2022-08-27 20:09:59
ታጋሾችን አበስራቸው›› (2:155)
ትዕግስት የሰው ልጅ ሊኖረው ከሚገቡ ድንቅ ስብዕናዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በተለይ በአላህ ያመኑ ሙዕሚኖች ሊሸለሙበት የሚገባ ውድና ድንቅ ጌጥ ነው፡፡ አላህ በተለያዪ የቁርአን አንቀፆች ስለ ትእግስ አውስቷል መልዕክተኛው በሀዲሳቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፣ በህይወታቸውም ብዙ ስቃይና መከራዎችን በትእግስት በማለፍ ተግባራዊ ትምህርት ሰጥተው አሳይተዋል፡፡ የሰው ልጅ በህይወቱ አንዴ በችግርና ሰቆቃ እየታሸ ሌላ ጊዜ ድሎትና ምቾት ፈንጠዝያ እየተፈተነ የሚኖር ፍጡር ነው።
አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ ቁርአን ስለ ሶብር እንዲህ ብሏል፦
‹‹ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎች በመቀነስ በእርግጥ እንፈትናችኃለን፡፡ ታጋሾችንም (በጀነት) አበስራቸው››
(አል በቀራህ:155)
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ታገሱ››
(አል-ዒምራን፡200)
የኢስላም ሊቃውን አንድ ሰው አላህ መልካም ችሮታውን ውሎለት ቢያመሰግን ይሻለዋል ወይስ ፈተና ገጥሞት በዚያ ላይ ቢታገስ በሚለው ሀሳብ ላይ የተለየዩ ሀሳቦችን ከሰነዘሩ ከባድ ልዩነትን ካንፀባረቁ በኃላ በመጨረሻ የደረሱበት መቋጫ ሀሳብ ግን በችግር ላይ መታገስ ይሻለዋለዋል የሚል ነበር።
ምክንያቱም ታላቁ አምላካችን እንዲህ ብሏልና ነው፦
‹‹ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው›› (ዙመር፡10)
ያለ መለኪያ፣ያለ ሚዛን ለሰብረኞች ምንዳቸውን ይሰጣቸዋል፡፡ አላህ ካዘጋጃቸው ምንዳዎች ለታጋሾች ከተዘጋጀው የሚበልጥ ምንደ ያለው የለም፡፡
ምንዳ የሚባለውን ነገር ለምሳሌ እንደ "ፍሬ" አድርገን ብንወስደው አመስጋኞች ከፍሬው ተቆጥሮ ሲሰጣቸው ታጋሾች ግን እየታፈሰ ያለገደብ ይሰጣቸዋል።
ስለዚህም ታገስ ምንዳህን ያለ ሀሳብ ያለ ገደብ እፈስ!
‹‹የታገሰና ምህረት ያደረገም ሰው ይህ ከምርሮቹ (ከተፈላጊዎቹ) ነገሮች ነው፡፡›› (ሹራ፡43)
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዳዱ፡፡ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና››(አል በቀራ፡153)
የአኼራን ምንዳን በመፈለግ ነፍስን ከመጥፎ በመከልክል አላህን ከማመፅ በማቀብ ታገዙ፡፡
‹‹ከእናንተም ታጋዮቹንና ታጋሾቹን እስከምናውቅ፣ ወሬዎቻችሁንም እስከምንገልፅ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኃለን›› (ሙሀመድ፡31)
ይህ ማለት እውነተኛው ታጋሽ አማኝ ከውሸተኛው እስከሚለይ ድረስ ላማለት ነው፡፡ ስለዚህ አማኞች ነቃ ብለው ራሳቸውን ሊፈትሹ ይህን ፈተና ለማለፍ ቀን ከሌት ሊጥሩ ይገባል! ለዚህም ትእግስት ያስፈልጋልና ታገሱ
ሳኒ ይመር ( @USTAZSANI )
የሱሀቦች ዘመን
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
138 views17:09