Get Mystery Box with random crypto!

ሁልም የሰዉ ልጅ ያለ ምንም ዘር ቀለም ሀብት ልይነት ኡኩል የሚሆንበት ሀይማኖት ኢስላም ብቻ | ★★የሱሀቦች ዘመን

ሁልም የሰዉ ልጅ ያለ ምንም ዘር ቀለም ሀብት ልይነት ኡኩል የሚሆንበት ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነዉ
ኢስላም ማለትኮ! የሰው ልጅ ይችን ዐለም ከመቀላቀሉ በፊት ጀምሮ የነበሩትና የአሏህን ትእዛዝ ፈፅሞ ነቅፈው የማያውቁት መላኢኮች የሚከተሉት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* የመጀመሪያው የሰው ዘር፣ ዝንጀሮን ፈፅሞ የማይመስሉትና የሚያምር ተክለ ቁመና የነበራቸው ታላቁ ነብይ አደም ዐለይሂ ሰላም ይከተሉት የነበረና ለልጆቻቸውም ያወረሱት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ነቢዩሏሂ ኑህ ዐለይሂ ሰላም ህዝቦቻቸው ከእሳት እንዲድኑ በማሰብ 950 አመት የለፉበትና የተሰቃዩለት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ነቢዩሏህ ኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም ለህዝቦቻቸው ከማስተማር ወደ ኃላ ባለማለታቸውና በዚሁ ላይ በመፅናታቸው ምክንያት ከነበልባሉ ከባድነት የተነሳ ሰዎች ሊጠጉት ወዳልቻሉት ከባድ እሳት የተወረወሩለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ነቢዩሏህ የህያ ዐለይሂሰላም ሀቅን በመናገራቸው ምክንያት በዘመኑ በነበረው አረመኔ ንጉስ ምክንያት የታረዱለት ሀይማኖት ነው።
ኢስላም ማለትኮ!! የኛ ውድ ነብይ አስማተኛ፣ ጠንቋይ፣ ገጣሚ ወዘተ እያሉ የመካ ሙሽሪኮች ክብራቸውን ሲያጎድፉት በትእግስት ያሳለፉለት
ዑቅበቱ ኢብኑ አቢ ሙዐይጥ የተባለው ጠማማ ሰው ሩኩዕ ላይ እያሉ ጀርባቸው ላይ የግመሉን ሽል አምጥቶ ሲጥልባቸው እና አንገታቸው ላይ ምልክት እስከሚወጣ ድረስ በቀሚሳቸው ጠፍርቆ ሲይዛቸው እንደምንም ሳይቆጥሩ ታግሰው ያሳለፉለት፤ በኡሁድ ዘመቻ ላይ ጥርሳቸውን የሸረፉለትና ደማቸውን ያፈሰሱለት፤
ለጧኢፍ ሰዎች በአኺራ ከእሳት ነበልባል ነፃ የሚያደርጋቸውን መንገድ ለመጠቆም ቢሄዱላቸው ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ እንዲሉ እብድና ህፃናትን አስልከው ያስደበደቧቸው ቢሆንም የተራራው መላኢካ መጥቶ ተራራውን አላተሜ ላጥፋልህ ሲላቸው እርሳቸው ግን በቀሉን ትተው አሏህ ከነርሱ መልካም ሰዎችን ሊያወጣልኝ ይችላል በማለት የስቃዩን ወቅት በትእግስት የገፉለት ሀይማኖት ነው።
*ምን ይሄ ብቻ!* ከነብያት ህይወት ወጣ ብለን ስንመለከተው ይህ እስልምና ብዙ መስዋእትነት ተከፍሎበት የመጣ እንደሆነ እንገነዘባለን።
አዎ *ኢስላም ማለትኮ!* የፊርዐውን ልጅ ፀጉር አበጣሪ የነበረችው አሏህን ፈሪ ሴት ርህራሄ የለሹና ግብዙ ፊርዐውን በአሏህ ክደሽ በኔ እመኚ ሲላት አሻፈረኝ ብላ በእምነቷ በመፅናቷ ምክንያት ዐይኗ እያየ ልጆቿን የፈላ ዘይት ውስጥ ሲከታቸውና አጥንታቸው ከስጋቸው ሲለያይ እያየች ከመታገሷ በላይ እርሷንም ሲከታት ነቅነቅ ሳትል እስከ ህልፈተ ህይወቷ ነክሳ የያዘችው ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ታላቁ ሶሀባ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሱብህ ሶላትን ለማሰገድ በቆሙበት ወቅት አቡ ሉእሉአተል መጁሲይ በተባለ ሰው በተደጋጋሚ ተወግተው የተሰውለት ሀይማኖት ነው፤
*ኢስላም ማለትኮ!* ሰይዱና ዑስማን ኢብኑ ዐፋን ኢስላምን ሽፋን ባደረጉ ሁይሎች እጃቸውን የተቆረጡለትና ከዚህም በላይ ራሳቸውን የሰጡለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* አራተኛው ኸሊፋና የምእመናን መሪ የነበሩት ሰይዱና ዐሊይ ምንም እንኳ ከውስጥ የመነጨ ባይሆንም ሶላት እንሰግዳለን ከማለታቸው የተነሳ ግንባርቸው በቆሰሉ፣ ፂማቸውን በማሳደግና ሽርጥ በመታጠቅ የነቢዩን መስመር የተከተሉ በሚመስሉና ቁርአንን ቢያነቡም ከጉሮሯቸው አይዘልም በማለት ነቢያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በገለጿቸው አፈንጋጭ ቡድኖች እጅ ራሳቸውን ተፈንክተው የተሰውለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* የመጀመሪያዋ ሸሂደህ ሱመያና ባለቤቷ ያሲር እምነታችንን አንለቅም በማለታቸው ምክንያት ብቻ ከብዙ ግፍና ስቃይ በኋላ ልቡ በታወረው አቡጀህል አማካኝነት ህይወታቸውን የሰውለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ታላቁ ሸሂድና የሸይኻችን ዋና ተማሪ የነበሩት ሸይኽ ኒዛር አል ሀለቢይ ሙስሊሙ በፋሽን ሀይማኖት እንዳይሸወድ የወሀቢያን ጉድ ግልፅልፅ አድርገው በመናገራቸውና በማስጠንቀቃቸው ምክንያት ብቻ በነዚሁ የሰው ነፍስ ማጥፋት እንደምንም በማይቆጥሩት ወሀቢያዎች እጅ ከ30 በላይ የጥይት ማእበል ዘንቦባቸው የተሰውለት ሀይማኖት ነው።
መች በዚህ ያቆምና ወደ ሀገራችንስ ጎራ ስንል ስንቱና ስንቱ ነው ለዲኑ ሲል መስዋእትነትን የከፈለው!?
አዎ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። የነቢዩ አዛን አድራጊና በህይወት እያሉ ጀነት እንደምትናፍቃቸው ከተገለፁት ሶሀባዎች መካከል አንዱ የሆኑት የሀበሻው ጀግና ቢላል ኢብኑ ረባህ እምነትክን ልቀቅ በማለት ጨካኙ አሳዳሪው ኡመያ ኢብኑ ኸለፍ በጠራራ ፀሀይ ላይ አንጋሎና ትልቅ ቋጥኝ ድንጋይ ጭኖ ሲያሰቃየውና ከዚህም በላይ አንገቱ ላይ ገመድ በማጥለቅ የመካ ህፃናት በየመንገዱ እንዲጎትቱት ሲያደርግ እርሱ ግን አሀድ አሀድ እያለ ከእምነቱ ነቅነቅ ሳይል ግፉን ተቋቁሞ ያሳለፈለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* ታላቁ ሃፊዝና የሀዲስ ሊቅ እንዲሁም የሀበሻና ብሎም የዐለም መኩሪያ የሆኑት ሸይኽ ዐብዱሏህ ኢብኑ ሙሀመድ አል ሐረሪይ በአረመኔው መሪ ተፈሪ መኮነን(አፄ ሀይለ ስላሴ በሚባለው) ለሁለት ጊዜ የታሰሩለትና በኋላ ላይም ወደ ተለያዩ ሀገራት ችግርና ረሀቡን ተቋቁመው ሙስሊሙ ኡማ በፋሽን ሀይማኖት እንዳይታለል የቁርአንና የሀዲስ ማስረጃዎችን ቀለል ባለ መንገድ በማቅረብ ሙስሊሙን ከችግር ለመታደግ እድሜ ልካቸውን የለፉለት ሀይማኖት ነው
*ኢስላም ማለትኮ!* የሀገራችን ሙስሊም ሴቶች በአፄዎቹ አገዛዝ እምነታችሁን ልቀቁ ሲባሉ አንለቅም በማለታቸው ምክንያት ጡታቸውን እየተቆረጡ እንኳ ምንም ሳይበገሩ ታግሰው ያስተላለፉት ሀይማኖት ነው፤
*ኢስላም ማለትኮ!* እንፍራንዝ ላይ የነበሩት ታላቁ የሀገራችን ዐሊም ሸይኽ ዐብዱሏህ ዋጤ በነዚሁ ወሀቢያዎች እጅ ጋዝ ተርከፍክፈውና ተቃጥለው የተገደሉለት ሀይማኖት ነው።
*ኢስላም ማለትኮ!* እምነቴን በዱንያዊ ጥቅማ ጥቅም አለውጥም ብለው በትክክለኛው የአህሉሱና ወል ጀማዐህ እምነት ላይ በመፅና
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA