Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት በቤቴ🔝

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_bebete
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...
For comment @Tmhert_bebete_info_bot
Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-08 23:44:10 በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ተቀጥሮ ያለአግባብ ደመወዝ ሲቀበል የነበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

ተከሳሽ ኢያሱ ባጫሊ የተባለው ግለሰብ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመገልገል ወንጀል በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ በእስራት ተቀጥቷል።

ተከሳሹ በሼይ ቤንች ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅህፈት ቤት ውስጥ በመጋቢት 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከሪፍት ቫሊ ዩንቨርስቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ በማስመሰል በሀሰት የተዘጋጀ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ ስራ ይቀጠራል።

የግለሰቡን የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥ ለተቋሙ በተፃፈ ደብዳቤ ግለሰቡ ከዩኒቨርሲቲው የተሰጠው ምንም ዓይነት ትምህርት ማስረጃ አለመኖሩን የሚገልፅ ደብዳቤ በመግለፁ ክስ ይመሰረትበታል።

ከዐቃቤ ህግ የቀረበትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት ተከሳሽ ኢያሱ ባጫሊ በሁለት አመት ከሶስት ወር ፅኑ እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ገፅታ ግንባታ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
4.9K viewsedited  20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 10:54:18
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግል ተማሪዎች ክፍያን በእጥፍ መጨመሩ ቅሬታ አስነሳ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለግል ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ላይ የ100 በመቶ ጭማሪ ማድረጉ ከተማሪዎች ቅሬታ ቀርቦበታል።

በዚህም ከፍተኛ ቅሬታ አድሮብናል ያሉት ተማሪዎቹ፣ በተለይ በዚህ ዓመት ለመማር እቅድ ይዘው የነበሩ አዲስ ተመዝጋቢዎች፣ የመግቢያ ፈተናውን ከተፈተኑ በኋላ የዋጋ ጭማሪውን ሲመለከቱ ብዙዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል።

ከገንዘብ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ለተማሪዎች መብታቸውን የሚያስከብርላቸው ጠንካራ ተቋም ባለመኖሩ የትምህርት ተቋማት ብዝበዛ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
896 views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 19:23:31
በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ የተወሰነው ሥርዓተ ትምህርት አብዛኛውን የማኅበረሰብ ክፍል እና ምሁራንን ሲያነጋገር እንደነበር ይታወሳል፡፡

ሥርዓተ ትምህርቱ ‹‹የግል ትምህርት ቤቶችን ያላማከለና በቂ የሆነ ጥናት ያልተደረገበት›› በማለት የሚከራከሩም አሉ፡፡

ሥርዓተ ትምህርቱ ከመስከረም 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ቢጀምርም የውጭ አገር ሥርዓተ ትምህርትን የሚከተሉ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡

መንግሥት ሥርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እንዲተገበር በጥብቅ ያሳሰበና ይህንን በማይተገብሩ ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ያስታወቀ ቢሆንም እምቢተኝነቱ ይታያል፡፡

የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ፣ ከመንግሥትና ከግል ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ኃላፊዎች ጋር በአፍ መፍቻ ቋንቋ እና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ውይይት መደረጉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ

https://www.ethiopianreporter.com/112391/
3.2K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 21:16:23 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች አዲስ ተማሪ መቀበል እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይፋ የተደረገው መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል አሳውቋል።

በመሆኑም ፦ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣ የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አሳውቋል፡፡

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
2.4K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 19:11:18
አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሀፍት ህትመት ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የምህራን መምሪያ እና የተማሪዎች መፅሀፍት የህትመት ሥራ ከሚያከናውኑ ድርጅቶች ጋር በተገባው ውል መሰረት ህትመቱ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

እስከዛ ድረስ መፅሀፍቱ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በሶፍት ኮፒ እንዲደርሳቸው መደረጉን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ ተናግረዋል።

ዘንድሮ ወደ ትግበራ ለገባው ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁት መፅሀፍት እና የመምህራን መምሪያ ህትመት ለነባሩ ስርዓተ ትምህርት ወጪ ከተደረገው በ57 ሚሊዮን ብር ያነሰ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
3.4K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 23:13:19 እንግሊዝኛ ከቻላችሁ እሄ ቻናል በፍጹም እንዳያመልጣችሁ, በጣም ለሂወታችሁ ጠቃሚ የሆነ ነው
1.7K views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 07:17:13
የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃዎች ስለሚበዛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ውጤቱ የሚመጣው ያልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኋላ አንድ ላይ የሚመጣ ይሆናል።

በሰላም እና ፀጥታ ምክንያት ፈተና ያልተቀመጡ ተማሪዎች በቅርብ ጊዜ ይፈተናሉ። (ከ 56,000 በላይ ተማሪዎች )

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
5.9K views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 13:42:31
አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሀፍትን ለግል እና ለመንግስት ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

እስካሁን 1.2 ሚሊዮን መፅሀፍት በከተማዋ ለሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ተደራሽ መደረጉ ተመላክቷል።

መፅሀፍቱ በዚህ ወር መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተደራሽ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በሶፍት ኮፒ እንዲደርሳቸው መደረጉን ቢሮው ገልጿል።

በተያያዘም የውጭ አገር ስርዓተ ትምህርትን በመጠቀም የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው መደረጉን የአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል፡፡  

በአፍ መፍቻ ቋንቋ የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት ትተው የውጭ አገር ስርዓተ ትምህርትን ተጠቅመው የሚያስተምሩ 26 የግል ትምህርት ቤቶች የመጀመርያ ዙር ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ባለሥልጣኑ ጠቁሟል።

በአዲስ አበባ ከ1, 500 በላይ የግል እና የመንግስት የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
7.3K views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 22:31:10 When is your birthday month?
2.4K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 21:51:07
አፕል በቀጣይ የሚያመርታቸው የአይፎን ስልኮቹ የUSB-C የቻርጀር እና የዳታ ኬብል እንደሚቀበሉ ገለፀ።

ቀደም ሲል በአውሮፓ ህብረት ሁሉም ስልኮች እና ታብሌቶች በ 2024 USB-C  የቻርጀር እና ዳታ ኬብል እንዲቀበሉ የተላለፈ ህግ እንደነበረ ይታወሳል። ነገር ግን ይህ ህግ ልክ እንደ አፕል ላሉ የራሳቸውን የፈጠራ ዲዛይን ለሚጠቀሙ ድርጅቶች ትልቅ ስጋት ሆኖ ከርሟል።

የአፕል አይፎን ተጠቃሚዎች ከአፕል ውጪ በሌላ ድርጅት የተመረቱ USB-C ቻርጀር፣ ዳታ ኬብሎች እና ሌሎችም መሳሪያዎች እንዳይገዙ እንደሚፈልጉና የእነዚ አይነት ቁሶችን ሙሉ ለሙሉ በአፕል ድርጅት እንዲሸጡ ፍላጎት ስለነበራቸው እንጂ የዚህ አይነት ጥያቄ በተደጋጋሚ ይደርሳቸው እንደነበር ባለሞያዎች ይገልጻሉ።

የታዋቂው የቴክኖሎጂ ድርጅት አፕል የበላይ ሀላፊዎች በውሳኔው ደስተኞች ባይሆኑም የአለም መንግስታቶች ብዙ ነገር የማድረግ ስልጣን ስላላቸው አፕልም ይህን ውሳኔ ከመቀበል ውጭ ብዙ አማራጭ እንደሌላችው የአፕል ምክትል ፕሬዚዳንት ግሬግ  ጆስዊአክ ገልጸዋል።

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
4.8K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ