Get Mystery Box with random crypto!

' የመማር ሞራላችን ላይ ነው የተጫወቱት ' ፈተና ተፈትነው ወደ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒ | ትምህርት በቤቴ🔝

" የመማር ሞራላችን ላይ ነው የተጫወቱት "

ፈተና ተፈትነው ወደ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ ተማሪዎች ውጭ እራሱ ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርሲቲው የመደባቸው ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው እንደማይቀበላቸው እንደገለፀላቸው እና ከሩቅ ቦታ የመጡ ተማሪዎች ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸው መፍትሄም እንደሚፈልጉ መግለፃቸው ይታወሳል።

እነዚህ ተማሪዎች አሁን ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደቡ በትምህርት ሚኒስቴር አድራሻ መመልከታቸውን ገልፀው አሁን የተመደቡባቸው ተቋማት ራቅ ያሉ መሆናቸውን አስረድተዋል።

መልዕክታቸውን በስልክ የላኩ የቲክቫህ አባላት መንግስት በራሱ ችግር ክፉኛ አጉላልቶናል ለዚህም በይፋ ይቅርታ እንኳን የጠየቀን የለም " የመማር ሞራላችን ላይ ነው የተጫወቱብን " ብለዋል።

ወደ አዳማ ተመድበው ግቢው እንደማይቀበል የተለፀው በርካታ ተማሪዎች ሲሆኑ አሁን እንደ አዲስ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ተንቀሳቅሰው እንደሆነ የጠየቅናቸው የቤተሰባችን አባላት አለመሄዳቸውን አስረድተዋል።

በተደረገው ድርጊቱ ሁሉ ማዘናቸውንም ገልፀዋል።

መስለል ድርጊቶች በሌሎች ተማሪዎች ላይ እንዳይፈፀም ቀደም ብሎ ማስተካከል ይገባል፤ የማይቻል ከሆነ ቀድሞውኑ አለመመደብ ፤ ተማሪ ሀገር አቋርጦ ከመጣ በኃላ አንቀበልም ማለት ማንገላታት ፍፁም ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።

tikvahethiopia

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete