Get Mystery Box with random crypto!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የግልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያነሷቸውን ችግሮች | የትምህርት ሚኒስቴር

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

የግልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያነሷቸውን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር አድርጓል።
በመድረኩ ላይ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚታዩ ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋን ከማፍራት አንጻር፣ ተማሪዎችን ሳያስመርቁ መጥፋት፣ ብቁ መምህራንን አለመቅጠር እና መረጃን ከመስጠት አንጻር ክፍተት እንደሚስተዋልባቸው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በበኩላቸው በመንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍና ክትትል አናሳ መሆኑን አንስተዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም አሁን ላይ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የሚታዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ለዚህም በተቋማቱ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችንና የህግ ጥሰቶችን መቆጣጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም በሁለቱ አካላት መካከል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል የሚያግዝ የመማክርት ጉባኤ መቋቋሙን ገልጸዋል።
ጉባኤው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ሚኒስቴሩ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በመንግስት በኩል ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት።

 ትምህርት ሚኒስቴር
@MINISTERY_OF_EDUCATION