Get Mystery Box with random crypto!

በምእራብ ኦሮሚያ በምእራብ ኦሮሚያ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተዘግተው የቆዩ 955 ትምህርት ቤ | የትምህርት ሚኒስቴር

በምእራብ ኦሮሚያ

በምእራብ ኦሮሚያ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተዘግተው የቆዩ 955 ትምህርት ቤቶች በህብረተሰቡ ርብርብ መከፈታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ለዘጠኝ ቀናት ተዘግተው የቆዩት ትምህርት ቤቶቹ በየአካባቢው የሚገኙ ማህበረሰብ ርብርብ ነው በትናንትናው እለት ተከፍተው ስራ የጀመሩት።
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በከልሉ በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ በስድስት ዞኖች 1 ሺህ 765 ትምህርት ቤቶች እስከ 2 ሳምንት ተዘግተው ቆይቷል።

የፀጥታ ችግሩ በተከሰተባቸው ምእራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ቦረና ዞኖች ናቸው።

የምእራብ ወለጋ የህብረተሰብ ክፍል ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጋ ካደረጉት አካላት ጋር በመነጋገር ተዘግተው የቆዩት 955 ትምህርት ቤቶች ስራ እንዲጀምሩ አድርገዋል ነው ያሉት ዶክተር ቶላ።

በሌላ በኩል እስካሁን ትምህርት ቤቶቹ የተዘጋባቸው የአምስቱ ዞኖች የማሀበረሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ሁሉም አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር
@MINISTERY_OF_EDUCATION