2022-06-03 17:54:27
ክቡር ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት ዝግጅት ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየውን ነጻ የክህሎት ስልጠና ነገ ያጠናቅቃል።
ከአዲስ አበባ እና ከሰበታ ከተማ ከሚገኙ ከ75 በላይ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ500 በላይ ተማሪዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል።
College and Career Readiness Bootcamp የተባለው ስልጠናው፤ ተማሪዎቹ ለቀጣይ ሙያቸውና ህይወታቸው የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት ያገኙበት መሆኑን የክቡር ኮሌጅ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ መኩሪያ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል።
ከግንቦት 04/2014 ዓ.ም ጀምሮ በተሰጠው ስልጠና፤ ተማሪዎቹ በ12 የስልጠና አይነቶች የህይወት እና የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ መደረጉን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
የስልጠናው ማጠቃለያ ዝግጅት ነገ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ብስራተ ገብርኤል በሚገኘው አዶት ሲኒማ ይካሄዳል ተብሏል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የፈጠራ ባለሙያዎች እና ሌሎችም በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ እንደሚገኙ ይጠበቃል።
በመድረኩ ምሁራን ልምዳቸውን የሚያካፍሉ ሲሆን ለሰልጣኞች የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ይሰጣል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
4.0K views14:54