Get Mystery Box with random crypto!

ጸሎት ጸሎት ቋንቋ ነው! ለምሳሌ እኔ እና እናንተ የምንግባባው በአማርኛ ቋንቋ ነው አይደል? | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ጸሎት

ጸሎት ቋንቋ ነው!

ለምሳሌ እኔ እና እናንተ የምንግባባው በአማርኛ ቋንቋ ነው አይደል? አዎ!

እግዚአብሔር እና የሰው ልጅ የሚግባቡበት ቋንቋ ደግሞ ጸሎት ነው!

ጸሎት ትልቅ ኃይል አለው!
በጸሎት ሁሉንም ነገር ማድረግ ይቻላል!

ከአባቶቻችን አበው መካከል ጸሎት የማያረግ ማን አለ?
ሐዋርያቶች ይጸልዩ ነበር
ጻድቃን ይጸልዩ ነበር
ሰማዕታት ይጸልዩ ነበር
ባህታውያን ይጸልዩ ነበር
አባቶቻችን በሙሉ ይጸልዩ ነበረ ምክንያቱም መጸለይ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደሆነ ስለሚያውቁ!

እናም እናንተ ብትችሉ 7 ጊዜ ጸልዩ ባትትችሉ 3 ባትችሉ 2 የመጨረሻ ቢያቅታችሁ 1 ጊዜ ጸልዩ !

እስኪ አስተውሉት በ1 ቀን ውስጥ 24 ሰዓት አለ አይደል? ታዲያ በእነዚህ 24 ሰዓት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ለ5 ደቂቃ መነጋገር ከብዷችሁ ነው? ስለዚህ ጸልዩ!

የጸሎትን ጥቅም ልንገራቹ እና ልጨርስ!

አንድ ነብር ሚዳቋ እና ከርከሮ ነበሩ! ነብሩ ተርቤያለሁ እና እባክህ አምላኬ አብላኝ አብላኝ እያለ በጽኑ ይጸልያል! ሚዳቋም በበኩሏ እባክህ ጌታዪ አድነኝ አድነኝ አታስበላኝ አድነኝ እያለች በጽኑ ትለምናለች ! ከርከሮው ግን አይልይም ዝም ብሎ ይበላል ይጠጣል ዝም ብሎ ይኖራል ! ነበብሩ እና ሚዳቋ ከጸለዩ በኋላ ነብሩም ምግብ ሊፈልግ መዘዋወር ጀመረ ሚዳቋም ሳሯን መጋጥ ጀመረች ! ሲዘዋወር ነብሩ ይቺኑ ሚዳቆ ያያታል እሷም ቀና ስትል ታየዋለች ፊት ለፊት ተፋጠጡ ! ነብሩም አምላኬ ሆይ ጸሎቴን ሰማኸኝ ማለት ነው ብሎ ሊበላት ሲሮጥ ወደሷ ሚዳቋም አድነኝ ብዪህ ልታስበላኝ ነው? ታደርገውም ብላ መሮጥ ጀረች ነብሩ አብላኝ አብላኝ ይላል በልቡ ሚዳቋም አውጣኝ አውጣኝ ትላለች ! ሲራራጡ ሚዳቆዋ ከርከሮ ወዳለበት እሮጠች እሷን እይዛለሁ ብሎ ነበሩ ሲከተላት ተኝቶ የሚበላ የሚጠጣውን አገኘው ከዛም እራጫውን ትቶ ከርከሮውን በላው! ያቺ ሚዳቋ አመለጠች !

ለእዚህ ነው አባቶቻችን

አውጣኝ ያለ ውጣ
አብላኝ ያለ በላ
የተኛ (ያልጸለየ) ተበላ! የሚሉት!

ጸልዩ ተኝታችሁ እንዳትበሉ ዋ!!!

የተቀደሰ ቀን ተመኘሁላችሁ!!!


ዲ/ን ፍቅረ አብ
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube
@seratebtkrstian

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ