Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት በቤቴ🔝

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_bebete
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...
For comment @Tmhert_bebete_info_bot
Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-11-22 08:52:02 ጨረቃ ላይ ውሃን ለማግኘት እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮጵያዊ የናሳ ተመራማሪ

ኢትዮጵያዊው የናሳ ተመራማሪ ኢንጂነር ብርሃኑ ቡልቻ (ዶ/ር) በጨረቃ ላይ ያለውን ውሃ የመለየት ችግር መፍትሄ ለመስጠት ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመስራት ላይ የሚገኙ ሳይንቲስት ናቸው፡፡

ተመራማሪው ከዚህ በፊት ጨረቃ ላይ ውሃ ለማግኘት የሚያስችል በመጠን አነስተኛ የሆነ ቁስ የኳንተም ፊዚክስ ቀመርን በመጠቀም መስራታቸው ይታወሳል።

"ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ስመጣ የባህል ልዩነቱ እና የሚደግፈኝ ባለመኖሩ ተቸግሬ ነበር" የሚሉት ኢንጂነር ብርሃኑ፤ "ሁሌም የማስበው ጠንክሮ መሥራት እና በትምህርት ስኬታማ መሆንን ነበር" ይላሉ፡፡

አሁን ላይ በጨረቃ ላይ ያለውን ውሃ የመለየት ችግር መፍትሄ ለመስጠት እና ሰዎች ጨረቃ ላይ መኖርን እንዲያልሙ የሚያስችል አስደናቂ ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ በሜሪላንድ የሚገኘው የናሳ የጠፈር በረራ ማዕከል ኢንጂነሩ፤ በዚሁ የምርምር ማዕቀፍ ውስጥ ያበለፀጉትን ፕሮቶታይፕ ለማጠናቀቅ የሚያስችላቸው 2.5 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ እንዳቀረበላቸው የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

በፕሮቶታይፑ ላይ የሚሰራውን የቴክኒካል ሥራ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት ሊፈጅ እንደሚችል ኢንጂነር ብርሃኑ ይገልጻሉ።

ውሃ ከምድር ወደ ጨረቃ ሊጓጓዝ ቢችልም ወጪው የማይቀመስና ሥራው ውጤታማ ባለመሆኑ የኢንጂነር ብርሃኑ ቡድን ምርምር ትልቅ ውጤት የሚያስገኝ ነው፡፡

ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች ጨረቃ ላይ አነስተኛ መጠን ውሃ መኖሩ ቢረጋገጥም የውሃ ውህዶችን በትክክል መለየት ግን ሳይቻል ቆይቷል።

በጨረቃ ላይ ያሉትን የውሃ አካላት ከውህዳቸው ለመለየት እና ብሎም በትክክል ቦታውን ለማመላከት የሚያግዘው የኢንጂነር ብርሃኑ የምርምር ሥራ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ #EBC

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
1.1K viewsedited  05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 09:19:41
"የተሰረቀና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰጥበት የትምህርት ስርዓት ይዘን መቀጠል አንችልም " ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
................................................

በ31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ላይ እየተደረገ ባለው ውይይት በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

አራተኛ ክፍል ደርሶ ማንበብ የማይችል ተማሪ እንዲሁም የተሰረቀና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰጥበት የትምህርት ስርዓት ይዘን መቀጠል አንችልም ያሉት ሚኒስትሩ ለአንዴና ለመጨረሻ የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

ችግሮቹን ደረጃ በደረጃ ለይቶ በመፍታት ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ማፍራት እንደሚገባም አብራርተዋል ።

እንደ ትምህርት ማህበረሰብ በቀጣይ አራት ዓመት መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት መሥራት ይኖርብናል በማለት ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የትምህርት ዘርፍ አመራር፣ ባለድርሻ አካላት እና የህዝቡን ትብብር እንፈልጋለን ብለዋል።

በተለይም ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ በማጥራት መሥራት የምንፈልገውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እንተገብራለን ያሉ ሲሆን በዚህም ወደ ኋላ የምንልበት ሁኔታ የለም በማለት ተናግረዋል ።

በትምህርት ሴክተሩ መሥራት ያለብንን ለዛሬ ሳይሆን ለነገው አስበን እንስራ ይህንንም ማድረግ እንችላለን በማለት ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በዚህ የትምህርት ጉባኤ የትምህርት ስርዓቱን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
3.1K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 12:18:18 ለአብዛኞቹ English ቋንቋ አቀላጥፈው እንዲናገሩ ምክንያት የሆናቸው ቻናል ልጋብዛችሁ
እንግሊዝኛ መደመጥ እንጅ መነገር ከባድ የሆነባችሁ ሁሉ ይህን ቻናል ተቀላቀሉት
ትወዱታላችሁ


Join

https://t.me/+SqArvXoN63khCOGw
https://t.me/+SqArvXoN63khCOGw

1.8K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 07:24:42 ራስህን እወቅ!

መሆን ምትፈልገውን ሰው መሆን ከፈለክ ይህንን ጥያቄ ራስህን ጠይቅ
ዕለት ዕለት የማደርገው ነገር መሆን የምፈልገውን ሰው እንድሆን የሚረዳኝ ነው ወይስ አይደለም?
እኔ መሆን ምትፈልገው ሰው ዕለት ዕለት የማደርገውን ነገር ያደርጋል ወይስ አያደርግም?
መሆን ምትፈልገውን ሰው ለመሆን ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ምን እያደረኩ ነው?
እነዚህን ጥያቄዎች በመጠየቅ ራስህን ፈትሽ/ፈትሺ!!

ያሰባቹትን የምታሳኩበት ቀን ይሁንላችሁ

@temhert_bebete
@temhert_bebete
5.7K viewsedited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 15:33:01
31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ህዳር 8 /2015ዓም ይጀመራል።

ህዳር 8/2015 ዓም . የከፍተኛ እና አጠቃላይ ዘርፎች እቅድ ፣ አፈጻጸምና የየዘርፎቹን ዝርዝር ተግባራት ከየዘርፎቹ ተጠሪ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር በተመሣሣይ ጊዜ የሚከናወን ልዩ መርሃ ግብር የሚካሄድ መሆኑንና ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤው ህዳር ዘጠኝ ሁለቱም ዘርፎች እና ባለድርሻ አካላት በጋራ በተገኙበት የሚካሄድ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ተመላክቷል።

በጉባኤው የአጠቃላይ ትምህርት እና የከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የለውጥ ስራዎችና ሌሎችም ተዛማጅ የትምህርት ጉዳዮችም ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

የክልል ትምህርት ቢሮዎች አፈጻጸም ሪፖርት እና የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እቅድ ፣ የምርምር ተቋማትና ሌሎችም ዓመታዊ ክንውኖችም እንዲሁም የትምህርት ዘርፍን የወደፊት አቅጣጫ አመላካች ጥናታዊ ጽሁፎች እና የትምህርት አጋር ድርጅቶች ሞሽን በጉባዔው እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

በአገራዊ የትምህርት ዘርፍ አፈጻጸሞችና የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ የሚመክረው ጉባዔ መፍትሄዎችን በማመላከትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ቅዳሜ ይጠናቀቃል ።

በጉባዔው ላይ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ዘርፍ ኃላፊዎችና የትምህርት ስራ ባለድርሻዎችን ጨምሮ 400 በላይ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
3.7K views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 21:51:31 "የሚቀጥሉት አራት ዓመታት የመንግስት የትምህርት ዘርፍ ትኩረት ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ አስተማማኝ መሰረት መጣል ይሆናል።"

ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከስምንት እስከ አስር ሺህ የሚጠጉ የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል።

"በርከት ያሉ የመጀመሪያ ደረጃ እና በርከት ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገንብተናል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቀዳማዊት ዕመቤት ጽ/ቤት ብቻ 28 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብቷል ብለዋል።

"የነገሮች ሁሉ መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ነው" ሲሉ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ዩኒቨርሲቲዎችን ከመክፈት ይልቅ ለታችኛው የትምህርት ደረጃ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የተማሪዎች ምገባን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ 9.5 ሚሊዮን ህጻናትን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ መቻሉን አመልክተዋል።

"ይህም አሀዝ የአንዳንድ አገራት ህዝብ ቁጥር እንደማለት ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

"የምገባ ፕሮግራሙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው" ብለዋል።

"ታዳጊ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው በዳቦ ምክንያት ተስተጓጉለው እንዳይቀሩ እንደሀገር አበክረን ልንሰራ ይገባል" ብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
7.7K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 19:00:53
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት እስከ ሦሥት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ገለጹ።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሦሥት ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ ሆኖ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲ ምድብ ይወጣል ብለዋል።

"አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተከትሎ ባህር ዳር፣ ሀራማያ፣ ጅማ፣ መቐለ፣ ሀዋሳ ... የመሳሰሉት ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች በፍጥነት ከመንግስት በጀት ወጥተው ራስ ገዝ (Autonomous) መሆን አለባቸው" ብለዋል።

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ መንግስት አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
7.8K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 10:36:42
የዓለም ህዝብ ቁጥር ዛሬ 8 ቢሊዮን ይደፍናል።

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትንበያ ከሆነ የዓለም ህዝብ ቁጥር ዛሬ ኖቬምበር 15 ቀን 2022 ዓ.ም ስምንት ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። እንደ ትንበያው ከሆነ ሕንድ በፈረንጆቹ 2023 ከቻይና የበለጠ የሕዝብ ቁጥር ልታስመዘግብ እንደምትችል ይጠበቃል።

via - visual capitalist

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
7.9K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 15:43:44
#Online_Opportunity

በተባበሩት መንግስታት የኦንላይን በጎ ፍቃድ ፕሮግራም (UNOVP) ይሳተፉ

➭ ሙሉ ወጪ የሚሸፈንበት
➭ ምንም የማመልከቻ ክፍያ የማይጠይቅ
➭ በኦንላይን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥበት
➭ በጎ ፍቃደኞች በፈለጉት መስክ የመምረጥ ዕድል ያገኛሉ

ፕሮግራሙ በጎ ፍቃደኞች ከዓለም አቀፍ ታዋቂ ተቋማት ጋር የመስራት፣ ሥራዎቻቸውን ለማሳየት እና ትስስር ለመፍጠር ዕድል ያስገኛል።

ምዝገባው በመካሄድ ላይ የሚገኝ

ለማመልከት ➭ https://tinyurl.com/38m4y28x

Via- tikvah university

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
8.3K views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 13:50:07 #sat #analogy

501 Word Analogy Questions
File size: 216.7 kB
File type: PDF

SAT ላይ ለሚመጡ Analogy ጥያቄዎች በጣም አሪፍ መፅሃፍ ነው። Amazon ላይ 4.5 star አለው። አውርዳችሁ ተጠቀሙበት።

Endre-Acadamy

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
291 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ