Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት በቤቴ🔝

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_bebete
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...
For comment @Tmhert_bebete_info_bot
Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2022-05-10 16:46:46
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደቡ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 04 እና 05/2014 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ የሚያደርጉባቸው እና ትምህርታቸውን የሚከታተሉባቸውን ካምፓሶች ዩኒቨሲቲው አሳውቋል።

Freshman Social Science, Freshman Teachers Education in Social Science እና
Freshman Teachers Education in Natural Science የተመደባችሁ በዋናው ግቢ።

Freshman in Natural Science የተመደባችሁ በጅማ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት እና በጅማ ግብርና እና ሕክምና ኮሌጅ ካምፓሶች።

https://portal.ju.edu.et ላይ በመግባትና የአድሚሽን ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ እንደምትችሉ ተገልጿል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
8.4K viewsedited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 19:21:26
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።

የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች #ዳግም_ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪዎች ሪፖርት የሚያደርጉባቸው ካምፓሶች፦

Natural Science & Teacher Education in Natural Science የተመደባችሁ ~ በዋናው ግቢ፣

Social Sciences & Teacher Education in Social Science የተመደባችሁ ~ በቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት መሆኑን ዩኒቨርስቲው አሳውቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
9.6K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 15:48:15
" ተማሪዎቹ በድጋሚ እንዲፈተኑ ተወስኗል "

በኮንሶ ዞን በፀጥታ ችግር የ2013 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ መወሰኑን የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።

መምሪያው ይህን ያሳወቀው የክልሉን ትምህርት ቢሮ ዋቢ በማድረግ ነው።

ተማሪዎቹ ድጋሜ እንዲፈተኑ ውሳኔ የተላለፈው ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በቀረበ ቅሬታ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀርቧል።

በኮንሶ ዞን አከባቢ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎች በሙሉ ቀልባቸው አልተማሩም።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኑ 824 ተማሪዎች መካከል 51 ተማሪዎች ብቻ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ሲሆን፤ 773ቱ ወደ ዩኒቨርሲቲ ማለፍ አልቻሉም።

እኚሁ 773 ተማሪዎች ናቸው በድጋሜ የ12ኛ ክፍል ፈተና እንዲወስዱ ዕድል የተመቻቸላቸው።

ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ ክልሎች በፀጥታ ችግር ውስጥ ሆነው ፈተና ተፈትነው ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ከ2014 ተፈታኞች ጋር በድጋሜ እንዲፈቱን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20/2015 ዓ.ም በኃላ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃውን ከኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ነው ያገኘነው።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
9.9K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 14:06:47
ኢትዮጵያ ከባለ 5ጂ ኢንተርኔት ባለቤቶች ጎራ ልትቀላቀል ነው


ኢትዮቴሌኮም 5ጂ ለመቀበል ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ከዛሬ ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ጀምሮ ኢትዮጵያ ከባለ 5ጂ ኢንተርኔት ባለቤቶች ጎራ ትቀላቀላለች።

ኩባንያው ፕሮጀክቱን ከቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ (Huawei) በተገኘ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ተግባራዊ እያደረገ ነው። አሁን ላይ ተግባራዊ የሚደረገው በአዲስ አበባ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና መ/ቤት እና ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ነው ተብሏል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት ለንግድ አገልግሎት የዋለው እ.ኤ.አ. በ2018 በቬሪዞን ነበር። በአፍሪካ ደግሞ የ5ጂ ኔትወርኮች በኬንያ እና በደቡብ አፍሪካ ይገኛሉ።


capital

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
9.9K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 20:36:33
#Update
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ግንቦት 09 እና 10/2014 ዓ.ም መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።

የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች #ዳግም_ቅበላ ግንቦት 11 እና 12/2014 ዓ.ም መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተመደቡባቸውን ካምፓሶች ያሳወቀ ሲሆን በተገለጹት ቀናት በየካምፓሶቹ ሪፖርት አድርጉ ብሏል። (ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል።)

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
10.8K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 13:53:24
" የመማር ሞራላችን ላይ ነው የተጫወቱት "

ፈተና ተፈትነው ወደ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ ተማሪዎች ውጭ እራሱ ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርሲቲው የመደባቸው ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው እንደማይቀበላቸው እንደገለፀላቸው እና ከሩቅ ቦታ የመጡ ተማሪዎች ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸው መፍትሄም እንደሚፈልጉ መግለፃቸው ይታወሳል።

እነዚህ ተማሪዎች አሁን ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደቡ በትምህርት ሚኒስቴር አድራሻ መመልከታቸውን ገልፀው አሁን የተመደቡባቸው ተቋማት ራቅ ያሉ መሆናቸውን አስረድተዋል።

መልዕክታቸውን በስልክ የላኩ የቲክቫህ አባላት መንግስት በራሱ ችግር ክፉኛ አጉላልቶናል ለዚህም በይፋ ይቅርታ እንኳን የጠየቀን የለም " የመማር ሞራላችን ላይ ነው የተጫወቱብን " ብለዋል።

ወደ አዳማ ተመድበው ግቢው እንደማይቀበል የተለፀው በርካታ ተማሪዎች ሲሆኑ አሁን እንደ አዲስ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ተንቀሳቅሰው እንደሆነ የጠየቅናቸው የቤተሰባችን አባላት አለመሄዳቸውን አስረድተዋል።

በተደረገው ድርጊቱ ሁሉ ማዘናቸውንም ገልፀዋል።

መስለል ድርጊቶች በሌሎች ተማሪዎች ላይ እንዳይፈፀም ቀደም ብሎ ማስተካከል ይገባል፤ የማይቻል ከሆነ ቀድሞውኑ አለመመደብ ፤ ተማሪ ሀገር አቋርጦ ከመጣ በኃላ አንቀበልም ማለት ማንገላታት ፍፁም ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።

tikvahethiopia

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
11.4K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 09:03:47
ዝውውር በላኪና ተቀባይ ዩንቨርሲቲዎች የጋራ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ትምህርት ሚኒስቴር ወሰነ።

ትምህርት ሚኒስቴር ዝውውርን በተመለከተ ያለፉትን ጥቂት አመታት ሲጠቀምበት የነበረውን ማለትም ዝውውር የሚጠይቁ ተማሪዎች ከመንግስት ሆስፒታሎች በህክምና ቦርዶ የተረጋገጠ ማስረጃ ይዘው ለመስሪያ ቤቱ በማቅረብ ዝውውር ይፈፅም የነበረውን ስርዓት የተማሪዎችን ጊዜ እና ገንዘብ ወጪ እያስደረገ መሆኑን በማየት ዝውውርን በተቀባይና በላኪ ዩንቨርሲቲዎች የጋራ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ውሳኔ አስተላልፏል።

#ማሳሰቢያ

፨ዝውውር የሚጠይቁ ተማሪዎች ከመንግስት የህክምና ተቋማት የህክምና ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
13.0K viewsedited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 07:55:41 AASTU አዲስ ገቢ ተማሪዎች የዶርም ምደባ፣ የመታወቂያ ቁጥር እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አድርጉ፤

http://www.aastu.edu.et/freshmaninfo/
ይህንን ሊንክ በChrome ወይም በምትፈልጉት Browser ክፈቱት።

Admission No. ፃፉና Get info የሚለውን ንኩት።

የሚያስፈልጋችሁ መረጃ ይመጣላችኋል። ከዚያ ለሌላ ጊዜ እንድትጠቀሙበት Screenshot አድርጉት።

ከላይ የዩኒቨርስቲውን ካርታ Attach ተደርግጓዋል ። መንገድ መጠየቅ አያስፈልግም ማለት ነው።

የዩኒቨርስቲው Official የቴሌግራም ቻናል @pir2011 ነው፤ በዚያ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
10.1K viewsedited  04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ