Get Mystery Box with random crypto!

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የሰርጥ አድራሻ: @seratebtkrstian
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.08K
የሰርጥ መግለጫ

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 125

2022-07-16 20:04:36 YouTube መጠቀም ለምትችሉ ቪዲዮውን ተመልከቱት ግን መጠቀም ለማትችሉ በAudio post አደርጋለሁ ከደቂቃዎች በኋላ!!
2.1K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 19:54:41 ከጋብቻ በፊት ድንግልናን መጠበቅ እንዴት ይቻላል? መጠበቅስ አስፈላጊ ነው? ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (ግብረ ሥጋ ግንኙነት) መፈጸም ዝሙት ነው ሊባል ይችላል? ሳላውቅ ሩካቤ ብፈጽም እንደ ኃጢያት ይቆጠርብኛል? ከጋብቻ በኋላ ከባሌ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር ሩካቤ ብፈጽም ዝሙት ነው ሊባል ይችላል?
ወዘተ.....
መፍትሔውስ ምንድነው ?

መልሱን እዚህ ቪዲዮ ውስጥ ያገኛሉ
!











2.1K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:22:21
ከጋብቻ በፊት ድንግልናን (ንጽኅናን) እንዴት መጠበቅ አለብን?

ነገ ከቀኑ 11:00 በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ላይ post ይደረጋል !!!


YouTube ለምትጠቀሙ ገብታችሁ Subscribe አድርጋችው የ ምልክቷን ነክታችሁ ጠብቁ!! ሊንኩ ይኸው
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

ግን YouTube ለማትጠቀሙ በተነጋገርነው መሠረት በAudio እዚሁ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ላይ post ይደረጋል!!!

እንዳያመልጣችሁ!! በእርግጠኝነት ታተርፉበታላችሁ!!!

መልካም ሌሊት
3.4K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 22:05:00
አብዛኛዎቻችሁ የጠየቃችሁት ጥያቄ YouTube ላይ የሚለቀቀው ትምህርት በtelegram ተጽፎ Post ይደረግ እኛ YouTube መጠቀም ለማንችለው የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳል!

ሥለ ጥያቄያችሁ በማመስገን ወደ መልሱ ስገባ Ethiopia ውስጥ አብዛኛው ሰው YouTube እንደማይጠቀም አውቃለሁ ያም የሚሆነው በ internat access ችግር ነው ። ሆኖም እኔ ደግሞ 1 video ለYouTube ብዪ ከቀረጽኩኝ በኋላ እንደገና ያንን ሁሉ ትምህር ወደ ጽሑፍ መቀየር በጣም ከባድ ነው በጣም ማለት ነው! አንድ የ30 ደቂቃ ትምህርት እየአንዳንዱን ቃል ልጻፍ ማለት እንደሚከብድ ትረዱታላችሁ ብዪ አስባለሁ እናም ብትችሉ ሙሉ ቪዲዮውን አይታችሁ ብትማሩ ደስ ይለኝ ነበር ግን ሥለ አልቻላችሁ video ቀረቶ በ Audio post ቢደረግ የሚሻል ይመስለኛ መጻፍ በጣም ስለሚከብድ እና ምን ታስባላችሁ? የተሻለ መንገድ ካለ ሐሳብ ብትሰጡኝ እቀበላለሁ ደግሞም ቪዲዮውን ቀኑን ሙሉ ስጽፍ እውላለሁ የሚል ካለም ይጻፍ እና ይላክልን post እናደርገዋለን እናም ምን ታሥባላችሁ በAudio ቢለቀቅ?
3.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:48:09 በእጮኝነት (ፍቅር ) ጊዜ መገናኘት ስላለባቸው 6 ምክንያቶች

መታየት ያለበት በዚህ ዘመን ላሉ ፍቅረኛሞች የሚሆን ትልቅ ትምህርት



4.6K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 09:10:03 የመልካም ሴት ጸባይ
መልካም ሴት ከፈለክ ጸባይዋን መርምር











8.2K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:03:55 መልካም ቤተሰብ
ክርስቲያናዊ ቤተሰብ አመሠራረት የልጅ አስተዳደግ መንፈሳዊ ሰው ማድረግ!









9.3K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:05:53








የዚህ ሁሉ ጥያቄ ቪዲዮ ውስጥ መልስ አለ ስለዚህ ቪዲዮውን አይታችሁ መልሱ!!!

//1// ለሚከተሉት ጥያዌዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጥ!

፩ መጻሕፍት ተጽፈው ሕግጋት በመጻሕፍት ከመሠጠታቸው በፊት በነበረው ዘመን የነበሩ አባቶች ይመሩበት የነበረው ሕግ ምን በመባል ይታወቃል!

ሀ ዐሥሩ የኦሪት ሕግጋት
ለ ማኅበራዊ ሕግ
ሐ ስድስቱ ቃላተ ወንጌል
መ የኅሊና ሕግ
ሠ ሁሉም መልሰ ናቸው።


፪ ለአዳምና ሔዋን ''ዕፀ በለስን አትብሉ'' ተብሎ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ትእዛዝ የየትኛው ሕግ ምሳሌ ነው?


ሀ የኅሊና ሕግ
ለ ያልተጻፈ ሕግ
ሐ ዐሥሩ የኦሪት ሕግጋት
መ የተጻፈ ሕግ
ሠ ስድስቱ ቃላተ ወንጌል

//2// ለሚከተሉት ጥያቄዎች የተብራራ መልስ ስጥ።

፩ ዐሥሩ የኦሪት ሕግጋት መኖር ያስፈለገባቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?

፪ በኅሊና ሕግ ምክንያት ሰዎች ከማይፈጽሟቸው ድርጊቶች ሦስት ምሳሌዎችን ጥቀስ?

፫ ስድስቱ ቃላተ ወንጌል የሚባሉትን ዘርዝር?

፬ አስርቱ ትዕዛዛትን ዘርዝር?

፭ ሥነ-ምግባር ማለት ምን ማለት ነው?

ቪዲዮውን ያየ ሰው ሁሉንም ይመልሰዋል በእርግጠኝነት!!








9.6K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 09:42:13 " ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ሕገ እግዚአብሔር ሕገ ኦሪት ሕገ ወንጌል ሕገ ኅሊና












YouTube ለምትጠቀሙ ይኸው ተማሩ ለማትጠቀሙ ደግሞ በጽሑፍ እስኪጻፍ ታገሱን!!
8.5K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 09:19:29 ጸሎት

ጸሎት ቋንቋ ነው!

ለምሳሌ እኔ እና እናንተ የምንግባባው በአማርኛ ቋንቋ ነው አይደል? አዎ!

እግዚአብሔር እና የሰው ልጅ የሚግባቡበት ቋንቋ ደግሞ ጸሎት ነው!

ጸሎት ትልቅ ኃይል አለው!
በጸሎት ሁሉንም ነገር ማድረግ ይቻላል!

ከአባቶቻችን አበው መካከል ጸሎት የማያረግ ማን አለ?
ሐዋርያቶች ይጸልዩ ነበር
ጻድቃን ይጸልዩ ነበር
ሰማዕታት ይጸልዩ ነበር
ባህታውያን ይጸልዩ ነበር
አባቶቻችን በሙሉ ይጸልዩ ነበረ ምክንያቱም መጸለይ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደሆነ ስለሚያውቁ!

እናም እናንተ ብትችሉ 7 ጊዜ ጸልዩ ባትትችሉ 3 ባትችሉ 2 የመጨረሻ ቢያቅታችሁ 1 ጊዜ ጸልዩ !

እስኪ አስተውሉት በ1 ቀን ውስጥ 24 ሰዓት አለ አይደል? ታዲያ በእነዚህ 24 ሰዓት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ለ5 ደቂቃ መነጋገር ከብዷችሁ ነው? ስለዚህ ጸልዩ!

የጸሎትን ጥቅም ልንገራቹ እና ልጨርስ!

አንድ ነብር ሚዳቋ እና ከርከሮ ነበሩ! ነብሩ ተርቤያለሁ እና እባክህ አምላኬ አብላኝ አብላኝ እያለ በጽኑ ይጸልያል! ሚዳቋም በበኩሏ እባክህ ጌታዪ አድነኝ አድነኝ አታስበላኝ አድነኝ እያለች በጽኑ ትለምናለች ! ከርከሮው ግን አይልይም ዝም ብሎ ይበላል ይጠጣል ዝም ብሎ ይኖራል ! ነበብሩ እና ሚዳቋ ከጸለዩ በኋላ ነብሩም ምግብ ሊፈልግ መዘዋወር ጀመረ ሚዳቋም ሳሯን መጋጥ ጀመረች ! ሲዘዋወር ነብሩ ይቺኑ ሚዳቆ ያያታል እሷም ቀና ስትል ታየዋለች ፊት ለፊት ተፋጠጡ ! ነብሩም አምላኬ ሆይ ጸሎቴን ሰማኸኝ ማለት ነው ብሎ ሊበላት ሲሮጥ ወደሷ ሚዳቋም አድነኝ ብዪህ ልታስበላኝ ነው? ታደርገውም ብላ መሮጥ ጀረች ነብሩ አብላኝ አብላኝ ይላል በልቡ ሚዳቋም አውጣኝ አውጣኝ ትላለች ! ሲራራጡ ሚዳቆዋ ከርከሮ ወዳለበት እሮጠች እሷን እይዛለሁ ብሎ ነበሩ ሲከተላት ተኝቶ የሚበላ የሚጠጣውን አገኘው ከዛም እራጫውን ትቶ ከርከሮውን በላው! ያቺ ሚዳቋ አመለጠች !

ለእዚህ ነው አባቶቻችን

አውጣኝ ያለ ውጣ
አብላኝ ያለ በላ
የተኛ (ያልጸለየ) ተበላ! የሚሉት!

ጸልዩ ተኝታችሁ እንዳትበሉ ዋ!!!

የተቀደሰ ቀን ተመኘሁላችሁ!!!


ዲ/ን ፍቅረ አብ
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube
@seratebtkrstian

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ











9.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ