2021-04-13 13:28:06
#ሁሉም_የሞላለት_ስለሌለ_ሁሉም_የጎደለበትም_የለም
በአንድ የቻይና የገጠር መንደር የሚኖሩ አንድ ጎልማሳ ሰው ነበሩ
ሁሌም ታዲያ ማልደው በመነሳት ውሃ ሊቀዱ ወንዝ ይወርዳሉ፣ሆኖም ያሉዋቸው ሁለት ከሸክላ የተሰሩ የውሀ ማሰሮዋች ሲሆኑ
አንደኛው አዲስ ሲሆን ሌላኛው ግን ሰባራ ነው በዚህ ምክንያት
ውሃ ቀድተው ቤት ሲደርሱ አዲሱ ሙሉ ውሃውን እነደያዘ ቤት ሲደርስ ሰንጥቅ ያለበት አሮጌው ግን ግማሹን አፍሶ ግማሹን ደግሞ ይዞ ነው የሚገኝው በዚህ ምክንያት የሚያፈሰው አሮጌ
ማሰሮ ሁሌም እኚህ ሰውዬ ለምን እንደማያድሱት እያጉተመተመ
ከጓደኛው በማነሱ እየተሸማቀ ይኖር ነበር ::
አንድ ቀን የራሱ ተፈጥሮው በጣም ስላስጠላው ይህ እንዲሆን ለምን እንደፈቀዱ አፍ አውጥቶ ጌታውን በምሬት ጠየቀ :: አዛውንቱ ሰውዬም ሲመልሱለት ” ተፈጥሮህን ለምን ታማራለህ የምንሄድበትን መንገድ ተመልክተኸው ታውቃለህ በአንተ አቅጣጫ ያለው መሬት ሁሌም ለምለም ነው በሚያምሩ አበቦች የተሸፈነ ነው በጓደኛህ በኩል ያለው ግን ደረቅና አቧራማ ነው ይሄ አንተ በማፍሰስህ ምክንያት የመጣ ነው እነዚህ አበቦች ለአካባቢው ጌጦች የሳሎን ማድመቂያ ናቸው ህይወትን ያድሳሉ ::
በዚህ አለም ሁላችንም ብንሆን ከጉደለት ጋር ነው የተፈጠረነው አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ዋናው ነገር ከሌላው በማነፃፀር የራስን ተፈጥሮ በመጥፎ መሳልና ማማረር ተገቢ አይደለም ከዛ ተፈጥሮ የሚገኝን በጎ ነገር ማየትና ያንን ማድነቅ ያስፈልጋል “ ብለው መለሱለት ።
ሞራል : — ሁሌም ቢሆን አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ራስን ዝቅ አድርጎ ተፈጥሮን ማማረር ተገቢ አይደለም ።
#ሁሉም_ሙሉ_የሆነለት_የለም_ሁሉም_ደግሞ_የጎደለበት_የለም_ሙሉውን_በጎዶሎ_ጎዶሎውን_እየሞሉ_መኖ
#የበለጠ_ያግኙ
@Yewqetabugida67
180 views10:28