2021-02-20 17:44:46
ከእለታት ሁለት ቀን እንዲህ ሆነ
አንዲት ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ አረገዙ።
ከሦስት ወራት በኋላ ውሻይቱ ስድስት ቡችላ ወለደች።
ከስድስት ወራት በኋላ ደግሞ እንደገና ውሻይቱ አረገዘች።
በዘጠኝ ወር ውስት እንደገና ስድስት ቡችላ ደገመች።
እንዲህ እያለ ጉዳዩ ቀጠለ።
በአስራ ስምንተኛው ወር ውሻይቱ ለዝሆኗ ጥያቄ ጠየቀች።
"እርግጠኛ ነሽ እርጉዝ ነሽ? ሁለታችንም በተመሳሳይ ጊዜ
እርጉዝ ነበርን እኔ ለሦስተኛ ጊዜ ነፍ ቡችላ ወለድኩ።
እንደምታያቸውም ልጆቼ አድገውም ትላልቅ ውሻ ሆነዋል
ነገር ግን አንቺ እስካሁን እርጉዝ ነሽ ምን እየተካሄደ ነው?"
ብላ ውሻይቱ ዝሆኗን በጥያቄ አጠደፈቻት።
ዝሆኗም ረጋ ብላ መመለስ ጀመረች "የሆነ ነገር እንዲገባሽ
እፈልጋለው። እኔ የተሸከምኩት ነገር ቡችላ አይደለም። እኔ
የተሸከምኩት ዝሆን ነው። እሱንም በሁለት ዓመት ውስጥ
አንዴ ብቻ ነው መውለድ የምችለው። እና ግን የወለድኩት
ዕለት አንዴ ብቻ መሬቱን ሲረግጠው ምድር ሁሉ
ይሰማታል። የኔ ልጅ መንገድን ሲያቋርጥ የሰው ልጅ ቆሞ
በአድናቆት ያየዋል። እናም ምን ልልሽ ፈልጌ መሰለሽ እኔ
የተሸከምኩት ነገር በጣም ጠንካራ እና ታላቅ የሆነ ነገር
ስለሆነ ፅሞና እና ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡"
=============
እናም ጌታው ከጎንህ ያለው ሰው ሺ ጊዜ ውጤት ያመጣ
ቢመስልህ የራስህ እቅድ እና ውጥን ላይ ተስፋ
እንዳትቆርጥ። በፍፁም በሌላ ውጤት እንዳትቀና።
ሁሌም በልብህ "የኔ ጊዜ ይመጣል" በል ጊዜው ደርሶ
የአንተ ጊዜ መሬት ሲረግጥ ያኔ አንተን አያድርገኝ ልክ
እንደዝሆን ልጅ መንገዱን ሲያቋርጥ ሰው ቆሞ በአድናቆት
እንደሚያሳልፈው ያኔም ሰው ሁሉ ለአንተ አድናቆት ይቆማል። ለአንተ የፈለከው ነገር በቶሎ በቶሎ ብታገኝም እኔም የፈለኩት ነገር አሻሽሎ አምሮና አስተካክሎ ስለሚሰጠኝ ነው እንጂ ረፍዶበት አቅቶትም እንዳይመስልህ አይደለም ፈጣሪ ለልጁ ዘይግይቶ ወይም አርፍዶ አያውቅምና፡፡ አንድ አባባል አለች ሁሌም ደስ ምትለኝ ፦ #እናት ለህጻን ልጇ ሥጋ ከእነ አጥንቱ አትሰጠውም ይወጋዋል ብላ ስለምታስብ መርምራ ወይም አኝካ ነውና ምትሰጠው፣ አምላክም ግን ከዚህም በላይ ለልጆቹ ያማረውን የተሻለውን ስለሚሰጥ ፈልጎ እንጂ ያልበሰለ ፍሬ አድሎ አያውቅም፡፡
ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ !
#እውቀት አቡጊዳ
215 views14:44