Get Mystery Box with random crypto!

🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

የቴሌግራም ቻናል አርማ wbfqr — 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷
የቴሌግራም ቻናል አርማ wbfqr — 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷
የሰርጥ አድራሻ: @wbfqr
ምድቦች: ሽያጭ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 507

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-07 08:24:27 . #ድንቅ_እናት

ባለቤቷ ከሞተ በኋላ ልብሱን ቁም ሳጥን ውስጥ አንጠልጥላው በየጊዜው ገንዘብ ታስቀምጥበታለች ። ልጆቿ ለተለያየ ጉዳይ ወጪ ሲጠይቋት ሂዱ ቁም ሳጥን ውስጥ
ከአባታችሁ ደረት ኪስ ውሰዱ ትላቸዋለች "
እነሱም የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ቆጥረው ከአባታቸው ኪስ ይወስዳሉ ከዕለታት አንድ ቀን ልጆቹ እናታቸውን ለምን እንደዚህ እንደምታረግ ሲጠይቋት የአባታችሁ ሩህሩህነትና ለጋስነት እንድታውቁትና አባታችሁ እዛም ሆኖ ለእናንተ እንደሚጨነቅ እንድታውቁ (አባት የሞተበት ) ነን ብላችሁም እንዳታስቡ ለማስታወስ ነው!::

#አስተዋይ_እናት_ትምህርት_ቤት_ናት_የምንለው_ለዚህ_ነው!::


@Yewqetabugida67
206 views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 12:33:32
#እኛ_አበሾች_ስንተባበር

@Yewqetabugida67
293 views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 16:12:13
#ሁሉም_የሞላለት_ስለሌለ_ሁሉም_የጎደለበትም_የለም

በአንድ የቻይና የገጠር መንደር የሚኖሩ አንድ ጎልማሳ ሰው ነበሩ
ሁሌም ታዲያ ማልደው በመነሳት ውሃ ሊቀዱ ወንዝ ይወርዳሉ፣ሆኖም ያሉዋቸው ሁለት ከሸክላ የተሰሩ የውሀ ማሰሮዋች ሲሆኑ
አንደኛው አዲስ ሲሆን ሌላኛው ግን ሰባራ ነው በዚህ ምክንያት
ውሃ ቀድተው ቤት ሲደርሱ አዲሱ ሙሉ ውሃውን እነደያዘ ቤት ሲደርስ ሰንጥቅ ያለበት አሮጌው ግን ግማሹን አፍሶ ግማሹን ደግሞ ይዞ ነው የሚገኝው በዚህ ምክንያት የሚያፈሰው አሮጌ
ማሰሮ ሁሌም እኚህ ሰውዬ ለምን እንደማያድሱት እያጉተመተመ
ከጓደኛው በማነሱ እየተሸማቀ ይኖር ነበር ::

አንድ ቀን የራሱ ተፈጥሮው በጣም ስላስጠላው ይህ እንዲሆን ለምን እንደፈቀዱ አፍ አውጥቶ ጌታውን በምሬት ጠየቀ :: አዛውንቱ ሰውዬም ሲመልሱለት ” ተፈጥሮህን ለምን ታማራለህ የምንሄድበትን መንገድ ተመልክተኸው ታውቃለህ በአንተ አቅጣጫ ያለው መሬት ሁሌም ለምለም ነው በሚያምሩ አበቦች የተሸፈነ ነው በጓደኛህ በኩል ያለው ግን ደረቅና አቧራማ ነው ይሄ አንተ በማፍሰስህ ምክንያት የመጣ ነው እነዚህ አበቦች ለአካባቢው ጌጦች የሳሎን ማድመቂያ ናቸው ህይወትን ያድሳሉ ::
በዚህ አለም ሁላችንም ብንሆን ከጉደለት ጋር ነው የተፈጠረነው አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ዋናው ነገር ከሌላው በማነፃፀር የራስን ተፈጥሮ በመጥፎ መሳልና ማማረር ተገቢ አይደለም ከዛ ተፈጥሮ የሚገኝን በጎ ነገር ማየትና ያንን ማድነቅ ያስፈልጋል “ ብለው መለሱለት ።

ሞራል : — ሁሌም ቢሆን አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ራስን ዝቅ አድርጎ ተፈጥሮን ማማረር ተገቢ አይደለም ።
#ሁሉም_ሙሉ_የሆነለት_የለም_ሁሉም_ደግሞ_የጎደለበት_የለም_ሙሉውን_በጎዶሎ_ጎዶሎውን_እየሞሉ_መኖ

#የበለጠ_ያግኙ
@Yewqetabugida67
375 views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 17:38:55 #ምክር_ለወዳጅ


በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል።

ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው! በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፤ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።

የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ
ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል።

ዓይንህ የፊቱን ቢያይ፤ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ፤ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው።

ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት።

ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው።

ለሀብታም አትሳቅ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን፣ ነገርህን በልክ፣ ቃልህን በጣዕም፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው።

እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ።

ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም።

በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ።

የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ነገ ከመምጣቱ በፊት ቀድመህ አስብ ።

@Yewqetabugida67
173 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 12:46:07 . #ድንቅ_እናት

ባለቤቷ ከሞተ በኋላ ልብሱን ቁም ሳጥን ውስጥ አንጠልጥላው በየጊዜው ገንዘብ ታስቀምጥበታለች ። ልጆቿ ለተለያየ ጉዳይ ወጪ ሲጠይቋት ሂዱ ቁም ሳጥን ውስጥ
ከአባታችሁ ደረት ኪስ ውሰዱ ትላቸዋለች "
እነሱም የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ቆጥረው ከአባታቸው ኪስ ይወስዳሉ ከዕለታት አንድ ቀን ልጆቹ እናታቸውን ለምን እንደዚህ እንደምታረግ ሲጠይቋት የአባታችሁ ሩህሩህነትና ለጋስነት እንድታውቁትና አባታችሁ እዛም ሆኖ ለእናንተ እንደሚጨነቅ እንድታውቁ (አባት የሞተበት ) ነን ብላችሁም እንዳታስቡ ለማስታወስ ነው!::

#አስተዋይ_እናት_ትምህርት_ቤት_ናት_የምንለው_ለዚህ_ነው!::


@Yewqetabugida67
191 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-18 09:21:08
You will always have more of what you complain about, and more of what you appreciate. The principle behind this is, whatever you focus on increases.

I know you want more, but be grateful for the ones you have. Learn to appreciate the things you have before it becomes what you had.

Don't wait to have everything you desire before you become grateful for what you have, rather be grateful for what you have so you can have everything you desire.

ከሌለን ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለን ነገር ይበልጣል። "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ..ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ መልካም ነገሮች አሉ።

ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን። በሰላም ውሎ በሰላም ማደር እጅግ ትልቅ ነገር ነው።አዲስ ቀን አዲስ ህይወት ነው።

አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል።

ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን በመኖርህ ብቻ ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት።

ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!

መልካም ነገር ሁሉ ይድርሰን

@Yewqetabugida67
260 views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 07:33:05
240 views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 07:32:17
#መልካም_አዲስ_ዘመን_ለሁላችሁም
235 views04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-23 08:59:02 #እነሆ_የሕይወት_ስንቅ

ያንድ ወቅትችግር የቀሪ ሕይወትህን ደስታ እንዲያበላሸው አትፍቀድለት፤ሕይወትንም ባስቸጋሪው ወቅት በነበረህ መነፅር አትያት፤በአንድ ክፉ አጋጣሚ ወክለህም አትመልከታት፤ ይልቁንም በአስቸጋሪ ጊዜ ነገም ሌላ ቀን ነው ብለህ ጽና እናም የተሻለው ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኛ ሁን።

«በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆንህን ስትረዳ መጥፎ ነገርን ፍራ። በመጥፎ ሁኔታ ላይ መሆንህን ስትረዳ ጥሩ ነገር ተስፋ አድርግ ,,,,,,ብዙ ሰዎች ሞትን እየፈለጉ ኖረዋል። መኖርን እየፈለጉ ሞተዋልና»

ህይወት እንደ መሰላል ነች፤ መውጣት መውረድ የበዛባት ። ዛሬ ተሳክቶልን እየረገጥነው የወጣነውን ነገ ቀን ይቀየርና ዝቅ ብለን እየጨበጥነው እንወርዳለን ። ስንረግጥም ስንጨብጥም በልክ ይሁን!




@Yewqetabugida67
165 views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-10 07:17:26 ​#ፈጣሪ_አህያን_ፈጠረና_እንዲህ_አለው….
አህያ ትሆናለህ፡፡ ሸክሞችን በጀርባህ በመሸከም ፀሐይ ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ያለመታከት ትሰራለህ። የምትመገበው ደግሞ ሳር ነው፡፡ ምንም አይነት ኢንቴለክት(የማሰብ፣የማመ ዛዘን ችሎታ) የለህም፡፡ እናም 50 ዓመት ትኖራለህ፡፡
አህያው እንዲህ ሲል መለሰ…
አህያ እሆናለሁ ችግር የለውም ነገር ግን 50 ዓመት በጣም ብዙ ነውና ሃያውን ብቻ ስጠኝ፡፡ እግዚያብሔርም የፍላጎቱን ሰጠው፡፡
✰ ✰ ✰
#ፈጣሪ_ውሻን_ፈጠረና_እንዲህ_አለው….
የሰውን ልጅ ቤት ትጠብቃለህ፡፡ የሰው ልጅም እውነተኛ ጓደኛ ትሆናለህ፡፡ ከጌታህ የሚጣልልህን ፍርፋሪ ትመገባለህ፡፡ እናም 30 ዓመት በሕይዎት ትኖራለህ፡፡ ውሻም ትባላለህ፡፡
ውሻው ሲመልስ…
ጌታየ 30 ዓመት እጅግ ብዙ ነው አስራ አምስቱ ዓመት ይበቃኛል አለ፡፡ ፈጣሪም የፍላጎቱን ሰጠው…
✰ ✰ ✰
#ፈጣሪ_ዝንጀሮን_ፈጠረና_እንዲህ_አለው….
ዝንጀሮ ትሆናለህ፡፡ በዛፎች ቅርንጫፍ ወዲያና ወዲህ እየተንጠላጠልክ ትርኢት ትሰራለህ፡፡ በድርጊትህም አስገራሚ ትሆናለህ እናም 20 ዓመት ትኖራለህ፡፡ ዝንጀሮው ሲመልስ…
ሃያ ዓመት መኖር በጣም ብዙ ነውና አስሩ ብቻ ይበቃኛል አለ፡፡ ፈጣሪም የሚኞቱን ሰጠው፡፡
✰ ✰ ✰
#በመጨረሻም_ፈጣሪ_አዳም_ጋ_ደረሰ__ፈጠረና|እንዲህ አለው….
የሰው ልጅ ትባላለህ፡፡ በምድር ላይ ካሉት ፍጡራን አመዛዛኝ፣ አሳቢና ምክኒተዊ ፍጡር አንተ ብቻ ነህ፡፡ በሌሎች ፍጡራን ላይ ለመንገስም የማሰብ ችሎታህን ትጠቀማለህ፡፡ በሌሎች ፍጡራን ላይ ነግሰህም 20 ዓመትን ትኖራለህ አለው። የሰው ልጅ የተሰተውን የማሰብ ችሎታው ተጠቅሞ ሲመልስ…
ጌታዬ እሺ! የሰው ልጅ እሆናለሁ፡፡ ነገር ግን ሃያ ዓመት መኖር እጅግ ሲበዛ ትንሽ ነው፡፡ ስለሆነም ሠላሳ ዓመት አህያው የተቃወመውን፣ አሥራ አምሥት ዓመት ውሻው አልፈልገውም ያለውን እናም ደግሞ አስሩን ዓመት ዝንጀሮው የማይፈልገውን ስጠኝ ሲል ጥያቄውን አቀረበ (ከራሱ ጋር የሌሎችን ደማምሮ 75 ዓመት አደረሰው)፡፡ ፈጣሪም የፍላጎቱን ሰጠው…

#እናም የሰው ልጅ ሕይዎት ከዛን ጊዜ ጀምሮ 20ውን ዓመት #እንደ_ሰው ይኖራል (ሳያገባ ትዳር ሳይመሰርት ለአንድ ሆዱ ሲኖር ማለት ነው)፡፡
ከዛ በኋላ አግብቶ ትዳር ሲመሰርትና የቤተሰብ ኃላፊ ሲሆን 30ውን ዓመት ልክ #እንደ_አህያው የአህያውን ሚና ወስዶ ይኖራል፡፡ የቤተሰብ ኃላፊነቱን ይሸከማል፤ የአባወራነቱን ኃላፊነት ለመወጣትም ቀን ከሌት ያለመታከት ይሰራል፡፡ ቀጥሎም ልጆቹ እያደጉ ሲሄዱ 15ቱን ዓመት ልክ #እንደ_ውሻው አይነት ኑሮን ይመራል፡፡ ቤቱን ይጠብቃል ይንከባከባል፣ ከልጆቹ ተርፎ የሚሰጠውንም ይበላል፡፡ አርጅቶ እየሸመገለ በሄደ ጊዜም ጡረታ ይወጣና 10ሩን ዓመት #እንደ_ዝንጀሮው አኗኗር ዘይቤ ይኖራል፡፡ ልጆቹን አጎራብቶ ከአንደኛው ቤት ወደ ሌላኛው ቤት በመዘዋወር የልጅ ልጆቹን በማጫወት፣በማዝናናት ያለፉ ዘመናትን ታሪክ በማውራት ያሳልፋል፡፡
#ሕይዎት_ማለት_ይች_ናት!

@Yewqetabugida67
222 views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ