2022-10-02 18:23:42
በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ሊሰጥ ነው። የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የዕውቅና ፍቃድ ጥያቄን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉ ተገለጸ፡፡
የት/ት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመነጋገር ኢ-ለርኒንግን ለማስፋፋት ፕሮጀክት ቀርጾ የ22 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱንና በአሜሪካው አሪዞና ዩኒቨርሲቲ አማካይነት መርሃ ግብሩን ዕውን ለማድረግ ሥራዎች መጀመራቸው ታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በርቀት የትምህርት መደብ የተወሰኑ ት/ቶችን ቢሰጡም በመደበኛነት የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ የሰጠው የትምህርት ተቋም የለም።
ትምህርት ሚኒስቴር በተያዘው ዓመት አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ት/ት ለመስጠት ፈቃድ እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱን የገለጸ ሲሆን ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ በደረጃ የኦንላይን ትምህርት እንዲሰጡ መታቀዱ ተገልጿል፡፡
የኦንላይን/E-Learning ት/ቱ ዋነኛ ትኩረቶች፦
• ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠቀሙበት የትምህርት አማራጭ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማቅረብ።
• ሁሉም መምህራን በኦንላይን የመማር ማስተማር የትምህርት ዘዴ ተጨማሪ ስልጠና ይወስዳሉ።
• የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኦንላይን ለመማር የሚችሉበት ሰልጠና ይሰጣቸዋል፡፡
የኦንላይን ትምህርትን ለማስፋፋት የት/ት ሥልጠና ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ባወጣው መመርያ ፈቃድ የወሰዱ ውስን የግል ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ዩኒቨርሲቲዎች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የኦንላይንን ትምህርትን ለማጠናከር የመሠረተ ልማቶችንና ፋሲሊቲዎችን የማሟላት ሥራዎች መጀመራቸው ተገልጿል።
https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
3.7K views15:23