Get Mystery Box with random crypto!

#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል1 በወቅቱ እንደማንኛውም ታዳጊ ጨዋታን አብዝቼ የምወድ የ7ኛ ክፍል ተማ | 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

#የፍቅር_አቦጊዳዬ
#ክፍል1

በወቅቱ እንደማንኛውም ታዳጊ ጨዋታን አብዝቼ የምወድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ በትምርቴ ከ1-10 ባለው ደረጃ እወጣ ነበር፡፡ በብዛት 4ኛ እና 5ኛ የኔ ደረጃዎች ነበሩ፡፡ ከዛ በዘለለ ግን ሙሉ ቀን ሙሉ ለሊት ስጫወት በውልና ባድር ጨዋታ የማልሰለች ልጅ ነበርኩ፡፡

ከቀኖች ሁሉ በቅጡ በማላስታውሰው በአንዱ ቀን ከተወሰነ የት/ት ክፍለ ግዜ በኀላ ለእረፍት ተለቀን ከተወሰኑ ተማሪዎች ጋር ተመራርጠን አባሮሽ እየተጫወትን ነው፡፡

በሰዓቱ እኔ አባርሬ እንድይዝ የተሰጠኝ አንዲት ቀይ ቀጠን ያለችን ልጅ ነበር፡፡ ልጅቷን ከዚህ በፊት ልብ ብዬ አይቻት አላቅም፤ ስሟንም ሰምቼው አላቅም፡፡ ጨዋታው ተጀመረና እኔ ነብር እሷ ሚዳቆ ሆነን በረጅሙ የት/ቤታችን የሳር ሜዳ ላይ ያዝኩሽ አመለጥኩህ ሩጫ ያዝን፡፡

ልይዛት በጣም እቀርብና በድንገት የእኔ ፍጥነት ቀንሶ የእሷ በመጨመር ታመልጠኛለች፡፡ ከብዙ ልብ አፍርስ ሩጫ በኀላ ከነብር እጅ ሚያመልጥ የለምና ሚዳቆዋን ያዝኳት፡፡ ነገር ግን እሷ ልታመልጠኝ እኔም ይዣት ለማስቀረት ስንሞክር እኔ በእሷ ላይ ወደቀን ተገኘን፡፡

ዩኒፎርሟ እንደመገላለጥ ብሎ ነበርና እንደማፈር ብላ ልብን በሚያቀልጥ ሁኔታ በእነዛ ሁለት አይኖቿ ለመጀመሪያ ግዜ አይኖቼን ተመልክታ እየተሽኮረመመች ከመሬት ተነስታ ሄደች፡፡ በዛች ቅፅበት ያቺ ቀጭን ቀይ ቆንጆ የመጀመሪያ ፍቅሬ ልትሆን ሳታስፈቅድ ወደ ልቤ ዘልቃ ገባች። ክፍል ሁለት ይቀጥላል