:57:36 #የፍቅር_አቦጊዳዬ
#ክፍል 2
በሰዓቱ እረፍት አልቆ ተደውሎ ስለነበር እሷ ከጓደኞቿ ጋር እየሮጠች ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡ እኔም በወደኩበት ከእይታ እስክትርቅ ድረስ በአይኔ ሸኘዋት፡፡

ክላስ ገብቼ ልክ እንደሌሎቹ ደብተር አውጥቼ እስክርቢቶ በእጄ ይዣለው፡፡ ነገር ግን በአእምሮዬ ከደቂቆች በፊት አይኔን ስለወጋኝ ውበት እያሰላሰልኩ ነው፡፡ "ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? ስሟ ማነው? እንዴት እስከዛሬ አላየዋትም? " በዛች ቅፅበት ፍቅርን አዝለው ወደ አእምሮዬ የመጡ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

እንዳያልቅ የለም ቀሪው የት/ት ክፍለ ግዜ አልቆ ምሳ ተደወለ፡፡ ምሳ አብሬው ምበላ፣ ወደቤት የሆነ መንገድ ድረስ አብሬው የምሄድ፣ አብዛኛውን ግዜዬን አብሬው ማሳልፈው #ወገን የሚባል ጓደኛ ነበረኝ፡፡

እናም ምሳ እየበላን "ስማ ቅድም አባሮሽ ስንጫወት እኔ እንዳባራት የተሰጠችኝን ልጅ ታቃታለህ እንዴ?" ብዬ ጠየኩት፡፡

"እእእእእ ፀገነትን ነው? አዎ" በማለት መለሰ፡፡

"ፀገነት ነው ስሟ! ማለት ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? የነማን ጓደኛ ናት? ምሳ የት ነው ምትበላው?" በማለት ስለሷ ለማወቅ እንደጓጓው በሚያሳብቅ መልኩ የጥያቄ ናዳ አወረድኩበት፡፡

እሱም "እንደኛው ሰባተኛ ነች፡፡ ሰፈሯ ከእኔ ሰፈር ብዙም አይርቅም፤ ቅርብ ለቅርብ ነን፡፡ እና ቆንጆ ነች፡፡" አለ እየሳቀና በእጁ መታ እያደረገኝ፡፡

ወዳው እንዴት እንደሆነ በማላውቀው መልኩ ውስጤ እሷን እሷን ሲለኝ ተሰማኝ፡፡ "ምሳ የት ነው ሚበሉት?" አልኩት፡፡

እሱም በልተን እንጨርስና እወስድሀለው ብሎ የሚበሉበት ቦታ ወሰደኝ፡፡ የመማሪያ ክላስ ሲሆን ግድግዳው በጠፍጣፋ ጣውላ ተደርድሮ የተሰራ ነው፡፡ በጣውላና ጣውላው መካከል ባላው ቀዳዳ አጮልቄ እንዳይ ጠቆመኝ፡፡ አዎ #ፀጊ ከሶስት ጓደኞቿ ጋር ምሳዋን እየበላች ነበር፡፡ በሰውነት ሁሉም ይበልጧታል፡፡ በመልክ ግን አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ትቦንሳቸዋለች፡፡ ስትስቅ ደሞ ላለመሳቅ ቀጠሮ የያዘ ሰውም ቢሆን ፈገግ ይላል፡፡ በቃ እንዴት እንደሆነ ባላቅም ገና በ14 አመቴ ፍቅር ይዞኛል፡፡ ግን ፍቅር ምንድን ነው? አላቅም!!!....... ፫
@Yewqetabugida67
18 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 22:22:28 #የፍቅር_አቦጊዳዬ
#ክፍል1

በወቅቱ እንደማንኛውም ታዳጊ ጨዋታን አብዝቼ የምወድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ በትምርቴ ከ1-10 ባለው ደረጃ እወጣ ነበር፡፡ በብዛት 4ኛ እና 5ኛ የኔ ደረጃዎች ነበሩ፡፡ ከዛ በዘለለ ግን ሙሉ ቀን ሙሉ ለሊት ስጫወት በውልና ባድር ጨዋታ የማልሰለች ልጅ ነበርኩ፡፡

ከቀኖች ሁሉ በቅጡ በማላስታውሰው በአንዱ ቀን ከተወሰነ የት/ት ክፍለ ግዜ በኀላ ለእረፍት ተለቀን ከተወሰኑ ተማሪዎች ጋር ተመራርጠን አባሮሽ እየተጫወትን ነው፡፡

በሰዓቱ እኔ አባርሬ እንድይዝ የተሰጠኝ አንዲት ቀይ ቀጠን ያለችን ልጅ ነበር፡፡ ልጅቷን ከዚህ በፊት ልብ ብዬ አይቻት አላቅም፤ ስሟንም ሰምቼው አላቅም፡፡ ጨዋታው ተጀመረና እኔ ነብር እሷ ሚዳቆ ሆነን በረጅሙ የት/ቤታችን የሳር ሜዳ ላይ ያዝኩሽ አመለጥኩህ ሩጫ ያዝን፡፡

ልይዛት በጣም እቀርብና በድንገት የእኔ ፍጥነት ቀንሶ የእሷ በመጨመር ታመልጠኛለች፡፡ ከብዙ ልብ አፍርስ ሩጫ በኀላ ከነብር እጅ ሚያመልጥ የለምና ሚዳቆዋን ያዝኳት፡፡ ነገር ግን እሷ ልታመልጠኝ እኔም ይዣት ለማስቀረት ስንሞክር እኔ በእሷ ላይ ወደቀን ተገኘን፡፡

ዩኒፎርሟ እንደመገላለጥ ብሎ ነበርና እንደማፈር ብላ ልብን በሚያቀልጥ ሁኔታ በእነዛ ሁለት አይኖቿ ለመጀመሪያ ግዜ አይኖቼን ተመልክታ እየተሽኮረመመች ከመሬት ተነስታ ሄደች፡፡ በዛች ቅፅበት ያቺ ቀጭን ቀይ ቆንጆ የመጀመሪያ ፍቅሬ ልትሆን ሳታስፈቅድ ወደ ልቤ ዘልቃ ገባች። ክፍል ሁለት ይቀጥላል
6 views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 17:05:20
ቸሩ የእኔ ጌታ መሃሪ ይቅር ባይ
ከክፉው ወረርሽኝ ከኮሮና ቫይረስ
ከባህሩ ስጥመት ድልድይ ሆነህ
ከጥፋት ከልለህ ትላንት ካሻገርከኝ
በሰላም በጤና ዛሬ ላይ አኑረህ
ተመስገን ጌታዬ ነገም አንተ አለህ
የዘመናት ሠሪ የዓመታት አባት
ሁሉን አሳላፊ አልፋና ኦሜጋ
ያለፈውን ዘመን ደግሞ እንዳይመጣ
በምሕረትህና በቸርነት ይለፍ
እውነተኛ መሪ መንጋውን ሰብሳቢ
ከሃሳዊ መሲህ ተዋህዶን ጠባቂ
አሁንም አድለን እንባ አባሽ መሪ
ዘመነ ማቴዎስ ዘመነ ፍሥሃ ! ፡፡



@Yewqetabugida67
68 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 17:01:56 . #እንቁ_ጣጣሽ
​​ "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?

ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡

በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡

ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡

ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡

አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡

#መልካም_አዲስ_አመት_ይሁንልን
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

@Yewqetabugida67
64 views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:35:28 ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንትና የድርጅቱ ሰራተኞቹን ሰብስቦ የማነቃቂያ ንግግር አደረገ በንግግሩም ደጋግሞ የተጠቀመው ቃል የማይቻል ነገር የለም #ይቻላል ብሎ ንግግሩ ቋጨ፡፡ በመጨረሻም ጥያቄ ያለው ሲል በመስሪያ ቤቱ አዝግ በሚል ቅጽል ስም የሚጠራ ሰራተኛ እጁን አወጣ ኃይሌም እድሉን ሰጠው፦ "አመሰግናለሁ ሻለቃ እንደው ደፈርከኝ አትበለኝና ብሎ በንግግርህ ደጋግመህ ይቻላል ይቻላል ስትለን ነበር ግን ከምር ሁሉ ነገር ይቻላል???? " ሲል ኃይሌም ቀበል አርጎ "ከሞከርክ ሁሉም ይቻላል" አለው፡፡ ሰራተኛው ግን አልተዋጠለትም እንግዳው ሁሉም የሚቻል ከሆነ አንድ ነገር አድርግልኝ እኔ አልቻል ስላለኝ ነው ሲል ፣
ሻለቃ ኃይሌም፦ ኮስተር ብሎ ምንድነው እሱ አለው??
ሠራተኛው ፦ "ይቻላል የሚለው ቃል ይበልጥ እንዲገባን እዚህ ግድግዳ ላይ ውኃን በፕላስተር አጣብቀህ/አንጠልጥለህ ይዘህ አሳየን"ሲል
ሻለቃ ኃይሌ፦ ከመልሱ በፊት "እኔ ምለው አንተ የእኔ ሠራተኛ ነህን ??? አላለም ፡፡
መልካም የእሁድ ቀትር
Join & shsre @yewqetabugida67
39 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 09:45:12 #በዓለም_ላይ_3_ዐይነት_ሰዎች_አሉ!

1, የተቀመጡ ሰዎች
2, የተሰረቁ ሰዎች
3, ባለ ራዕይ ሰዎች

#የተቀመጡ_ሰዎች

የሚባሉት ህይወትን በ TV ነው የሚያዩት፣ ትችትን ፣ ነቀፌታን ፣ተግዳሮት የማይፈልጉ ፣ አሸናፊነትንም ሆነ ሀላፊነትን አይወዱም ባአጠቃላይ [Challenge Life] አይፈልጉም።

#የተሰረቁ_ሰዎች

ሌላዉን መስሎ መኖር ምኞታቸው ነው። የራሳቸው የሆነ አቋምም ሆነ ማንነት የላቸውም። የተሰረቀ ሰው ራሱን ከሌላ ጋር እያወዳደረ ነው የሚኖረው።

#ባለራዕይ_ሰዎች

ነፃ እና ተፈጥሯዊ ሰዎች ናቸው። የበታችነት ስሜት አይሰማቸውም!! መተባበር፣ ፍቅር እና ማህበራዊ ተቆርቋሪነት መገለጫቸው ነው።እነዚህ ሰዎች በቅድሚያ፦
ማህበረሰቡን
ሲቀጥል ቤተሰባቸው
በመጨረሻ ራሳቸዉን የሚያስከትሉ ናቸው።

እንዲህ አይነት ሰው ካርታውን ያለማጭበርበር የሚጫወት እንጂ የሚያሸንፍ አይደለም።

ሁሉም ጥሩ ይሆናል ዋናው ነገር ሰላምና ጤና

@Yewqetabugida67
256 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 23:01:00
ባለ ጊዜ ጉልበተኛ አልጠግብ ባይ ስትሆንና ቀን ሲጥልህ መራመድ ሲያቅትህ

@Yewqetabugida67
250 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 16:57:24 ✤ሰው እንጂ እግዚአብሔር አልረሳኝም✤ መርሣት የባህሪውም አይደለምና፦
በጸሎት ኃይል የሚያምን አምኖም የሚተጋ አንድ ፅኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደኃ ፣የሚበላውን የሚቸገር ረሃብተኛ ፣ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርብ ሆኖ ይታዘብ የነበረው ወዳጁ እንዲህ አለው ‹ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማስገኘት ካልቻለ የመጸለይህ ትርጉም ምንድር ነው? በቃ ፈጣሪህ አልሰማህም ማለት ነው!› ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያ ምስኪን ክርስቲያን ግን እንዲህ ሲል መለሰለት ተሣስተሃል ‹እግዚአብሔርማ አልረሳኝም! ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ ነግሮት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን ይህ ሰው ረስቶኛል!!!›
ክርስቲያኖች ለምን አንዳንዶች ከዕለት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ እንጀራ ያጣሉ? መቼም ‹ለሰው ፊት የማያዳላ› እግዚአብሔር አድልዎ ኖሮበት ነው አትሉም?! (ሐዋ. 10፥34) ይህስ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙት ምንም የሌላቸውን በመርዳት እና በመመገብ በባሕርይው መግቦትን ገንዘብ ያደረገውን አምላክ በጸጋ እንዲመስሉትና በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡
ስለዚህ ‹የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ› ብለን የለመንነው አምላክ ከዕለት እንጀራችን አትርፎ የሚሰጠን ይህን አምላካዊ አደራ እንድንወጣም ስለሚፈልግ እንደሆነ ብንረዳው እንዴት መታደል ነበር!!!
★በዚህ ዓለም በዚህ ዘመን ሰው ዝም ብሎ ራሱ ተስፋ ቆርጦ ሰውን ተስፋ ቢስ የሚያደርግ ሙሉ ነው፡፡ ነገር ግን ወዳጄ ምንም ጊዜ ምንም ይሁን ምን ሰውን ያለቦታው የሚያውሉ ያላዩትን የሚናገሩ ዝም ብለው ስም የሚያወጡ በመሰለኝ የሚናገሩ አሉና እንዳትሰማ ፦
" #ሰው ሲጨርስ እግዚአብሔር እንደገና ይጀምራል፤ #ፈጣሪ ሰው አይደለማ " ፡፡ ተስፋ ሕይወት ነው ተስፋ ጠል ነው ተስፋ አያልቅም ጅረት ነው ....
ደስ የሚል የተስፋ ቀን ይሁንልን ፡፡
#የእውቀት አቡጊዳ

@Yewqetabugida67
274 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ