Get Mystery Box with random crypto!

#መስታወት_ፊት_ቆሜ_እንዲህ_እላለሁ #አው_ደግሜ_እላለሁ 'በለስ ፍሬ ባትሰጥ | 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

#መስታወት_ፊት_ቆሜ_እንዲህ_እላለሁ
#አው_ደግሜ_እላለሁ

"በለስ ፍሬ ባትሰጥ፣ ሎሚ መሽተት ቢሳናት
ኤሊ ላባ ብትለብስ፣ ወፌን ድንጋይ ቢጫናት
ሰማይ እንዳለት ቢወቀር
ጊዜ ደክሞት ቆሞ ቢቀር
ጨረቃ አመድ ብትቅም
ፀሐይ ጥርሷን ብትለቅም

ስልጣኔን ነቀዝ በልቶት፣ ኦና ቢሆን አገር ምድሩ
ፒራሚዶች ባንድ ሌሊት፣ የኩበት ክምር ሆነው ቢያድሩ
ተፈጥሮ ለሕዝብ ቅነሳ
ሰው በሰው ላይ ብታስነሳ
አንዱ ካንዱ ቢተራረድ
ጠፈር በከል ቢጋረድ

ሙሴን ባሕር ቢበላው፣ የኖህ መርከብ ቢሰጥም
ሕይወት ምስጢር ባትገልጥም
የድል ድርሻየን ጥዋ፣ ጭላጭ ሳይቀር እስካጣጥም
የምሻውን እስከማገኝ፡ ለመሽነፍ እጅ አልሰጥም
እንኳን ተስፋ፣ ጢም አልቆርጥም።

በእውቀቱ ስዩም

@Yewqetabugida67