Get Mystery Box with random crypto!

#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል3 ከዛን ቀን ጀምሮ በእየቀኑ ስለሷ ማ | 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል3
ከዛን ቀን ጀምሮ በእየቀኑ ስለሷ ማሰብና መጨነቅ ስራዬ ሆነ፡፡ ት/ት ቤት፣ ሰፈር፣ ማታ አልጋዬ ላይ ተኝቼ የማስበውም የማልመውም እሷኑ ሆነ፡፡ በሰዓቱ ገና የ14 አመት ልጅ ስለነበርኩ በተጨማሪም ለእንደዚህ አይነት ስሜት አዲስ በመሆኔም ስሜቱ ምን እንደሆነ አላቅም ነበር፡፡ ነገር ግን ህንድ ፊልም ላይ እንደምናየው ነገሩ ቀስ በቀስ ፍቅር መሆኑ እየገባኝ መጣ፡፡

በእየቀኑ ምሳ ስትበላ፣ ስትጫወት፣ ወደ ቤቷ ስትሄድ በቅርብ ዕርቀት እከታተላታለው፡፡ ነገር ግን በዛ በልጅነት አንደበት ማን ቀርቦ ያውራ? ዝም ብቻ፡፡

ይህ ስሜት ቀስ በቀስ የውስጥ መንፈሴን እየጎዳኝ መጣ፡፡ ለወትሮው ተጫዋች የነበርኩ ልጅ አሁን መቆዘም ትልቁ ስራዬ ሆነ፡፡ ትምርቴንም እየደከምኩ መጣው፡፡ በፍቅሯ መነደፌን ከጓደኛዬ #ወገን በስተቀር ማንም እንዳያውቅብኝ ብጥርም የማሳያቸው ያልተለመዱ ባህሪያት ሚስጥሬን አደባባይ አወጡት፡፡ አብዛኞቹ የክላሴ ልጆች እንዲሁም የፀጊ ጓደኞች እና እራሷ ፀጊ ጭምር እሷን ማፍቀሬን ደረሱበት፡፡ ይህ ደሞ ይበልጥ ኑሮን አከበደብኝ፡፡

ማንኛውም ሰው እኔን እያየ ከተጫወተና ከሳቀ በፍቅሬ ያፌዘና ያላገጠ መስሎ ይሰማኝ ጀመር፡፡ በቃ በሰዓቱ እራሴን ሙሉ በሙሉ እሷን በማለምና በመፈለግ ውስጥ አጣውት፡፡

ከወገን ውጪ ቀርቤ የማወራውም የማማክረውም ጓደኛ አልነበረኝም፡፡ ት/ት ቤት ስሆን ከእሱ ጋር እቤት ስሆን ከግጥም ደብተሬ ጋር ሆነ ግዜዬን የማሳልፈው፡፡ በሰዓቱ የግጥም ደብተሬ የምለው አሁን ላይ ግጥም የሚለውን መጠሪያ ለመያዝ ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በእዛን ወቅት ስለሷ የሚሰማኝን እና ለእሷ መንገር አለብኝ ብዬ የማስበውን በሙሉ ለእኔ ብቻ ትርጉም በሚሰጡ ቃላት የማሰፍርበት፣ የምተነፍስበት ጓደኛዬ ነበር፡፡......4
@Yewqetabugida67