Get Mystery Box with random crypto!

ቸሩ የእኔ ጌታ መሃሪ ይቅር ባይ ከክፉው ወረርሽኝ ከኮሮና ቫይረስ ከባህሩ ስጥመት | 🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷


ቸሩ የእኔ ጌታ መሃሪ ይቅር ባይ
ከክፉው ወረርሽኝ ከኮሮና ቫይረስ
ከባህሩ ስጥመት ድልድይ ሆነህ
ከጥፋት ከልለህ ትላንት ካሻገርከኝ
በሰላም በጤና ዛሬ ላይ አኑረህ
ተመስገን ጌታዬ ነገም አንተ አለህ
የዘመናት ሠሪ የዓመታት አባት
ሁሉን አሳላፊ አልፋና ኦሜጋ
ያለፈውን ዘመን ደግሞ እንዳይመጣ
በምሕረትህና በቸርነት ይለፍ
እውነተኛ መሪ መንጋውን ሰብሳቢ
ከሃሳዊ መሲህ ተዋህዶን ጠባቂ
አሁንም አድለን እንባ አባሽ መሪ
ዘመነ ማቴዎስ ዘመነ ፍሥሃ ! ፡፡



@Yewqetabugida67