Get Mystery Box with random crypto!

ይቅር ባይ ሁን ቂም አትያዝ ቅይም አርግዘህ ክፋትን ከምትወልድ፣ የሸይጧንን ሙራድ | ★★የሱሀቦች ዘመን

ይቅር ባይ ሁን ቂም አትያዝ

ቅይም አርግዘህ ክፋትን ከምትወልድ፣ የሸይጧንን ሙራድ ከምትሞላና ነፍስህን በስቃይ አለንጋ ከምትገርፍ ፡፡ ይቅር ባይ ሆነህ የአላህን ውዴታ ማግኘት፣ የውስጥህን ሰላም ማግኘትህና ሸይጧንን ማስቆጨትህ ለድርድር የማይቀርብ ትልቅ ምርጫ ነው።
አላህ አፏ ባዮችን ይወዳልና የሱን ውዴታ አስበልጥ
ለአላህ ብሎ ዝቅ ያለ አላህ ከፍ ያደርገዋል
አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና ታገስ
አላህ አፋ እንዲልህ የምትፈልግ ከሆነ አንተም ሌሎችን አፋ በል
አላህ እንዲያዝንልህ የምትፈልግ ከሆነ አንተም ለባሮቹ እዘን
አላህ ይቅር እንዲልህ የምትፈልግ ከሆነ አንተም ይቅር ባይ ሁን
ሸኽ ኢብኑ ባዝ አላህ ይርሀማቸውና እንዲህ ብለዋል።
ነፍስያህን አፋታ (ይቅር ባይነትን) ካስለመድካት፦
ነፍስህ ሰላም ታገኛለች
ቀልብህ ይረጋጋል
አላህና ባሮቹ ዘንድ ደረጃህ ከፍ ያለ ይሆናል።
حديث المساء ٢١٢
ቂም ይዘህ ምን ታተርፋለህ
ይቅር ማለትህ እዝነትን እንደሚወልድ ሁሉ ቂም መያዝህ መበቀልን ይወልዳልና ተጠንቀቅ።
መች እንደምትሞት አታውቅምና እስከነ ጥፋትህ አላህ ፊት ከመቆምህ በፊት ነገ ዛሬ ሳትል የበደልከውን ሰው ይቅርታ ጠይቅ። ኩራትና መኮፈስን ከውስጥህ አስወግድ። ሸይጧን ከአላህ እዝነት ያባረረው ይህ ኩራቱ ነውና ተጠንቀቅ።
ከተበደልክ ደሞ ይቅር ባይ ሁን። ለምን ተነካሁ ለምን ይህ ተባልኩ በማለት የግድ ሁሉ ነገር እኔ እንዳልኩት ይሁን አትበል። አንዳንዴ እያወክም ቢሆን ተሸነፍ። አላህ ዘንድ ያለው የተሻለ ነውና ያንን ምረጥ። የግድ የማትተወው ሀቅ ካለ ደሞ ሳትቀያየምና ሳትቆራረጥ በአግባቡና በስርአቱ ጠይቅ።
በጣም የሚገርመው ደሞ እናት አባቱን፣ ወንድም እህቱን፣ ሚስትና ልጁን አልፎም ወድ ጓደኛውን ለትንሽ ጉዳይ ብሎ ተቆራርጦ፣ ተኮራርፈው፣ በጎሪጥ የሚተያዩ፣ በአሽሙር የሚተቻቹ፣ እንደ ጠላት የሚተያዩ፣ ሸይጧንን በመታዘዝ የሱን አላማ የሚያሳኩና የሰሩትን መልካም ስራ አላህ ዘንድ እንዳይደርስ በመሀል እንዲንጠለጠል የሚያደርጉ ብዙዎች አሉ።
ይቅርታ መጠየቅና አፋ ማለት የበታችነት ሳይሆን የበላይነት፣ የመዋረድ ሳይሆን የአዋቂነትና በሳልነት አልፎም የአርቆ አሳቢነት ምልክት ነው።
አላህ ሆይ ከዚህ ክፋ በሽታ አንተው ጠብቀን

ሳኒ ይመር ( @USTAZSANI )
የሱሀቦች ዘመን
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA