Get Mystery Box with random crypto!

#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 2 በሰዓቱ እረፍት አልቆ ተደውሎ ስለነበ | 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

#የፍቅር_አቦጊዳዬ
#ክፍል 2
በሰዓቱ እረፍት አልቆ ተደውሎ ስለነበር እሷ ከጓደኞቿ ጋር እየሮጠች ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡ እኔም በወደኩበት ከእይታ እስክትርቅ ድረስ በአይኔ ሸኘዋት፡፡

ክላስ ገብቼ ልክ እንደሌሎቹ ደብተር አውጥቼ እስክርቢቶ በእጄ ይዣለው፡፡ ነገር ግን በአእምሮዬ ከደቂቆች በፊት አይኔን ስለወጋኝ ውበት እያሰላሰልኩ ነው፡፡ "ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? ስሟ ማነው? እንዴት እስከዛሬ አላየዋትም? " በዛች ቅፅበት ፍቅርን አዝለው ወደ አእምሮዬ የመጡ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

እንዳያልቅ የለም ቀሪው የት/ት ክፍለ ግዜ አልቆ ምሳ ተደወለ፡፡ ምሳ አብሬው ምበላ፣ ወደቤት የሆነ መንገድ ድረስ አብሬው የምሄድ፣ አብዛኛውን ግዜዬን አብሬው ማሳልፈው #ወገን የሚባል ጓደኛ ነበረኝ፡፡

እናም ምሳ እየበላን "ስማ ቅድም አባሮሽ ስንጫወት እኔ እንዳባራት የተሰጠችኝን ልጅ ታቃታለህ እንዴ?" ብዬ ጠየኩት፡፡

"እእእእእ ፀገነትን ነው? አዎ" በማለት መለሰ፡፡

"ፀገነት ነው ስሟ! ማለት ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? የነማን ጓደኛ ናት? ምሳ የት ነው ምትበላው?" በማለት ስለሷ ለማወቅ እንደጓጓው በሚያሳብቅ መልኩ የጥያቄ ናዳ አወረድኩበት፡፡

እሱም "እንደኛው ሰባተኛ ነች፡፡ ሰፈሯ ከእኔ ሰፈር ብዙም አይርቅም፤ ቅርብ ለቅርብ ነን፡፡ እና ቆንጆ ነች፡፡" አለ እየሳቀና በእጁ መታ እያደረገኝ፡፡

ወዳው እንዴት እንደሆነ በማላውቀው መልኩ ውስጤ እሷን እሷን ሲለኝ ተሰማኝ፡፡ "ምሳ የት ነው ሚበሉት?" አልኩት፡፡

እሱም በልተን እንጨርስና እወስድሀለው ብሎ የሚበሉበት ቦታ ወሰደኝ፡፡ የመማሪያ ክላስ ሲሆን ግድግዳው በጠፍጣፋ ጣውላ ተደርድሮ የተሰራ ነው፡፡ በጣውላና ጣውላው መካከል ባላው ቀዳዳ አጮልቄ እንዳይ ጠቆመኝ፡፡ አዎ #ፀጊ ከሶስት ጓደኞቿ ጋር ምሳዋን እየበላች ነበር፡፡ በሰውነት ሁሉም ይበልጧታል፡፡ በመልክ ግን አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ትቦንሳቸዋለች፡፡ ስትስቅ ደሞ ላለመሳቅ ቀጠሮ የያዘ ሰውም ቢሆን ፈገግ ይላል፡፡ በቃ እንዴት እንደሆነ ባላቅም ገና በ14 አመቴ ፍቅር ይዞኛል፡፡ ግን ፍቅር ምንድን ነው? አላቅም!!!....... ፫
@Yewqetabugida67