Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት በቤቴ🔝

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_bebete
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...
For comment @Tmhert_bebete_info_bot
Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-09-29 12:48:04
ለ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
16.7K views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 09:41:38 ሰበብ መደርደሩን አቁም!

አሁን ለገጠመህ ችግር ሰዎችን መውቅስ አቁም! በሁኔታዎች ማማረር አቁም! በኑሮህ፣ በገቢህ፣ በትዳርህ ወይ በፍቅር ግንኙነትህ ደስተኛ ካልሆንክ በራስህ ምክንያት ነው፤ እኔ ራሴ ከፈጣሪ ጋር ሁሉንም አስተካክለዋለው በል!

አንተ ለራስህ ካልሆንክ ሌላ ማን እንዲሆንልህ ትፈልጋለህ? ይህቺ አለም ወደ ውስጡ ለሚያይና ራሱን ለሚቀይር ታሽቃብጣለች፤ በሰዎችና በሁኔታዎች ለሚያሳብብ ደግሞ ፊቷን ታዞራለች። ችግሩም መፍትሄውም እኔ ነኝ በል ወዳጄ!

inspire_ethiopia

@temhert_bebete
@temhert_bebete
8.4K viewsedited  06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 21:54:51
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብሄራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እና የማዕከላዊ ጎንደር ትምህርት መምሪያ ሃላፊዎች በጋራ መስከረም 18/2014 ዓ.ም በማራኪ ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ በፈተናው ዙሪያ እስከአሁን የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ግምገማ አካሄዱ።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲም በጎንደርና በአካባቢው የሚገኙ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን እያደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ በዋናነት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት ፈተናውን ስኬታማ በሆነ መንገድ ለማጠናቀቅ የተለያዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ወደ 43 ሺ ተማሪዎችን ለመቀበል የመፈተኛ ክፍሎች፣ የተማሪ አቀባበል፣ የመኝታ፣ የመብራትና የውሃ አገልግሎት፣ እንዲሁም የምግብ ግብአትና ልዩ ልዩ ግብአቶችን አስቀድሞ የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ገልፀዋል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
9.1K views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 16:49:43 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገለፀ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስታውቋል ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የመፈተኛ ተቋማት በማዘጋጀት በኩል ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መመሪያ ሀላፊ አ/ቶ ጌታሁን ፈንቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በዞኑ ተማሪዎች የሚፈተኑባቸው አምስት ተቋማት እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል ።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
8.1K viewsedited  13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 13:04:37 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል።

የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተፈቀዱ ነገሮች፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተከለከሉ ነገሮች፦

➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት)፣ ህክምና መስጫ መርፌ መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር)

➣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

➣ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

https://t.me/Temhert_Minister
https://t.me/Temhert_Minister
1.7K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 10:46:50
PREMIUM DUOLINGO TEST PAYMENT SERVICE

በተለያዩ አለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች የትምህርት እድል ( SCHOLARSHIP ) ለማግኘት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃት ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ያውቃሉ ታዲያ በብዙዎች ተቀባይነት ይለውን DUOLINGO PROFICENCY TEST ን ለመውሰድ አስበው እንዴት መክፈል እንዳለቦት ግራ ገብቶታል

Millions of students are using the Duolingo English Test to get accepted to the school of their choice.

DUOLINGO በመላው አለም ከ TOFEL እና IELTS ቀጥሎ ከ 5000 በላይ በ Duke ,coloumbia university ,  Yale , jhon hopkins ን ጨምሮ አለማቀፍ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው የ ENGLISH LANGUAGE PROFICIENCY ፈተና ነው ።

@leinadani
               በ  2999 Birr  ብቻ

በ 1 ሰዓት ውስጥ የሚጠናቀቀውን  ፈተና በማንኛውም ቦታ ወስደው በ 2 ቀናት ውስጥ ውጤቶን ይቀበሉ ።

ክፍያ በአካል (CASH ) ወይንም በ Mobile Banking  እና Tele Birr

No matter where or what you want to study, the test is a convenient way to certify your English.

RE-EXAM ለሚወስዱ በ 50 % ቅናሽ እናስተናግዶታለን ።

                 በ  2999 Birr  ብቻ

የ DUOLINGO ፈተናን ወስዳቹ ውጤት እስከሚመጣላቹ የምትፈልጉትን ሙሉ ድጋፍ ከኛ ታገኛላቹ ።

በ +251965312666 ወይንም @leinadani ያገኙናል
2.8K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 23:10:08 Being fluent in english might be easier than you think

Spoken English
Reading
Writting
phrasal Verbs

Click here, you won't regrate
4.1K views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 16:43:15
አሳዛኝ ዜና

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
4.5K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 18:19:22
በአዲስ አበባ 49 ሺህ 203 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ይወስዳሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናው የሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፦

• አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
• ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
• የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
• አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
• የፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት

ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብ እና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በብሔራዊ ፈተናው ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናውን ለማስፈፀም ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
642 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 14:02:56
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናዉን ለማስተግበር ከተቋቋመዉ ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክፍለ ከተማ የትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
2.3K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ