Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት በቤቴ🔝

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_bebete
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...
For comment @Tmhert_bebete_info_bot
Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-10-30 18:29:52 እንግሊዝኛ ከቻላችሁ እሄ ቻናል በፍጹም እንዳያመልጣችሁ, በጣም ለሂወታችሁ ጠቃሚ የሆነ ነው
3.7K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 07:01:47 አይምሯችን መሬት ነው፤ የተዘራበትን ማብቀል ነው ስራው። መልካም ነገር ከነገርነው፣ መልካም ነገር ካየ የህይወት መንገዳችን ያማረና ደስተኛ እንሆናለን።

ለሆዳችን እኮ በጣም ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በፍፁም የቆሸሸ ምግብ አንበላም። ታዲያ የነገ መድረሻችንን ለሚወስነው አይምሯችን ምንድነው የምንመግበው? መጥፎ ዜና ነው ወይስ መንፈሳዊ ሀሳብ? ስለ ሰው አሉባልታ ነው የምናስበው ወይስ ስለ ነገ መድረሻችን? ምርጫው የኛ ነው!

ምርጥ ቀን ይሁንላችሁ

inspire_ethiopia

@temhert_bebete
@temhert_bebete
7.8K views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 19:21:49
#competition

በምግብ ደህንነት ላይ ትኩረቱን ባደረገው ውድድር ኢትዮጵያዊቷ የእንሰትን ምርት በሚያሻሻል የፈጠራ ሃሳብ የ10ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆኑ።

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ውድድሩን በገንዘብ መደገፉንም ሌክስ ብሎግ የተሰኘው ድረገፀ አስነብቧል።

ውድድሩ የምግብ ደህንነትን የሚመለከት ሆኖ ከናይጄሪያ እና ከኢትዮጵያ ከ750 በላይ አመልካቾች ተሳትፈውበታል።

አስር ሃሳቦች ለኢትሴፍ ብሔራዊ የምግብ ውድድሩ ቀርበው የመጨረሻዎቹ ሶስቱ በዴንማርክ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ላብራቶሪ የመጨረሻው ፍተሻ ተደርጓል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
8.4K viewsedited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 07:38:26
ውጤት ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ይለቀቃል ሲሉ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
19.8K views04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 14:56:05 #MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?

- "የፈተና ዝግጅት እና ህትመት" ከቀድሞው እንዲለይ በኮድ ብዛት እና በገፅ አወቃቀር በመለየት በሁለቱም የትምህርት መስኮች " 12 ኮድ " እንዲኖር እና የመለያ ኮዱ ከሚታወቅበት 2 ኮድ ወደ 3 ተቀይሮ ፈተናው ተሰጥቷል።

- #ስልክ እና ማንኛውም #ኤሌክትሮኒክ_መሳሪዎችን ተፈታኞች ይዘው እንዳይመጡ መልዕክት ቢተላለፍም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 59 ተፈታኞች #ስልክ_ይዘው ገብተው ለመጠቀም ሙከራ አድርገው ተይዘዋል።
ጫት፣
አደንዛዥ ዕፅ፣
ሲጋራ፣
ስለታማ ነገሮች፣
ጥይት፣
አልኮል ..... ወዘተ ተፈታኞች ይዘው በመምጣት በተለያየ መልክ ለማስገባትና በአንዳንድ ቦታዎችም ለመጠቀም ሙከራ አድርገዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ " ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ግቢ " የሚወስደው ድልድይ በመደርመሱ ምክንያት 451 ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል ፤ 1 ተማሪ ህይወቱ ሲያልፍ 232 ተማሪዎች ቀላል የአካል ጉዳት ፣ 201 ተማሪዎች መካከለኛ ጉዳት ፣ 13 ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ፣ 5 ተማሪዎች በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ 5 የፀጥታ ኃይሎች እና 2 ፈተና አስፈፃሚዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- " በሶስት ዩኒቨርሲቲዎች " ቀደም ሲል በነበር የጤና እክል ምክንያት 3 ተማሪዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ በጉዞ ወቅት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ የተወሰኑ ተማሪዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ፈተና መውሰድ ያልቻሉና በከፊል የተፈተኑ በአንድ ወር ጊዜ የሚዘጋጀውን ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል። ተፈታኞቹ የጤና ሁኔታቸው ለፈተናው የማያበቃቸው ካሉ ከ2015 ዓ/ም ተፈታኞች ጋር በመደበኛነት እንዳፈተኑ ይደረጋል።

- " ፈተና አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ዳግም በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እንድል አይሰጣቸውም፤ በግል በ2015 ዓ.ም የመፈተን መብታቸው የተጠበቀ ነው።

በ " ማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ፈተና ሳይፈተኑ የወጡ ተማሪዎች ፦

ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ (1,700 ተማሪዎች)
ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (1,226 ተማሪዎች)
ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (2,711 ተማሪዎች)
ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (7,356 ተማሪዎች) በድምሩ 12,993 ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተና ሳይጀምሩና የአንድ ቀን ሁለት ፈተና ከወሰዱ እንዲሁም የሁለት ቀን 4 ፈተናዎች ከወሰዱ በኃላ " አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች ከዚህ በኃላ በ " መደበኛ ተማሪነት " መፈተን #የማይችሉ ሲሆን በ2015 በግል መፈተን ይችላሉ።

- በታወቁ የጤናና ሌሎችም እክሎች ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ።

- " የፈተናው ዉጤት " በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ ይፋ ይደረጋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
12.1K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 12:40:58
የፈተናው ውጤት ከወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይገለጻል---ትምህርት ሚንስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከወር ባነሰ ጊዜ እንደሚገለጽ አስታውቋል፡፡

በ2014 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና በአጠቃላይ ከ900 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው የተፈታኝ ቁጥር በእጅጉ እንደሚልቅ ተገልጿል። በአጠቃላይም ከተመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ 98.8 በመቶ ተማሪዎች ፈተናዉን ወስደዋል፡፡

ፈተናውን ለማስፈፀምም ከ25 ሺህ በላይ ፈተና አስፈፃሚዎች እና ከ 6 ሺህ በላይ የፀጥታ ሀይሎች ለፈተናው ተሰማርተዉ እንደነበር ተነግሯል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ያጋጠመው አደጋ እና ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተፈታኞች ያጋጠመዉ ትራፊክ አደጋ ፣ በመቅደላ አምባ፣ ደብረማርቆስ፣ ባህር ዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርስቲዎች ላይ 12 ሺ 993 ተማሪዎች አንፈተንም ብለው ፈተና ትተው መውጣታቸው በፈተና ወቅት ያጋጠሙ ክስተቶች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታዉሰዋል።

በፈተና ወቅትም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 53 ተፈታኞች ስልክ ይዘው ለመግባት የሞከሩ ሲሆን ፈተና አስፈፃሚዎችንም የማዋከብ እና ሌሎች የፈተና ስነ-ምግባር ግድፈቶች መታየታቸውን እና በፈታኞችም በኩል የፈተና ስርዓትን ያለመከተል ችግሮች እንደነበሩም ተገልጿል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
10.2K views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 17:33:53
" ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ይገለጻል።"

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)


የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ወይም 98 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ያልወሰዱና በተለያዩ አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ እንዲሁም በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

በአራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ12 ሺህ በላይ ፈተናውን አንፈተንም ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ #እንደማይችሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን #በግል መፈተን ይችላሉ ብለዋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሚገለጽ ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
13.6K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 11:04:06
የ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተናን #በግንቦት ወር ለመስጠትም ታቅዷል ፦ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስቴር በ " ኮቪድ-19 ወረርሽኝ " ምክንያት የተዛባውን የትምህርት ካላንደር በዘንድሮው ዓመት እንደሚያስተካክል ጠቁሟል።

" በ2015 ሁለት ፈተና ነው የምንሰጠው። አሁን የምንሰጠው ፈተና (ከመስከረም 30 ጀምሮ) የ2014ን ፈተና ነው።

ከኮቪድ ጊዜ ጀምሮ መርሀ ግብሩ እየተበላሽ በአጠቃላይ የትምህርት ስርዓታችን ግልፅ የሆነና ሁሉም የሚያውቀው የአካዳሚክ ካላንደር ሊኖረን አልቻለም ፤ እሱን በዚህ ዓመት እናስተካክላለን አሁን መስከረም 30 የምንሰጠው የ2014ን ነው ግንቦት ላይ የ2015 ተማሪዎችን እንፈትናለን።

ከዛ በኃላ ባሉት ጊዜያት የአካዳሚክ ካላንደሩ ከሞላ ጎደል ወደ ስርዓቱ ይገባል። "

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
11.3K viewsedited  08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 13:25:34
በፊሊፒንስ የሚገኝ ኮሌጅ ተማሪዎች ፈተና እንዳይኮራረጁ “ጭንቅላታችሁን ሸፍኑ” ማለቱ እያነጋገረ ነው

በፊሊፒንሷ ልጋዝፒ ከተማ የሚገኝ አንድ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኝ ኮሌጅ ተመሪዎች ወደጎናቸው አጮልቀዉ በመመልከት ፈተና እንዳይሰርቁ በማሰብ ጭንቅላታቸውን የሚሸፍን ነገር እንዲለብሱ ታዘዋል።

ይህንን ተከትሎም ተማሪዎች ካርቶኖችን፣ የእንቁላል መደርደሪያዎችን፣ የሞተር ሳይክል ሄልሜት እንዲሁም ከሌሎች የወዳደቁ ነገሮች በራሳቸው ፈጠራ የሰሯቸውን መሸፈኛዎች ለብሰው በፈተናው ላይ መገኘታውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ማንዳን፤ ተማሪዎች እንዳይኮራረጁ የተተገበረው አሰራር ውጤታማ እንደነበረ አስታውቀዋል።
በፈተና ወቅት ፊት መሸፈን እንዲተገበር ያነሳሳቸው ከዓመታት በፊት በታይላንድ ውስጥ ተተግብሮ ያዩት አንደሆነም ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ተናግረዋል።
በፈረንጆጁ 2013 ላይ የባንኮክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተና ላይ በሚቀመጡበት ወቅት በግራና በቀኝ በኩል ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ በወረቀት እንዲሸፍኑ በማድረግ ፈተና እንዲፈተኑ ተደርጎ ነበር።

ከዚህ በመነሳት “የፀረ ኩረጃ ኮፍያ” በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ መተግበሩንም ፕሮፌሰሯ አስታውቀዋል።
ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ፤ ጥብቅ የፈተና ቁጥጥር ተማሪዎች ለማጥናት አነሳስቷል ያሉ ሲሆን፤ ይህም የተሸለ አፈጻጸም ማስገኘቱንም ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት በርካቶች ፈተናቸውን በአግባቡ እና በተሰጣቸው ጊዜ ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ፕሮፌሰሯ፤ ፈተና ሲሰርቅ የተያዘ ተማሪ እንደሌለም አስታውቀዋል።

#አልዓይን

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
12.9K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 07:59:42 ውድድር ጀምር !

ህይወት ያለውድድር ወደፊት እንድትሄት አታደርግህም ! ውድድር ከሌለባት ወደኋላ ነው የምትሄደው ፤ ነገር ግን ዋናው ቁም ነገር የምትወዳደረው ከማን ጋር መሆኑን መለየት ነው! ከሰዎች ጋር ወይስ ከራስህ ጋር ? እኔ የምመክርህ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ውድድርህን ከራስህ ጋር አድርገው ከትላንት ማንነትህ ጋር ተወዳደር ፤ የሰዎችን እማ ያለፉበትን ነገር ምን ታውቃለህ ምን እንደገጠማቸው ምን እንደሚያስቡ ምን እንደሚፈልጉ በምን ታውቃለህ ከምናቸው ጋር ነው የምትወዳደረው ? በዚህች ምድር ላይ እኮ ጠንቅቀህ የምታውቀው አንተን ራስህን ብቻ ነው ስለዚህ ትላንትህን ታሪክህን እምነትህን ድልህን አስበው ዛሬ ላይ ደግሞ ምን እንዳለህ እየው ከዛም ከትላንቱ የበለጠ ለማሸነፍ ታጥቀህ ተነሳ ራስን እነደማሸነፍ ትልቅ ድል የለም !

የድል ቀን ተመኘን

inspire_ethiopia

@temhert_bebete
@temhert_bebete
13.2K viewsedited  04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ