Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ ministery_of_education — የትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ ministery_of_education — የትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @ministery_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.05K
የሰርጥ መግለጫ

ትምህርት ሚኒስትር @MINISTERY_OF_EDUCATION

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2019-07-24 19:14:28 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዕረፍት ጊዜያቸው ችግኝ በመትከልና
በመንከባከብ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ሚኒስቴር ዴኤታው
ጥሪያቸውን ያቀረቡት ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ
ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር ሐምሌ 14 ቀን 2011 ዓ.ም
በከተማው ችግኝ በተከሉበት ጊዜ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር
@MINISTERY_OF_EDUCATION
335.3K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-07-24 08:23:57 ለብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች

ከትላንት ጀምሮ በመላዉ ሀገሪቱ የ10ኛ እና 12ኛ ክፊል ብሐራዊ ፈተና ዉጤት በሐምሌ 30 ይለቀቃል ተብሎ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ፍፁም ከእዉነት የራቀ መሆኑን አዉቃችሁ ተማሪዎች በመንግስት ሚዲያዎች እና በቻናላችን በኩል እስከምናስተላልፍ በትዕግስት እንድትጠብቁን በጥብቅ እናሳስባለን።

የትምህርት ሚኒስቴር
@MINISTERY_OF_EDUCATION
300.2K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-06-21 19:34:41 የከፍተኛ ትምህርትን ሳይማሩ የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ባለቤት የሚሆኑትን ለመከላከል የሚያስችለውን ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡

ሰኔ 14፣2011(ሸገር 102.1)
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማስቆም ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ የተነገረለት አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር ከፊታችን ሐምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ኤጀንሲው እንደሚናገረው ከሆነ ዘመናዊው አሰራር በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚፈፀሙ ያልተገቡ አሰራሮችንም ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡

በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ተባባሪነት የተዘጋጀው የአሰራር ሥርዓት የተማሪዎችን ሙሉ መረጃ በመያዝ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ይከላከላል ተብሏል፡፡

ከአሁን ቀደም የትምህርት ተቋማት የእውቅና ፈቃድ ለማውጣት ወይንም ለማሳደስ በቋሚነት ያልቀጠሯቸውን መምህራንን የቀጠሩ በማስመሰል መረጃ ያቀርቡ ነበር ተብሏል፡፡

ይህ ደግሞ ግለሰቦች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ለተለያዩ ተቋማት እያከራዩ በትምህርት ጥራቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር መቆየቱ ተነግሯል፡፡

ከአሁን ወዲህ ግን እንዲህ ዓይነት የተዘረከረኩ አሰራሮች እንደማይኖሩ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ሰምተናል፡፡

ባለፉት አመታት በመስሪያ ቤቱ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሕገ-ወጥ ተቋማትን የተመለከቱ ቅሬታዎች ከዜጎች ሲቀርቡ ነበር ተብሏል፡፡

የኤጀንሲው የስራ ሀላፊዎችም ከቀረቡት ቅሬታዎች በመነሳት ባካሄዱት ፍተሻ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሰራር ውስጥ በርካታ እና ውስብስብ ህገ ወጥነቶችን መለየታቸው ነው የተነገረው፡፡

ኤጀንሲው በሐምሌ ወር እጀምረዋለሁ ያለው የዘመናዊ አሰራር እነዚህን ችግሮች ይከላከልልኛል የሚል እምነቱን አሳድሮበታል፡፡
@MINISTERY_OF_EDUCATION
252.3K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-03-12 22:37:41 በዩኒቨርሲቲዎች የተንሰራፋዉን ሙስናና ብልሹ አሠራር መከላከል አንደሚገባ ጥሪ ቀረበ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ዩኒቨርሲቲዎች የአገርና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም በጥሩ ተምሳሌትነት የአገራችንን ዕድገት እውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል አሉ፡፡

ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጋራ በአዲስ አበበ ለአንድ ቀን በዘጋጀው ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በጥሩ ስነምግባር የታነፁ ብቁና በቂ ዜጎችን ለማፍራት ችግሩን በሳይንሳዊ ጥናት በማቅረብ በጋራ በመወያየት ዘለቄታ መፍትሄ እንደሚስፈልግ አሳስበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርሲቲ አከባቢ የሚታዩትን ብልሹ አሠራርና ሙስናን የመከላከል ሃላፊነት እንዳለባቸው ጥሪ መቅረቡን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌስ ቡክ ደረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በ10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ባተደረገ ጥናት በዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ጉዳዮች -በተማሪዎች እና መምህራን፣ በፕሮጀክት ግንባታዎች፣ በበጀትና ግዥ ሥርዓት ፣ በሠራተኛ ቅጥርና ሹመት ብልሹ አሠራሮች መኖራቸው በጥናት መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር @MINISTERY_OF_EDUCATION    
190.4K views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-03-12 22:15:18 በዩኒቨርሲቲዎች የተንሰራፋዉን ሙስናና ብልሹ አሠራር መከላከል አንደሚገባ ጥሪ ቀረበ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ዩኒቨርሲቲዎች የአገርና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም በጥሩ ተምሳሌትነት የአገራችንን ዕድገት እውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል አሉ፡፡

ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጋራ በአዲስ አበበ ለአንድ ቀን በዘጋጀው ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በጥሩ ስነምግባር የታነፁ ብቁና በቂ ዜጎችን ለማፍራት ችግሩን በሳይንሳዊ ጥናት በማቅረብ በጋራ በመወያየት ዘለቄታ መፍትሄ እንደሚስፈልግ አሳስበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርሲቲ አከባቢ የሚታዩትን ብልሹ አሠራርና ሙስናን የመከላከል ሃላፊነት እንዳለባቸው ጥሪ መቅረቡን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌስ ቡክ ደረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በ10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ባተደረገ ጥናት በዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ጉዳዮች -በተማሪዎች እና መምህራን፣ በፕሮጀክት ግንባታዎች፣ በበጀትና ግዥ ሥርዓት ፣ በሠራተኛ ቅጥርና ሹመት ብልሹ አሠራሮች መኖራቸው በጥናት መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር @MINISTERY_OF_EDUCATION    
169.5K views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-01-17 18:27:32
143.6K viewsHENOK, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-01-16 21:23:25 የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና መስጫ ቀን ይፋ ሆነ::

የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ የፈተና መስጫ ቀናቱ ለሁሉም ክልሎች መላኩን ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም ክልሎቹ የተለየ ምክንያት ካላቸው ሌላ የፈተና መስጫ ቀን በመምረጥ ለኤጀንሲው ማሳወቅ እንደሚችሉም ለኢዜአ ተናግረዋል።
ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥባቸው ቀናት ፤

የ10ኛ ክፍል ከግንቦት 21 እስከ 23 ቀን 2011 ዓ.ም

የ12ኛ ክፍል ከግንቦት 26 እስከ 30 ቀን 2011 ዓ.ም

የ8ኛ ክፍል ከሰኔ 5 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚሰጥ ኤጀንሲው ገልጿል።
 
ትምህርት ሚኒስቴር
@MINISTERY_OF_EDUCATION
137.3K viewsHENOK, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-01-11 14:38:59 የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር

ሃገር በቀል እውቀቶች በምርምር አልፈውና በቴክኖሎጂ ተደግፈው ወደ ህብረተሰቡ ለማውረድ የሚያስችል መመርያ ማፅደቁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመማር መስተማር ስራዎቻቸው በተጨማሪ የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ እና ከዛም አልፎ ሀገሪቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግኝቶችን በምርምር ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

በሀገሪቱ የሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎችም በተወሰነ ደረጃ ይህን አብይ ጉዳይ ለማሟላት ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ዪኒቨርስቲዎች ሀገር በቀል እውቀቶችን መነሻ አድርጎ መስራት ላይ በርካታ ውስንነቶች የሚስተዋሉባቸው መሆኑ ነው የተገለፀው።

ትምህርት ሚኒስቴር
  @MINISTERY_OF_EDUCATION
121.9K viewsHENOK, 11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-01-01 18:59:00 በምእራብ ኦሮሚያ

በምእራብ ኦሮሚያ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተዘግተው የቆዩ 955 ትምህርት ቤቶች በህብረተሰቡ ርብርብ መከፈታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ለዘጠኝ ቀናት ተዘግተው የቆዩት ትምህርት ቤቶቹ በየአካባቢው የሚገኙ ማህበረሰብ ርብርብ ነው በትናንትናው እለት ተከፍተው ስራ የጀመሩት።
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በከልሉ በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ በስድስት ዞኖች 1 ሺህ 765 ትምህርት ቤቶች እስከ 2 ሳምንት ተዘግተው ቆይቷል።

የፀጥታ ችግሩ በተከሰተባቸው ምእራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ቦረና ዞኖች ናቸው።

የምእራብ ወለጋ የህብረተሰብ ክፍል ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጋ ካደረጉት አካላት ጋር በመነጋገር ተዘግተው የቆዩት 955 ትምህርት ቤቶች ስራ እንዲጀምሩ አድርገዋል ነው ያሉት ዶክተር ቶላ።

በሌላ በኩል እስካሁን ትምህርት ቤቶቹ የተዘጋባቸው የአምስቱ ዞኖች የማሀበረሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ሁሉም አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር
@MINISTERY_OF_EDUCATION
109.6K viewsHENOK, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2018-12-31 18:54:01 የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

የግልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያነሷቸውን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር አድርጓል።
በመድረኩ ላይ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚታዩ ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋን ከማፍራት አንጻር፣ ተማሪዎችን ሳያስመርቁ መጥፋት፣ ብቁ መምህራንን አለመቅጠር እና መረጃን ከመስጠት አንጻር ክፍተት እንደሚስተዋልባቸው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በበኩላቸው በመንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍና ክትትል አናሳ መሆኑን አንስተዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም አሁን ላይ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የሚታዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ለዚህም በተቋማቱ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችንና የህግ ጥሰቶችን መቆጣጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም በሁለቱ አካላት መካከል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል የሚያግዝ የመማክርት ጉባኤ መቋቋሙን ገልጸዋል።
ጉባኤው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ሚኒስቴሩ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በመንግስት በኩል ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት።

 ትምህርት ሚኒስቴር
@MINISTERY_OF_EDUCATION
99.8K viewsHENOK, 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ