Get Mystery Box with random crypto!

★★የሱሀቦች ዘመን

የቴሌግራም ቻናል አርማ suhabaa — ★★የሱሀቦች ዘመን
የቴሌግራም ቻናል አርማ suhabaa — ★★የሱሀቦች ዘመን
የሰርጥ አድራሻ: @suhabaa
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.92K
የሰርጥ መግለጫ

🌹የሱሀቦች ዘመን 🌹
አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 19)
https://t.me/lYllYi

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 21:42:35 ሁልም የሰዉ ልጅ ያለ ምንም ዘር ቀለም ሀብት ልይነት ኡኩል የሚሆንበት ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነዉ
ኢስላም ማለትኮ! የሰው ልጅ ይችን ዐለም ከመቀላቀሉ በፊት ጀምሮ የነበሩትና የአሏህን ትእዛዝ ፈፅሞ ነቅፈው የማያውቁት መላኢኮች የሚከተሉት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* የመጀመሪያው የሰው ዘር፣ ዝንጀሮን ፈፅሞ የማይመስሉትና የሚያምር ተክለ ቁመና የነበራቸው ታላቁ ነብይ አደም ዐለይሂ ሰላም ይከተሉት የነበረና ለልጆቻቸውም ያወረሱት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ነቢዩሏሂ ኑህ ዐለይሂ ሰላም ህዝቦቻቸው ከእሳት እንዲድኑ በማሰብ 950 አመት የለፉበትና የተሰቃዩለት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ነቢዩሏህ ኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም ለህዝቦቻቸው ከማስተማር ወደ ኃላ ባለማለታቸውና በዚሁ ላይ በመፅናታቸው ምክንያት ከነበልባሉ ከባድነት የተነሳ ሰዎች ሊጠጉት ወዳልቻሉት ከባድ እሳት የተወረወሩለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ነቢዩሏህ የህያ ዐለይሂሰላም ሀቅን በመናገራቸው ምክንያት በዘመኑ በነበረው አረመኔ ንጉስ ምክንያት የታረዱለት ሀይማኖት ነው።
ኢስላም ማለትኮ!! የኛ ውድ ነብይ አስማተኛ፣ ጠንቋይ፣ ገጣሚ ወዘተ እያሉ የመካ ሙሽሪኮች ክብራቸውን ሲያጎድፉት በትእግስት ያሳለፉለት
ዑቅበቱ ኢብኑ አቢ ሙዐይጥ የተባለው ጠማማ ሰው ሩኩዕ ላይ እያሉ ጀርባቸው ላይ የግመሉን ሽል አምጥቶ ሲጥልባቸው እና አንገታቸው ላይ ምልክት እስከሚወጣ ድረስ በቀሚሳቸው ጠፍርቆ ሲይዛቸው እንደምንም ሳይቆጥሩ ታግሰው ያሳለፉለት፤ በኡሁድ ዘመቻ ላይ ጥርሳቸውን የሸረፉለትና ደማቸውን ያፈሰሱለት፤
ለጧኢፍ ሰዎች በአኺራ ከእሳት ነበልባል ነፃ የሚያደርጋቸውን መንገድ ለመጠቆም ቢሄዱላቸው ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ እንዲሉ እብድና ህፃናትን አስልከው ያስደበደቧቸው ቢሆንም የተራራው መላኢካ መጥቶ ተራራውን አላተሜ ላጥፋልህ ሲላቸው እርሳቸው ግን በቀሉን ትተው አሏህ ከነርሱ መልካም ሰዎችን ሊያወጣልኝ ይችላል በማለት የስቃዩን ወቅት በትእግስት የገፉለት ሀይማኖት ነው።
*ምን ይሄ ብቻ!* ከነብያት ህይወት ወጣ ብለን ስንመለከተው ይህ እስልምና ብዙ መስዋእትነት ተከፍሎበት የመጣ እንደሆነ እንገነዘባለን።
አዎ *ኢስላም ማለትኮ!* የፊርዐውን ልጅ ፀጉር አበጣሪ የነበረችው አሏህን ፈሪ ሴት ርህራሄ የለሹና ግብዙ ፊርዐውን በአሏህ ክደሽ በኔ እመኚ ሲላት አሻፈረኝ ብላ በእምነቷ በመፅናቷ ምክንያት ዐይኗ እያየ ልጆቿን የፈላ ዘይት ውስጥ ሲከታቸውና አጥንታቸው ከስጋቸው ሲለያይ እያየች ከመታገሷ በላይ እርሷንም ሲከታት ነቅነቅ ሳትል እስከ ህልፈተ ህይወቷ ነክሳ የያዘችው ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ታላቁ ሶሀባ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሱብህ ሶላትን ለማሰገድ በቆሙበት ወቅት አቡ ሉእሉአተል መጁሲይ በተባለ ሰው በተደጋጋሚ ተወግተው የተሰውለት ሀይማኖት ነው፤
*ኢስላም ማለትኮ!* ሰይዱና ዑስማን ኢብኑ ዐፋን ኢስላምን ሽፋን ባደረጉ ሁይሎች እጃቸውን የተቆረጡለትና ከዚህም በላይ ራሳቸውን የሰጡለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* አራተኛው ኸሊፋና የምእመናን መሪ የነበሩት ሰይዱና ዐሊይ ምንም እንኳ ከውስጥ የመነጨ ባይሆንም ሶላት እንሰግዳለን ከማለታቸው የተነሳ ግንባርቸው በቆሰሉ፣ ፂማቸውን በማሳደግና ሽርጥ በመታጠቅ የነቢዩን መስመር የተከተሉ በሚመስሉና ቁርአንን ቢያነቡም ከጉሮሯቸው አይዘልም በማለት ነቢያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በገለጿቸው አፈንጋጭ ቡድኖች እጅ ራሳቸውን ተፈንክተው የተሰውለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* የመጀመሪያዋ ሸሂደህ ሱመያና ባለቤቷ ያሲር እምነታችንን አንለቅም በማለታቸው ምክንያት ብቻ ከብዙ ግፍና ስቃይ በኋላ ልቡ በታወረው አቡጀህል አማካኝነት ህይወታቸውን የሰውለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ታላቁ ሸሂድና የሸይኻችን ዋና ተማሪ የነበሩት ሸይኽ ኒዛር አል ሀለቢይ ሙስሊሙ በፋሽን ሀይማኖት እንዳይሸወድ የወሀቢያን ጉድ ግልፅልፅ አድርገው በመናገራቸውና በማስጠንቀቃቸው ምክንያት ብቻ በነዚሁ የሰው ነፍስ ማጥፋት እንደምንም በማይቆጥሩት ወሀቢያዎች እጅ ከ30 በላይ የጥይት ማእበል ዘንቦባቸው የተሰውለት ሀይማኖት ነው።
መች በዚህ ያቆምና ወደ ሀገራችንስ ጎራ ስንል ስንቱና ስንቱ ነው ለዲኑ ሲል መስዋእትነትን የከፈለው!?
አዎ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። የነቢዩ አዛን አድራጊና በህይወት እያሉ ጀነት እንደምትናፍቃቸው ከተገለፁት ሶሀባዎች መካከል አንዱ የሆኑት የሀበሻው ጀግና ቢላል ኢብኑ ረባህ እምነትክን ልቀቅ በማለት ጨካኙ አሳዳሪው ኡመያ ኢብኑ ኸለፍ በጠራራ ፀሀይ ላይ አንጋሎና ትልቅ ቋጥኝ ድንጋይ ጭኖ ሲያሰቃየውና ከዚህም በላይ አንገቱ ላይ ገመድ በማጥለቅ የመካ ህፃናት በየመንገዱ እንዲጎትቱት ሲያደርግ እርሱ ግን አሀድ አሀድ እያለ ከእምነቱ ነቅነቅ ሳይል ግፉን ተቋቁሞ ያሳለፈለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ታላቁ ሃፊዝና የሀዲስ ሊቅ እንዲሁም የሀበሻና ብሎም የዐለም መኩሪያ የሆኑት ሸይኽ ዐብዱሏህ ኢብኑ ሙሀመድ አል ሐረሪይ በአረመኔው መሪ ተፈሪ መኮነን(አፄ ሀይለ ስላሴ በሚባለው) ለሁለት ጊዜ የታሰሩለትና በኋላ ላይም ወደ ተለያዩ ሀገራት ችግርና ረሀቡን ተቋቁመው ሙስሊሙ ኡማ በፋሽን ሀይማኖት እንዳይታለል የቁርአንና የሀዲስ ማስረጃዎችን ቀለል ባለ መንገድ በማቅረብ ሙስሊሙን ከችግር ለመታደግ እድሜ ልካቸውን የለፉለት ሀይማኖት ነው
*ኢስላም ማለትኮ!* የሀገራችን ሙስሊም ሴቶች በአፄዎቹ አገዛዝ እምነታችሁን ልቀቁ ሲባሉ አንለቅም በማለታቸው ምክንያት ጡታቸውን እየተቆረጡ እንኳ ምንም ሳይበገሩ ታግሰው ያስተላለፉት ሀይማኖት ነው፤
*ኢስላም ማለትኮ!* እንፍራንዝ ላይ የነበሩት ታላቁ የሀገራችን ዐሊም ሸይኽ ዐብዱሏህ ዋጤ በነዚሁ ወሀቢያዎች እጅ ጋዝ ተርከፍክፈውና ተቃጥለው የተገደሉለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* እምነቴን በዱንያዊ ጥቅማ ጥቅም አለውጥም ብለው በትክክለኛው የአህሉሱና ወል ጀማዐህ እምነት ላይ በመፅና
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
317 views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:42:35
ጂብሪል ዐ ሰ አንድ ቀን ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ።ረሱል ሰ ዐ ወ በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ
እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁት ሰዐት የጀሀነም አቀጣጣዮችን አላህ እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን
ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም"
ብሎ መለሰላቸው።
ረሱል ሰ ዐ ወ፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት።
ጅብሪልም ዐ ሰ፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ
እስክትሆን ድረስ
ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም
1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም
ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ. የመርፌ ቀዳዳ
ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት
ይቃጠል ነበር።ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.ከጀሀነም ሰዎች
ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር። ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ...አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም
ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይቀልጣል።ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ. በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር።
ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት
ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው።7 በሮች አሏት።ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ መለሰላቸው።ረሱልም ሰዐወ፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር
ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት
ያስኬዳል።እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል። የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ
የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል።ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ
ይታሰራል።እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል። ከዚያም
በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ
ይመቷቸዋል።
ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ
መለሰላቸው።ነቢያችንም
ሰ ዐ ወ፦" በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?" ብለው ጠየቁት።ጅብሪልም ዐ ሰ፦
"በታችኛው በር የሚገቡት
1፦ሙናፊቆች
2፦በዒሳ ዐሰ ማዕድ የካዱት
3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ የበሩ ስም ሀዊያ ይባለል። ሁለተኛው በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው።
ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም ለዟ ይባላል።
አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል።
ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች
ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት
ያዘው።ነቢያችንም ሰ ዐ ወ፦" ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው
ሲጠይቁት ጂብሪልም ዐ ሰ፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ
ሲመልስላቸው ረሱል ሰ ዐ ወ እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን ሰ ዐ ወ ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት
ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች
ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ
ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ።
/ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/
ረሱል ሰ.ዐ.ወ ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ።
ጅብሪልም፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ?እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው ።
#መሀመድ ይመር
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
251 views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:42:34 "አነስ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ነገሮችን አመቻቹ፤ አታጨናንቁ፤ አበሰሩ፤ (ሰዎች ከኢስላም) እንዲሸሹ አታድርጉ፡፡››

(ቡኻሪ ዘግበውታል)
- ቡኸሪ ዘግቦታ"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ከታች ያለዉን ሊንክ ከፍተዉ ፕሮግራሙን ለ እርሶም ያወርዱ
https://play.google.com/store/apps/details?id=hadith.bilal.app
244 views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:15:30 ለራስህ ስትል መልካም ሁን!!!
ለሰው መልካም መሆን ካልቻልክ ክፋትን አትመኝለት ::
ሰውን መርዳት ካልቻል ባገኘው ነገር አትመቀኘው ይልቁን በረካ እንዲያደርግለት ዱዐ አድርግለት ::
ለሰው ጥሩ መሆን ካልቻልክ መጥፎ ግን አትሁን መጥፎነትህ ቀን ቆጥሮ ይክስሀል ::
እርግጠኛ ሁን ዛሬ የጎዳህ ነገ እሱንም የሚጎዳው ሰው አያጣም :: ዛሬ ያስለቀሰህ ሰው ነገ የሚያስለቅሰው ሰው አያጣም ::
ምድር ትዞራለች አንተ የሚጠበቅብህ በሰብር መኖር ብቻ ነው።
ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደውና የዋህነት አይጎዳም::
አንዳንድ ሰዎች የዋህ ስንሆንላቸው እንደሞኝ ያዩናል ነገር ግን ያ የዋህ ሰው ካንተ በላይ ብልጥ መሆኑን እወቅ ::
ሰው ካስቀየመክ ሰው ካስከፍ ይቅርታ አድርግለት በአንተ ይቅርታ ማለት እሱም ይማርበታል በስራውም ነገር ያፍራል::
ለራስህ ስትል መልካም ሁን መልካምነት አያስከፍልም ::
ዛሬ ያጣነው ነገ እናገኘዋለን ዛሬ ያገኘነው ነገ እናጣዋለን ዱንያ እንዲህ ናት ፡፡
የሱሀቦች ዘመን
ሳኒ ይመር
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
435 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:15:30 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ [2:186]
ኢላሃና!
••❥ ወደ አንተ ካልሆነ ልመና ጩኸት ነው
••❥ ባንተ ላይ ካልሆነ ተስፋም ባዶነት ነው
••❥ ስላንተ ካልሆነ ንግግርም ውሸት ነው
••❥ ካንተ ጋር ካልሆነ ንግድም ኪሳራ ነው
••❥ ስለ ክብርህ ካልሆነ ፍቅርም እብደት ነው
••❥ በመንገድህ ካልሆነ ሞትም ጀሀነም ነው

@suhabaa
━━━━━ ━━━━━
https://t.me/lYllYi
301 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:15:30 ትርፋማዉ ንግድ
አላህ የመናገርን ፀጋ በመስጠት የሰው ልጅ ከሌሎች ፍጡራን በላይ አስበለጠዉ ፡፡ ለዚህም ምላስን የመነጋገሪያ መሳሪያ አደረጋት ፡፡ በመሆኑም ምላስ ለደግም ሆነ ለመጥፎ ያገለግላል ፡፡ ምላሱን ለኸይር ነገር የተጠቀመ ሰዉ በዱኒያ መልካም ደስታ በአኸራም ለጀነት ትልቅ እድል ያደርሰዋል ፡፡
ከቁርአን መቅራት በህዋላ ጊዜ ሊጠፋበት የሚገባ ታላቅ ነገር ቢኖር አላህን ማዉሳት ( ዚክር ) ነዉ ፡፡
የዚክር ጥቅሞች :-
ከአላህ ዘንድ ዉዴታን : ቅርበትን ; ወደሱ መመለስን ያወርሳል ፡፡
ከልብ ጭንቀትን : ልዩ ልዩ ሀሳቦችን ያስወግዳል ፡፡
ደስታን ያጎናፅፈናል ፡፡ ዚክር የቸገረን ነገር ያገራል ፡፡
ዚክር የልብ ፈውስ : ሀይሉና የትኛውም ጣእም የሚያስተካክል ምግቡ ነዉ ፡፡

ዚክር ማነሱ የንፍቅና ምልክት
ነዉ ፡፡
ሳኒ ይመር
https://t.me/Sanimuhaba
316 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:26:56 ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ في ظِلِّهِ، يَومَ لا ظِلَّ إلّا ظِلُّهُ: الإمامُ العادِلُ، وشابٌّ نَشَأَ في عِبادَةِ رَبِّهِ، ورَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ في المَساجِدِ، ورَجُلانِ تَحابّا في اللَّهِ اجْتَمعا عليه وتَفَرَّقا عليه، ورَجُلٌ طَلَبَتْهُ امْرَأَةٌ ذاتُ مَنْصِبٍ وجَمالٍ، فَقالَ: إنِّي أخافُ اللَّهَ، ورَجُلٌ تَصَدَّقَ، أخْفى حتّى لا تَعْلَمَ شِمالُهُ ما تُنْفِقُ يَمِينُهُ، ورَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خالِيًا فَفاضَتْ عَيْناهُ.﴾

“ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት በቂያማ ቀን በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። እነሱም፦ ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ ላይ ያደገ ወጣት፣ ልቡ ከመስጂዶች ጋር የተንጠለጠለን ሰው፣ ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ፣ የልቅናና የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት (ለዝሙት) ጠርታው ‘እኔ አላህን እፈራለሁ’ ያለ ሰው፣
ምፅዋትን ‘ሰደቃ’ የሚሰጥ ሆኖ ቀኝ እጁ የሚመፀውተውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ የሚደብቅ ሰው፣ አላህን በማስታወስ አይኑ የሚያነባ ሰው ናቸው።”

ቡኻሪ (1423) ሙስሊም (1031) ዘግበውታል
ሳኒ ይመር ( @USTAZSANI )
የሱሀቦች ዘመን
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
465 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:26:47
የሱሀቦች ዘመን
ኢስላማዊ ፌስቡክ ፌጅ
በፌስቡክ Follow በማረግ ይቀላቀሉን ፡፡
ኢስላማዊ እዉቀት ለሁልም ፡፡
Follow Our Facebook page ( website www.suhabaa.com )
365 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:26:47 ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿كلُّ ذنبٍ عسى اللهُ يغفرُهُ، إلّا مَنْ مات مُشرِكًا،﴾
“አላህ የታመፀባቸውን ሁሉንም ወንጀሎች ምህረት ያደርጋል። በሱ ላይ አጋርቶ የሞተ ሲቀር።”
አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 4270
ሳኒ ይመር ( @USTAZSANI )
የሱሀቦች ዘመን
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
379 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 17:49:29 ይቅር ባይ ሁን ቂም አትያዝ

ቅይም አርግዘህ ክፋትን ከምትወልድ፣ የሸይጧንን ሙራድ ከምትሞላና ነፍስህን በስቃይ አለንጋ ከምትገርፍ ፡፡ ይቅር ባይ ሆነህ የአላህን ውዴታ ማግኘት፣ የውስጥህን ሰላም ማግኘትህና ሸይጧንን ማስቆጨትህ ለድርድር የማይቀርብ ትልቅ ምርጫ ነው።
አላህ አፏ ባዮችን ይወዳልና የሱን ውዴታ አስበልጥ
ለአላህ ብሎ ዝቅ ያለ አላህ ከፍ ያደርገዋል
አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና ታገስ
አላህ አፋ እንዲልህ የምትፈልግ ከሆነ አንተም ሌሎችን አፋ በል
አላህ እንዲያዝንልህ የምትፈልግ ከሆነ አንተም ለባሮቹ እዘን
አላህ ይቅር እንዲልህ የምትፈልግ ከሆነ አንተም ይቅር ባይ ሁን
ሸኽ ኢብኑ ባዝ አላህ ይርሀማቸውና እንዲህ ብለዋል።
ነፍስያህን አፋታ (ይቅር ባይነትን) ካስለመድካት፦
ነፍስህ ሰላም ታገኛለች
ቀልብህ ይረጋጋል
አላህና ባሮቹ ዘንድ ደረጃህ ከፍ ያለ ይሆናል።
حديث المساء ٢١٢
ቂም ይዘህ ምን ታተርፋለህ
ይቅር ማለትህ እዝነትን እንደሚወልድ ሁሉ ቂም መያዝህ መበቀልን ይወልዳልና ተጠንቀቅ።
መች እንደምትሞት አታውቅምና እስከነ ጥፋትህ አላህ ፊት ከመቆምህ በፊት ነገ ዛሬ ሳትል የበደልከውን ሰው ይቅርታ ጠይቅ። ኩራትና መኮፈስን ከውስጥህ አስወግድ። ሸይጧን ከአላህ እዝነት ያባረረው ይህ ኩራቱ ነውና ተጠንቀቅ።
ከተበደልክ ደሞ ይቅር ባይ ሁን። ለምን ተነካሁ ለምን ይህ ተባልኩ በማለት የግድ ሁሉ ነገር እኔ እንዳልኩት ይሁን አትበል። አንዳንዴ እያወክም ቢሆን ተሸነፍ። አላህ ዘንድ ያለው የተሻለ ነውና ያንን ምረጥ። የግድ የማትተወው ሀቅ ካለ ደሞ ሳትቀያየምና ሳትቆራረጥ በአግባቡና በስርአቱ ጠይቅ።
በጣም የሚገርመው ደሞ እናት አባቱን፣ ወንድም እህቱን፣ ሚስትና ልጁን አልፎም ወድ ጓደኛውን ለትንሽ ጉዳይ ብሎ ተቆራርጦ፣ ተኮራርፈው፣ በጎሪጥ የሚተያዩ፣ በአሽሙር የሚተቻቹ፣ እንደ ጠላት የሚተያዩ፣ ሸይጧንን በመታዘዝ የሱን አላማ የሚያሳኩና የሰሩትን መልካም ስራ አላህ ዘንድ እንዳይደርስ በመሀል እንዲንጠለጠል የሚያደርጉ ብዙዎች አሉ።
ይቅርታ መጠየቅና አፋ ማለት የበታችነት ሳይሆን የበላይነት፣ የመዋረድ ሳይሆን የአዋቂነትና በሳልነት አልፎም የአርቆ አሳቢነት ምልክት ነው።
አላህ ሆይ ከዚህ ክፋ በሽታ አንተው ጠብቀን

ሳኒ ይመር ( @USTAZSANI )
የሱሀቦች ዘመን
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
549 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ