2021-02-16 21:32:25
#አንበሣን_ያሸነፈች_ብልህ_ሴት
#Bad_time_story
በድሮ ጊዜ አንድ ባሏ የሚበድላት ሴት ነበረች፡፡ ባልዋም ሁልጊዜም ይደበድባት ነበር፡፡ የሚፈልገውን ሁሉ ብታደርግለትም ሁልጊዜ ስለሚደበድባት በጣም ትቸገር ነበር፡፡ ከዛም ዘመድ አዝማዶቿን ሰብስባ “ሁልጊዜ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ አደርግለታለሁ ፤ እርሱ ግን ሁልጊዜ ይደበድበኛል ፤ እንደው ምን ባደርግ ይሻለኝ ይሆን?” ብላ መላ እንዲፈልጉላት ስታማክራቸዉ እነርሱም ተመካክረዉ ‹‹አንድ ብልህ ሰው አለ እሱ ዘንድ ሂጂ ፤ መድሃኒት ያገኝልሻል›› አሏት፡፡
እሷም የተባለቺዉን ብልህ ሰዉዬ ጋር ሄደች፡፡ እርሱም “ችግርሽ ምንድነው?” ብሎ ጠየቃት
#እሷም ችግሩዋን ነግራዉ ፤ ለዚህ ምን መፍትሔ ማግኘት እችላለሁ” ስትለዉ እሱም “እዚህ ምንም መፍትሔ የለም ፤ ምንም አይነት መድኃኒት ልሰጥሽ አልችልም ፤ ከቻልሽ ግን የአንበሣ ቅንድቦች ብታመጪልኝ አንድ ነገር አደርግልሻለሁ፡፡” አላት፡፡
ይህንን ስትሰማ በጣም ፈራች ነገር ግን ከባሏ ድብደባም መገላገል ስለፈለገች ፣ የአንበሣ ቅንድቦች እንዴት ላገኝ እችላለሁ? ብላ ማሰብ ጀመረች፡፡ ከዚያም አንዲት ፍየል አርዳ ስጋዋን ወደ ጫካ ይዛዉ ሄደች፡፡ ከዛም አንበሣ ሊያገኛት ከማይችልበት ዛፍ ላይ ወጥታ ተቀመጠች፡፡ በመጀመሪያውም ቀን ትልቅ ሥጋ ለአንበሣው ወረወረችለት ፤ አንበሳዉ በልቶ ሄደ ፤ ይህንንም በተከታታይ ለሰባት ቀናት አደረገች፡፡ አንበሳውም በተደጋጋሚ የሚወረወርለትን ሥጋ እየበላ ወደመጣበት ይመለሳል፡፡
በሰባተኛው ቀን ብዙ ስጋ ስለሰጠቺዉ ስጋዉን ከበላ ቡሃላ እዛዉ እሷ ካለችበት ዛፍ ስር እንቅልፍ ወሰደዉ፡፡ ከዛም መተኛቱን ካረጋገጠች ቡሃላ ቀስ ብላ ከዛፉ ላይ ወርዳ እሱ በተኛበት ቅንድቦቹን ቆርጣ ወደ ብልሁ ሰው ዘንድም አመራች፡፡ እሱም “እንዴት ልታመጪ ቻልሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“ለሰባት ቀናት ያህል የፍየል ሥጋ ስወረውርለት ቆይቼ በመጨረሻም ቀን እንቅልፍ ሲጥለው ቅንድቦቹን ቆርጬ አመጣሁ” አለችው፡፡
#ብልሁም_ሰው “ታዲያ አንበሳን ያሸነፍሽ መለኛ ሴት ሁነሽ ባልሽን ማሸነፍ እንዴት ያቅትሻል?! በይ ባልሽንም የምታሸንፊው ልክ እንደዚህ ነው፡፡ ሌላ መፍትሔ የለውም እሱ እንደሚፈልገው በመሆን በዘዴ ያዢው” አላት ይባላል፡፡
ከተመቻቹ ለሚወዱት ሰዉ ያጋሩ
@Yewqetabugida67
201 views18:32