Get Mystery Box with random crypto!

ለራስህ ስትል መልካም ሁን!!! ለሰው መልካም መሆን ካልቻልክ ክፋትን አትመኝለት :: ሰው | ★★የሱሀቦች ዘመን

ለራስህ ስትል መልካም ሁን!!!
ለሰው መልካም መሆን ካልቻልክ ክፋትን አትመኝለት ::
ሰውን መርዳት ካልቻል ባገኘው ነገር አትመቀኘው ይልቁን በረካ እንዲያደርግለት ዱዐ አድርግለት ::
ለሰው ጥሩ መሆን ካልቻልክ መጥፎ ግን አትሁን መጥፎነትህ ቀን ቆጥሮ ይክስሀል ::
እርግጠኛ ሁን ዛሬ የጎዳህ ነገ እሱንም የሚጎዳው ሰው አያጣም :: ዛሬ ያስለቀሰህ ሰው ነገ የሚያስለቅሰው ሰው አያጣም ::
ምድር ትዞራለች አንተ የሚጠበቅብህ በሰብር መኖር ብቻ ነው።
ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደውና የዋህነት አይጎዳም::
አንዳንድ ሰዎች የዋህ ስንሆንላቸው እንደሞኝ ያዩናል ነገር ግን ያ የዋህ ሰው ካንተ በላይ ብልጥ መሆኑን እወቅ ::
ሰው ካስቀየመክ ሰው ካስከፍ ይቅርታ አድርግለት በአንተ ይቅርታ ማለት እሱም ይማርበታል በስራውም ነገር ያፍራል::
ለራስህ ስትል መልካም ሁን መልካምነት አያስከፍልም ::
ዛሬ ያጣነው ነገ እናገኘዋለን ዛሬ ያገኘነው ነገ እናጣዋለን ዱንያ እንዲህ ናት ፡፡
የሱሀቦች ዘመን
ሳኒ ይመር
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA