Get Mystery Box with random crypto!

በዩኒቨርሲቲዎች የተንሰራፋዉን ሙስናና ብልሹ አሠራር መከላከል አንደሚገባ ጥሪ ቀረበ የሳይንስና | የትምህርት ሚኒስቴር

በዩኒቨርሲቲዎች የተንሰራፋዉን ሙስናና ብልሹ አሠራር መከላከል አንደሚገባ ጥሪ ቀረበ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ዩኒቨርሲቲዎች የአገርና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም በጥሩ ተምሳሌትነት የአገራችንን ዕድገት እውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል አሉ፡፡

ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጋራ በአዲስ አበበ ለአንድ ቀን በዘጋጀው ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በጥሩ ስነምግባር የታነፁ ብቁና በቂ ዜጎችን ለማፍራት ችግሩን በሳይንሳዊ ጥናት በማቅረብ በጋራ በመወያየት ዘለቄታ መፍትሄ እንደሚስፈልግ አሳስበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርሲቲ አከባቢ የሚታዩትን ብልሹ አሠራርና ሙስናን የመከላከል ሃላፊነት እንዳለባቸው ጥሪ መቅረቡን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌስ ቡክ ደረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በ10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ባተደረገ ጥናት በዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ጉዳዮች -በተማሪዎች እና መምህራን፣ በፕሮጀክት ግንባታዎች፣ በበጀትና ግዥ ሥርዓት ፣ በሠራተኛ ቅጥርና ሹመት ብልሹ አሠራሮች መኖራቸው በጥናት መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር @MINISTERY_OF_EDUCATION