Get Mystery Box with random crypto!

ትርፋማዉ ንግድ አላህ የመናገርን ፀጋ በመስጠት የሰው ልጅ ከሌሎች ፍጡራን በላይ አስበለ | ★★የሱሀቦች ዘመን

ትርፋማዉ ንግድ
አላህ የመናገርን ፀጋ በመስጠት የሰው ልጅ ከሌሎች ፍጡራን በላይ አስበለጠዉ ፡፡ ለዚህም ምላስን የመነጋገሪያ መሳሪያ አደረጋት ፡፡ በመሆኑም ምላስ ለደግም ሆነ ለመጥፎ ያገለግላል ፡፡ ምላሱን ለኸይር ነገር የተጠቀመ ሰዉ በዱኒያ መልካም ደስታ በአኸራም ለጀነት ትልቅ እድል ያደርሰዋል ፡፡
ከቁርአን መቅራት በህዋላ ጊዜ ሊጠፋበት የሚገባ ታላቅ ነገር ቢኖር አላህን ማዉሳት ( ዚክር ) ነዉ ፡፡
የዚክር ጥቅሞች :-
ከአላህ ዘንድ ዉዴታን : ቅርበትን ; ወደሱ መመለስን ያወርሳል ፡፡
ከልብ ጭንቀትን : ልዩ ልዩ ሀሳቦችን ያስወግዳል ፡፡
ደስታን ያጎናፅፈናል ፡፡ ዚክር የቸገረን ነገር ያገራል ፡፡
ዚክር የልብ ፈውስ : ሀይሉና የትኛውም ጣእም የሚያስተካክል ምግቡ ነዉ ፡፡

ዚክር ማነሱ የንፍቅና ምልክት
ነዉ ፡፡
ሳኒ ይመር
https://t.me/Sanimuhaba