Get Mystery Box with random crypto!

#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 4 ከወራቶች በኀላ #ወገን እንዳናግራት አደፋፈረኝና ላናግራ | 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 4

ከወራቶች በኀላ #ወገን እንዳናግራት አደፋፈረኝና ላናግራት ወሰንኩ፡፡ በሰዓቱ እንደሷ የምፈራው ሰው አልነበረም፡፡ በሆነ አጋጣሚ ሳያት ከያዘችኝ የምገባበት ነበር የሚጠፋኝ፡፡ ነገር ግን የሚሰማኝን በውስጤ አምቄ ከምሰቃይ ልተንፍሰውና ይለይለት ብዬ ወሰንኩ፡፡ እንደነገ ላወራት እንደዛሬ አዳር ላይ የምላትን እና ከእሷ ሊመጡ ይችላሉ የምላቸውን ምላሾች በመገመት በድጋሚ የምላትን ከእራሴ ጋር ስለማመድ አደርኩ፡፡

አይነጋ የለም ነግቶ ት/ት ቤት ገባን፡፡ ላናግራት የወሰንኩት ምሳ ሰዓት ስለነበር እስከዛ ያለው ሰዓት በጣም እራቀኝ። ሙሉ ሰውነቴን የፍራት ካባ ሲለብሰኝ ተሰማኝ፡፡ ምሳ እንደበላን ከትምርት ቤታችን ባለ 4 ፎቅ ህንፃ እራሱን እንደሚያጠፋ ሰው 4ኛው ላይ ሁኜ አስጠራዋት፡፡ ቦታውን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ተማሪዎች በምሳ ሰዓት ስለማይበዙበት ነበር። ሌላው ደሞ በሰዓቱ ሴትን ቀጥሮ ስለማውራትም ሆነ ምቹ ስለሆኑ ቦታዎች እውቀቱ ስላልነበረኝ ነው፡፡

ከትንሽ መንቆራጠጦች በኀላ በደም ፈንታ በደም ቧንቧዎቼ የምትዘዋወረው ቆንጆ ከህንፃው መወጣጫ ደረጃዎች በአንዱ በኩል መጣች፡፡ ልክ እንዳየዋት ውስጤ ይረበሽ ጀመር፤ ማታ የተዘጋጀውበት በሙሉ እንደ ጉም ተኖ ጠፋ፡፡ አጠገቤ እንደደረሰችም ልብን በሚያቀልጠው ፈገግታዋ ሞቅ ያለ ሰላምታ ከሰጠችኝ በኀላ እንዳላወቀ ሰው "ለምን ነበር የፈለከኝ?" አለች ትኩር ብላ እያየችኝ፡፡ አይኖቼ ከአይኖቿ ጋር ሲላተሙ ይባስ እፈራትና እረበሽ ጀመር፡፡

ትንፋሽ እንዳጠረው ሰው እያቃሰትኩ "እየውልሽ #ፀጊ አፍቅሬሻለው፤ ጓደኛ እንሁን" አልኳት አንዴ እሷን አንዴ መሬቱን እያየው፡፡

"አይ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር ማሰብ አልፈልግም፤ አልችልም፡፡" አለች እጥር ምጥን ብሎ ለጆሮ በሚከብድ አማርኛ፡፡

"እሺ፤ ቻው" ብያት እኔ በአንዱ ደረጃ እሷ በሌላኛው ዳግም ላንገናኝ በሚመስል መልኩ እየተጣደፍን ሄድን፡፡ ቀጥታ ክላሴ ገባውና እራሴን ካረጋጋው በኀላ ለምን ልናገር ያሰብኩትን እንዳልተናገርኩና "አልችልም" ስትለኝ "ለማስረዳት በመሞከር ፈንታ ለምን "እሺ" የምትለው ቃል ከአፌ እንደወጣች እራሴን ጠየኩት፡፡ ለካ ከሚያፈቅሩት ሰው ፊት መቆም ለሞት ፍርድ ከመቆም ባልተናነሰ ልብን ሰልቦ በፍርሀት ይለውሳል፡፡

..... ይቀጥላል